የአዲስ ኪዳን ሐቲት
New Testament Exegesis
-
የዐደራ ኑዛዜ ክፍል አንድ፡ በወንጌል ዙሪያ የተደራጀ ሕይወትና ማንነት
2 ጢሞቴዎስ ሕይወትን የሚቃኝና ሕይወታችንን በቅደም ተከተል የሚያደራጅ መልዕክት ነው። መጽሐፉ ነገሮችን በጥቁርና በነጭ ቁልጭ አድርጎ የሚያስቀምጥ መልዕክት ነው። ለግራጫ ሥፍራ የለውም። “የሚቃኝ” ስንል ወደ ዋነኛ ጥሪያችን እንድንመለስ፣ ትኩረታችንን እንድናስተካክል፣ ዋነኛውን ዋነኛ እንድናደርግ፣ የከበረውን ከተዋረደው እንድንለይ የሚያደርገን መልዕክት ነው ማለታችን ነው። ዴማስ ወደ ተሰሎንቄ ምን ሊሰራ እንደሄደ አልተነገረንም። በአንድ ወቅት ግን እንደ ጢሞቴዎስ አብሮ የወንጌል ሰራተኛ ነበር (ቆላ 4፡14; ፊል…
-
«በእኔ ኑሩ፣ በፍቅሬ ኑሩ!» (ዮሐ. 15:9-17)
በቨርጂንያ በምትገኘዋ ‘የቃል ኪዳን ወንጌል ቤተ ክርስቲያን’ በዘመን መለወጫ ዋዜማ (12/31/2020) የተካፈልኩት ቃል ነው። በዚህ በያዝነው ዓመት የቤተ ክርስቲያን ልሳን የፍቅር እንዲሆን፣ የእርሱን ፍቅር ተረድተን ከግንዱ ጋር የምንጣበቅበት፣ ብዙ የምናፈራበት ይሁንልን። ከግንዱ ጋር የተጣበቀ እንጂ «ከውጪ ተለጣፊ ቅርንጫፍ» ፍሬ አያፈራም። ይህንን አብ ይቆርጠዋል። ግን በእርሱ የሚኖሩትን ፍሬ እንዲያፈሩ አብ ይገርዛቸዋል። ውድ ወዳጆቼ፣ ከእርሱ ጋር እንጣበቅ፣ በእርሱ እንኑር። እናፈራለንና። አሊያ “ያለ…
-
የተሰቀለ-ክርስቶስ፡ ክርስቶስ እንደተሰቀለ ሆኖ በመልዕክታችን ይኑር
የአንደኛ ቆሮንቶስ 1:10 – 2:5 ሐቲት ኢየሱስን እንደ “ክርስቶስ” መቀበል እና እንደ “ተሰቀለ-ክርስቶስ” መቀበል ይለያያሉ። እኛ የምንሰብከው “የክርስቶስ መስቀል” ከሌሎች መስቀሎች እንዲለይ ያደረገው፤ “መሰቀል” የሚባለው እውነታ አይደለም (በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አይሁድ ወጣቶች ተሰቅለው ነበር – በተለይ በ4 ዓ.ዓ. አካባቢ ላይ)፤ ክርስቶስም የሚለው ቃል አይደለም (ብዙ መሲህ-ነኝ ባዮች ከኢየሱስ በፊት እንደ ስምዖን ወልደ-ጊዮራ ያሉ፣ በኋላም እንደ ስምዖን ወልደ-ኮኸባ ተነስተው ነበር) ይልቁንም…
-
በልጅ አንደበት ተናገረን፡ ወንጌልና አስተርዕዮ በእብራውያን መልዕክት (ክፍል-2)
«ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ…በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን» (ዕብ 1፡1:1-2) ባለፈው ክፍል፣ እግዚአብሔርን መግለጥ የሚችለው «ራሱ እግዚአብሔር ብቻ» እንደሆን ተመልክተናል። ስለዚህም ያለ አስተርዮ እግዚአብሔርን ማወቅ አንችልም። ስለ ነገረ-አስተርዕዮም (እግዚአብሔር ራሱን እንዴት እንደገለጠ) በቂ ግንዛቤ ካልያዝን ስለ እግዚአብሔር ያለን ግንዛቤ ሊዛባ ይችላል። ሁለቱ የተያያዙ ናቸው። ለምሳሌ በማርቲን ሉተር አስተሳሰብ ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበረው ነገር፦…
-
በልጅ አንደበት ተናገረን፡ ወንጌልና አስተርዕዮ በእብራውያን መልዕክት (ክፍል-1)
«ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ…በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን» (ዕብ 1፡1:1-2) “እግዚአብሔር ማን ነው?” ለሚለው ጥያቄ በቂ ያልሆነ ወይም የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖረን ከሚያደርጉን ነገሮች አንዱና ተቀዳሚው፤ ስለ ነገረ-አስተርዮ በቂ ያልሆነ ግንዛቤ መጨበጥ ነው። ለምን!? ምክኒያቱም እግዚአብሔርን ማወቅ የምንችለው «እግዚአብሔር ራሱን የገለጠልን እንደሆነ» ብቻ ስለሆነ ነው። እግዚአብሔርንም መግለጥ የሚችለው ራሱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለዚህም ያለ…
