Home / Portfolio / HEBREWS / The Fulfillment of the Davidic Covenant in Jesus of Nazareth, the Exalted Son, Psalm 2 (Part 8)

The Fulfillment of the Davidic Covenant in Jesus of Nazareth, the Exalted Son, Psalm 2 (Part 8)

Posted on

–   This is my recommendation that you would first listen to part seven of this series for comprehensiveness. This is the last session of part seven   –

አሕዛብ ለምን ያጕረመርማሉ? ወገኖችስ ለምን ከንቱን ይናገራሉ? የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሢሑ ላይ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። ማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል። በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል። እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ። ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ። ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ። በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ።

አንተ ልጄ ነህ (መዝ 2:7)

 • ይህ መዝሙር ከዳዊት ቤት የሆነው ልጅ ንጉስ ሆኖ ሲቀባ የሚዘመር የክብረ-በዓል መዝሙር ነው (ምናልባት 2 kings 11:12; 1King 1:39) ምንም እንኳ ይህ መዝሙር በዚህ ቀን መዘመሩ የሚያሳይ ክፍል ባይኖርም ነገር ግን ይህ መዝሙር በዳዊት የተስፋ ኪዳን ላይ (2ሳሙ 7:14) መመስረቱ ግን የማይካድ እውነት ነው።
 • ይህ መዝሙር በአራት chiastic አንጓዎች ተያይዟል።
A የአሕዛብ አመጽ፡ ነገሥታት በያህዌህና በመሢሁ ላይ (2:1-3)
            B በሰማይ ያለው የያህዌህ ምላሽ  (2:4-6)
            B’ የያህዌህ አዋጅ ቃል (2:7-9)
               A’ የመሲሑ አገዛዝ በምድር ዙሪያ (2:10-12)
 • ትንታኔ፡- መዝሙሩ በነገስታት ሤራና መናወጥ ጀምሮ እ/ርን በሚታመኑና ለመሲሁ ለሚገዙ በመባረካቸው ይጨርሳል። በኢየሩሳሌምንጉስሆኖበመቀባትየተሾመውንጉስበወሰን-መጠቅገዢው / universal king of kings በያህዌህ የተሾመንጉስ መሆኑንና በዚህ ንጉስ ያህዌህ ወሰን መጠቅ መንግሥቱን በመድር ዙሪያ እንደሚያሰፍን የሚያውጅ መዝሙር ነው። ለምድር ሁሉ ሰላም የሚመጣው በዚህ መንገድ ነው (cf. Pss 72; 89; 132; Isa 9:6–7; 11:1–10))
 1.  የአሕዛብ አመጽ/ ምክክር፡ ነገሥታት በያህዌህና በመሢሁ ላይ (The kings against the King 2:1-3) አሕዛብለምንያጕረመርማሉ (ያሴራሉ)? ወገኖችስለምንከንቱንይናገራሉ (ያውጠነጥናሉ)?የምድርነገሥታትተነሡ፥አለቆችምበእግዚአብሔርናበመሢሑላይእንዲህሲሉተማከሩ።“3ማሰርያቸውንእንበጥስ፥ገመዳቸውንምከእኛእንጣል።
  1. ያውጠነጥናሉ፦
   • ምስጉን የሆነው ጻድቅ የእ/ርን ሕግ ሌሊት ቀን ያሰላስላል (ም. 1)
   • አመጸኛ ነገስታት ግን እንዴት አድርገው ከእ/ርና እ/ር ከሾመው መሲህ እንደሚያፈነግጡ ይመካከራሉ።
   • ሤራቸው ያህዌህ የሾመውን የዳዊትን ንግሥና ከላያቸው አውልቀው ለመጣል ሲሆን ይህም የያህዌህን ወሰን-መጠቅ መንግሥት እውን ከመሆን እክል ይሆናል። (ልክ ክርስቶስ እውነተኛው የዳዊት ልጅ ሲገለጥ መንግስቱን ሰዎች ሊቃወሙትና ለሰዎች አመጽ ሊገፋ የሚችል ከመሆኑ ጋር ይዛመዳል) (v. 2).
   • ይህ የነገስታት ሤራ ከመዝ 1 ላይ ካለው ክፉዎች ምክር ጋር ይመሳሰላል (1:1); ጻድቃን የያህዌህን ሕግ በቀንና በሌሊት ሲያሰላስሉ፤ እነዚህ ነገስታት ግን ተሰብስበው የሚያሰላስሉት ሤራ ነው።
  2. በእግዚአብሔርና በመሢሑ/ በተቀባው፡
   • ይህ ሤራ ያነጣጠረው በያህዌህና በመሲሁ ላይ ነው። ንግስናውን የተቀበለው ሹመት በመሆኑ፤ የእ/ር መንፈስ ያረፈበትና ማረጋገጫ ማሕተብ ያለበት ንጉስ ነው።
   • ግን ለምን መሲሁንና ያህዌህን በአንድነት እነዚህ ነገስታት ተመለክቱ? የቅርብ ምሥራቅ ታሪክ እንደሚያረጋግጥልን፡ነገሥታት በቀጥታ ከአማልክት የተወለዱ “የአምካክ ልጆች” እንደሆኑ ስለሚያምኑ መንግስታቸው ከአማክቶቻቸው የተቀበሉት በመሆኑ ህዝቡን ያለጥያቄ ይገዛላቸዋል። ብርታታቸው የተመሰረተው በአማልክቶቻቸው ብርታት ነው። (kings” considered themselves to be “divine” monarchs, who are here portrayed as bringing together all their “sacral” powers and forces against the Lord God and his anointed)
   • መሲሁ ግን ልጅነቱን የሚለማመደው በያህዌህ ሕግ ሥር እንጂ ከራሱ የመነጨ አይደለም። ንጉሱ የእ/ርን ሕግ ያሰላስላል፤ የሕጉ መጽሀፍ የንጉሱ መተዳደሪያ ሕገ መንገስት ነው። መሲህነትን ገንዘቡ ያደረገ እለት በመጀመሪያ ታማኝነቱን ለኪዳኑ ያደረገ እንደሆን ነው። ከዚያ በኋላ ነው በዘይት ተቀብቶ (‘በያህዌ የተቀባው’ cf. 1 Sam 16:13; 1 Kings 1:39) በያህዌህ የተሾመ ንጉስ ሆኖ ዘውድ የሚደፋው። (2 Kings 11:12), 
   • ይህ ማለት በዳዊት ቤት ተስፋ መሰረት የነገሰው ምንም እንኳ የማይታዘዝ አመጸኛ ቢሆንም ለዳዊት ያህዌህ የገባለት ተስፋ ግን ዘላለማዊ ስለሆነ አይሻርም። ልጁን በዘንግ ቢገረፍም ለጥፋቱ፤ መንግስቱ ግን እንደ ሳኦል ቤት አይሻርም። The actual state of the kingdom in Israel at any age was at best a pale representation of the ideal kingdom.
   • ነብያት ወደ ፊት በዳዊት ልጅ በክርስቶስ ምድር እንድምትገዛ ተንብየዋል (Isa 9:2–7; Jer 23:5–6; 33:14–16; Ezek 34:23–24; 37:24–28; Hos 3:5) የምድር ሕዝቦች ሁሉ ለእርሱ መንገሥት ይገዛሉ (Isa 11:10; Mic 4:1–5). 
   • ነብያት ደጋግመው፤እንዲሁም ጌታችን ኢየሱስና ሐዋርያት፤ አህዛብ በእ/ርና በክርስቶስ/ በመሲሁ ላይ እደሚነሱ ተናግረዋል (ክርስቶስ ተመልሶ እስኪመጣና መሲሃዊው ዘመን እስከሚያበቃ ድረስ ይህ ሤራ ይቀጥላል) (Zech 12:1–9; 14:1–11; Matt 24:7; Luke 21:10; 2 Thess 2:3–4, 8–12; Rev 17:14; 19:14–21).
  3. የአመጹ፤ የሴራቸው አላማ “በልዕልና” ላይ የተመሰረተ ነውማሰርያቸውን እንበጥስ፥ ገመዳቸውንም ከእኛ እንጣል።
   • በቅርብ ምሥራቅ ታሪክ አስገባሪ (suzerains) and ገባሪ (vassals) የተለመደ የመንግሥታት አሰራር ነበር። ለምሳሌ በታወቀው የሒታይት ሰነድ ይታያል።
   • በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ደግሞ ለአይነተኛነት (ኢያሱ 9:6-8/ ሆሴ 12:1)
   • ዘማሪው የምድር ነገስታት ሤራ አዲስ ዘውድ ለደፋው መሲሕ ላለመገበር፤ ላለመገዛት፤ ውላቸውን ለመበጠስ ነው፦ ይህም በእነዚህ ቃላት ተገልጧል (ሰንሰለታቸውን እንበጥስ፤ የእግር ብረት አውልቀን እንጣል)። እነዚህ ዘይቤያዊ አነጋገሮች በእንሥሳት ላይ ተሽከርካሪ ለመግፋትና ለእርሻ የሚታሰሩ ናቸው (Jer 27:2; 30:8; Nah 1:13).
   • ማሰርያቸውን…ገመዳቸውንም…” የሚለው የሚያሳየን የመሲሁና የያህዌህ ንግሥና አንድ መሆኑን ነው የመሲሁ ሥልጣን የተመሰረተው ያህዌህ/ አብ ለቀባው ለልጁ በሰጠው ዕውቅ ላይ ነው። ከዚህ የተነሳ ለያህዌህ መገዛት ነገር ግን ለቀባው ለልጁ አለመገዛት አይቻልም።
   • ከዚህ የተነሳ ለምሳሌ ሐዋርያው ጴጥሮስ ይህ የሰቀላችሁት የናዝሬቱን ኢየሱስ ‘ጌታም ክርስቶስም አደረገው ይላል። The enthronement of his Messiah at his right hand constitutes the basis for the apostolic preaching (Acts 2:36).
 2. በሰማይ ያለው ንጉሠ-ነገሥት ያህዌህ 2፡4-6 “Psalm 2:4–6 በሰማይ የሚኖር እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል። በዚያን ጊዜ በቍጣው ይናገራቸዋል፥ በመዓቱም ያውካቸዋል። እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።”
  • ይህ ሳቅ ምጸታዊ ነው። የእነዚህ ነገስታት ሤራ ከንቱ እሆኑን ያሳያል። በጠላቶቻችን ላይ ይስቃል ምክኒያቱም መጨረሻቸውን ስለሚያውቅ፤ ሐሳቡ ስለማይሻር።
  • ይህ ንቀት ግን እ/ርን የሚመለከት ነውና መሲሁ በእርሱ መታመን ይችላል።
  • ይህ የተቀባው የዳዊት ልጅ የሚገዛው ከጽዮን ነው, ያህዌህ የመረጠው የማደርያ ሥፍራ ናት (cf. Ps 132; Deut 12:14, 18; 14:23; 15:20). ያህዌህ በመገኘቱ ከተማዋን ቀድሷታል; ስለዚህ, ጽዮን‘የተቀደሰ ተራራው” ነች.” ሆኖም ግን መንግሥቱ በጽዮን ተራራ፤ በመቅደሱ ሥፍራ፤ ብቻ እንዳልተወሰንም እናውቃለን (1 Kings 8:27; cf. Isa 66:1). ነገር ግን በተለየ መልክ እ/ር ከህዝቡ ጋር በጽዮን ይኖራል። ስለዚህ ጽዮን የእርሱ የእግር መርገጫ ናት (1 Chronicles 28:2; Pss 99:5; 132:7; Lam 2:1; Matt 5:35).
 3. የያህዌህ አዋጅ 2፡7-9
  • (ይህ አዋጅ የዳዊትን ቤት ንግሥናና የያህዌህን መንግሥት በምድር መመስረቱን ያውጃል) “ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ። ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ። በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ”
  • አሁን ንጉሱ ከያህዊህ ጋር ያለውን ልዩ ግንኙነት ያውጃል (publicly proclaiming his own relationship with God, the Great King.)
  • ይህ አዋጅ ሁለት ነገሮችን ያካትታል።
   • የመሲሁን ልጅነትና (v.7) ከእ/ር ጋር ያለውን ግንኙነትና (የአባትና የልጅ) 
   • የመሲሁ መታዘዝና ከአህዛብ ጋር ያለውን ግኙኝነት ያሳያል።
  • ይህ ልጅነት መብትን ያሳያል legal right.
  • ይህ ልጅነት/ ግንኙነት የሚጀምረው ንጉስ ሆኖ በተቀባ እለት ነው። “እኔ ዛሬ ወለድሁህ።.”
  • ስለዚህ ይህ የተቀባው ልጅ የአባቱን ፈቃድና መሻት ለሕዝቡ ያንጸባርቃል። የሚያንጸባርቀውም በመታዘዝ ነው። ልጅነቱ ግን  በዙሪያቸው ያሉ አህዛብ እንደሚያደርጉት የባህርይ ሳይሆን  ግብራዊ ነው (functional)
  • መንግስቱ በያህዌህ የተሰጠውና እንደ ያህዌህ በጽድቅ ሊገዛ ነው። ይህም “ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥እኔ ዛሬ ወለድሁህ።(Jesus is the Christ, the “Son” of God by the Father’s proclamation (Matt 3:17; Mark 1:11; Luke 3:22). He is seated at the right hand of the Father (Acts 2:33; Heb 1:3), the place of kingly rule and authority.)
  • የተቀባው ንጉስ ሥራው የማይታየውን አምላክ አገዛዝ በምድር ዙሪያ ማንጸባረቅና ማስፈን ነው።”
  • እንደ ልጅነቱ መንግሥቱ እንድትሰፋ ይጠይቃል ምክኒያቱም የእ/ር አላማ ይህ ስለሆነ። አባቱ የምድርን ሁሉ ዳርቻ እንደ ርስት መስጠቱ የተመሰረተው በዚሁ ግንኙነቱ ነው።
  • ይህ ተስፋ ከክርስቶስ የተነሳ የአማኞችም ተስፋ ሆኗል (cf. Rev 2:26–27; 6:10; 19:15).
  • ከባቢሎን ግንብ ፍርድ በኋላ የተበታተነችው ምድር በመሲሑ በኩል ትሰበሰባለች (Gen 11:1–9), ያ የባቢሎን ዓመጽ ግን አሁን በእነዚህ ነገስታት ቀጥሏል።
  • እ/ር ለዳዊት የተስፋ ኪዳን ከገባለት (2 Sam 7:13–16) እና ደግሞ በመሃላ ከጸናለት በኋላ (2 Sam 23:5) የእ/ር ህዝብ በነብያቱ ትንቢት መሰረት ምድርን እረፍት የሚሰጠውን ንጉስ ሲጠባበቁ ነበር (Isa 2:2–4; 4:1–6; 9:6–7; 11:1–16; Jer 33:14–26; Ezek 37:24–28; Mic 4:1–5; Zech 9:9–10:1).
  • በመዝሙር 72 ላይ ለተቀባው ንጉሡ ሰለሞን የቀረበው ፀሎት
   • ግዛቱ ምድርን ያካላል “ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይገዛል
   • አገዛዙ የእ/ርን ክብር ይገልጣል “ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። 19የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘላለም ይባረክ፤ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን።
   • መንግሥቱ በፍትህና በጽድቅ ይዘረጋል “በጽድቅ፥ ችግረኞችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ…ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፥ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል። 14ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል፤ ስማቸው በፊቱ ክቡር ነው።
   • መንግሥቱ ለእ/ር ሕዝብ በረከትን ያፈሳል “ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ….በዘመኑም ጽድቅ ያብባል፥ ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።
   • የያህዌህ ሉዓላዊ ሥልጣን እስከ ምድር ዳርቻ ይሠፍናል (cf. 72:8–11) “በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ። 10የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ። 11ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።
  • ያህዌህ አምላክ አብርሃምን ከከለዳውያን ምድር ከዑር ሲጠራው ርስት አድርጎ ሊሰጠው የወደደው ምድር ከከነዓን ምድር ያለፈ መሆኑን ይጦቁመናል።፡(cf. Gen 22:17–18; 26:4; 28:14; cf. Mal 1:5).
  • ያህዌህ ዓለም ዓቀፍ በረከትን በዓለም አቀፍ መንግሥቱ በቀባው በዳዊት ልጅ በኩል በአህዛብ ሁሉ ላይ ይገልጣል።፡ [Amos 9:9–15 and Acts 15:13–18]
  • ያህዌህ ለመሲሁ (ለአብርሃም ልጅ፤ ለዳዊት ልጅ) የሰጠው ተስፋ መንገሥቱ ሉዓላዊ ወሰን መጠቅ አገዛዝ መሆኑን ሲጠቁም
   • “ብረት በትር…እንደ ሸክላ እንደሚያደቅ” መሳሪያ ይመስለዋል። ይህም የመሲሁ ሥልጣን ያሳያል (cf. Jer 19:11).
   • ሆኖም ግን የመሲሁ ሥልጣን ከያህዌህ የመነጨ ሹመት እንጂ የራሱ አይደለም።፡(Ps 76:12).
   • በትር የሚለው ሥልጣንን ያመለክታል። “The “scepter” (šēḇeṯ) is a symbol of rule. It is the means of discipline and judgment. As the scepter of a monarch, it symbolizes here the authority granted by God to rule with great power over the nations.”
  • “አሕዛብን” ለ “ርስትህ” (κληρονομία; cf. Heb. 1:2, 4). ይህ ርስት በአብርሃም ተስፋ ላይ የተመሰረተ ነው….ርስት….ምድር ዳርቻ….ነገሥታት….በአብርሃም ተስፋ ውስጥ ይገኛሉ።
   • የምድርን ነገሥታት ከበታቹ ሊያስገዛለት:
   • አህዛብን ርስት አድርጎ ሊሰጠው
   • የግዛቱን ክልል እስከ ምድር ዳርቻ ሊያደርግለት
 4. በምድር ያለው የመሢሁ አገዛዝና የአህዛብ ተገቢ ምላሽ 2:10-12 “አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፤ እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ። 11 ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ። 12 ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።”
 • መገዛታቸው የተገለጠው ”አገልጋይ” መሆናቸው ነው
 • ይህም በፈቃዳቸው በደስታ “በረዓድም ደስ ይበላችሁ።”
 • ገባሪ (vassal) እንዲሆኑና ይህም የእ/ርን አስገባሪነት (“lordship” suzerainty) መቀበላቸው ነው

ዕብራውያንና መዝ 2:7-8

ለዳዊት ልጅ የተሰጠው ተስፋ በአዲስ ኪዳን ከልጁ የተነሳ ለተገኙት ልጆችም ጥቅም ላይ ውሏል (Hebrews 2:10 ብዙልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ፥ ከእርሱ የተነሣ ሁሉ በእርሱም ሁሉ ለሆነ፥ ለእርሱ ተገብቶታልና) ሆኖም ግን ገና ወደ ዚያ አልደረሰም። እዚህ ጋር  ልጅ የሚለው ክርስቶስን ነው።ከእርሱ በፊት ብዙ የዳዊት ልጆች ነበሩ; ከአሁን በሁላ ግን እርሱ ብቻ የዳዊት ልጅ ነው። ግን ደግሞ ብዙ ልጆችን ወደ ክብሩ ያመጣል። In one sense it is an exclusive designation, messianic son, after him no one will be called as such. And yet there is this sonship by adoption has been in use.  The verse as a whole means: at some point in the past, God made statements of permanent validity declaring Christ to be his Son.
 • ዛሬ የሚለው የዳዊት ልጅ ንጉስ ሆኖ ሲቀባ ነው። ታድያ ለክርስቶስ ኢየሱስ ምን ማለት ነው?
 • ዛሬ የሚለውን ቃል ለመረዳት ወደ አዲስ ኪዳን እናምራ። ይህ መዝሙር በአዲስ ኪዳን በጥቅም ላይ ውሏል፡
 1. ከጥላነት አንጻር (from the perspective of typology)፤ ኢየሱስ የመዝሙር ም.2 ፍጻሜ ነው። የማቴዎስ፤ ማርቆስና ሉቃስ ወንጌላት በአንድነት በዚህ መዝሙር ላይ በመመርኮዝ ደጋገመው ክርስቶስ ኢየሱስ የዚህ ተስፋ ወራሽ እንደሆን አሳይተውናል።
  1. ኢየሱስ ሲጠመቅ የመጣለት ድምጽ ላይ “የምወድህ ልጄ አንተ ነህ” (መዝ 2፡7; cf. Matt 3:17; Mark 1:11; Luke 3:22). ክርስቶስ ሲጠመቅ አባቱ የመሲህነት ቢሮውን አረጋገጠለት። (Mk. 1:11 with Is. 42:1; Acts 4:25–28 (conflated with Ps. 88:21–22a and Is. 42:1); Acts 13:33-37, cf. v. 27; Rev. 2:26f.; cf. 12:5; 19:15)
  2. ወንጌላት ኢየሱስ የዳዊት ልጅ እንደሆን ያረጋግጡልናል (Matt 1:1; Luke 2:4, 11),
  3. የዳዊትን ተስፋና ዙፋን የመውረስን መብትና ሹመት ተቀብሏል (Luke 1:32),
  4. በማዕረግ የተለየ ልጅነትን ተቀብሏል (Matt 3:17; Luke 9:35; Heb 1:5),
  5. በሰማያት የተቀመጠውና ዳግም የሚመለሰው ሁሉን ከእግሩ ሥር ይገዛል ይህም የመዝ 2:8 ፍጻሜ ነው (1 Cor 15:25–27; Heb 2:5–8).
 2. የመጀመሪያቱ ቤተክርስቲያን በዚህ መዝሙር 2 ላይ የተጻፈው ሁሉ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ መፈጸማቸውን ሰብካለች። Acts 4:25–28
  1. በመዝሙር ሁለት ላይ የነበረው ሤራ (የአለቆች፤ ነገሥታት፤ ህዝቦችና ወገኖች መዝ 2:1-2) በክርስቶስ ኢየሱስ ሞት ጊዜ በአለቆች ሔሮድስና ጳንጦስ ጲላጦስ፤ በካህናት፤ የእሥራኤል ሽማግሌዎችና አህዛብ/ የእሥራኤል ሕዝብ በአንድነት ካደረጉት ሤራ ጋር ተመስሏል።
  2. ምንም እንኳ ተባብረው ሤራን ቢጠነሥሱ ሆኖም ግን ይህ ሤራ የራሱ የእ/ር አብ ዕቅድ ነበር (Acts 4:28; 1 Cor 2:8)
  3. ሐዋርያው ጳውሎስ ይህ መዝሙር “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ የሚለው” በክርስቶስ ኢየሱስ ልጅነት፣ በሞቱና በትንሳዔው ተፈጽሟል።  (which confirmed God’s promises in Jesus as the Messiah (Acts 13:32–33).)
  4. ሐዋርያው ዮሐንስ በራዕይ-ነክ አነጋገር ከሴቲቱ የተወለደው እርሱ ዘንዶውን ያሸነፈና ህዝቦችን በብረት በትር የሚገዛ እንደሆን ያውጃል . “rule all the nations with an iron scepter” (Rev 12:5). He is the Rider on the white horse who will “strike down the nations” in the day of God’s wrath (Rev 19:15; cf. 11:16–18).”
 3. በዕብራውያን መጽሀፍ ላይ በመዝሙር 2:8 ተስፋ መሰረት የተሾመው የልጁን/ የመሲሁን ክብር ይገልጥልናል , “የእ/ር ክብር መንጸባረቅና የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ ነው” ሐጥያትን ለመሸከም ዝቅ ያለው እርሱ በዚህ ተስፋ መሰረት እንደገና ከብሮ እናየዋለን (1:3), ከዚህ ሹመቱ የተነሳ ከመላዕክት ይልቃል (1:5–6).
  1. ስለዚህ ሐዋርያት 13:33–37, የተመረኮዘው በ መዝሙር 2 ላይ ሲሆን ይህም ደግሞ በጠጨማሪ ያህዌህ ለዳዊት በገባለት ኪዳን (2 Sa. 7: 1-18) ላይ የተመሰረተ ነው። (compare Acts 13:32f. with Heb. 1:1f. In Acts 13:33–37, as in Heb. 1 and 2 Sa. 7 is associated with Ps. 2:7; but whereas Paul in Acts is concerned to witness to the fulfillment of prophecy in the resurrection, Hebrews is exploring the significance of Christ’s Sonship
 4. Σήμερον (ዛሬ) (3:7, 13, 15; 4:7; 5:5; 13:8; Cf. Acts 13:33) ስለዚህ ይህ ዛሬ የሚለው የኢየሱስን እርገትና በእ/ር ቀኝ መቀመጥ (exaltation or enthronement) ያሳያል። ይህም በዕብ 1:5 ላይና በዕብ 1:13 ላይ በተደጋገመው ቃል ማረጋገጥ ይቻላል።

© 2014, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top