-
ነገረ-ክርስቶስ በዕብራውያን መልዕክት: መቅድም
(The Christology of Hebrews: An Introduction) የእብራውያን መጽሐፍ የሹመት መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉን ሙሉ ነገረ–መለኮታዊ ክብደት የሚሸከመው «በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ» የሚለው እውነታ ነው (ዕብ 1:3; 1:13; 8:1; 10:12-13; 12:2)። ኢየሱስ ከሁሉ እንደሚልቅ ሰባኪያችን ሲሞግት (ጸሐፊውን የምጠራው ሰባኪው በማለት ነው) የሚያቀርባቸው መሠረታዊ ማስረጃዎች በሙሉ በዚህ ልዕልና እና እውነታ ላይ የተመረኮዙ እንዲሁም የተቃኙ ናቸው። እውነታው «ተቀመጠ» (ኧካቲሰን | ἐκάθισεν)” (1:3) የሚለው ሲሆን፤…
-
ስለ አፈታት ጥቂት፡ ከምንባቡ ይዘት ጋር በቅርበት መተዋወቅ
ለአንዳንዶች ይጠቅም ስለሚችል፤ በአንድ ምንባብ ላይ ያተኮረ ትምህርት/ስብከት ሳዘጋጅ ወይም ጽሑፋዊ ሐቲት ስጽፍ፣ ጽሑፋዊ ዓውዱን ለማግኘት የምከተለው ቅደም ተከተል ከሞላጎደል በጥቂቱ እነሆኝ። መጠነኛ የቋንቋ ስልጠና ለወሰዱ ደግሞ አንዳንድ ይጠቅማሉ ብዬ ያሰብኳቸውን መርጃ መጻሕፍቶችንም እጠቁማለሁ ።ከዚህ ቀጥሎ የማሰፍረው በተከታታይ አለፍ አለፍ እያልኩ ስለ ምንባብ አተታተት የማቀርበው ይሆናል። የሚከተለው የመጀመሪያው መርህ ነው። #አንደኛ፡ ከምንባቡ ይዘት ጋር በቅርበት መተዋወቅ ወፍ በረር ትውውቅ (Big…
-
የይሁዳ መልክት – መንደርደሪያ ነጥቦች
[su_note note_color=”#f4f4f3″]► QUESTION: ሳሚየ እቺ እስቲ ኣስረዳኝ- “ከረጅም ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ወደ እናንተ ገብተዋልና፤ እነርሱ ፈሪሀ እግዚአብሔር የሌላቸው፣ የአምላካችንን ጸጋ በርኵሰት የሚለውጡና እርሱ ብቻ ልዑል ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው” ይሁዳ 4 “ምን ማለት ነዉ ከረጅም ጊዜ በፊት ለዙህ ፍርድ የተጻፉ ሲል? ጸጋ ብርኩሰት መለወጥስ? የጌታ የሱስ ጌትነት መካድ እንዴት ነዉ?” (Azeb Berhane)[/su_note]…
-
Confessing Jesus as the Son of God: In Christian and Muslim Context
This is my summary and brief response to a workshop I attended in 2013, taught by Dr. Donald A. Carson on the subject of the Sonship of Christ in Christian and Muslim context. Dr. Carson mentions three objectives. (1) It is important to try to find how one moves from exegesis to doctrinal confessions. Some systematic theologies assume the bible…
-
009-010: በፊቱ ቅዱሳንና ነውር አልባ እንሆን ዘንድ – ኤፌ. 1:4 (የኤፌሶን ምዕራፍ አንድ ጥናት)
ክፍል ሁለት፦ [የምንባርከው] የመጀመሪያ ምክኒያት ስለመረጠንና ልጆቹ እንሆን ዘንድ አስቀድሞ ስለወሰነን ነው (ኤፌሶን 1:4-6) 1.1 ቅዱሳን እንድሆን ዘንድ መርጦናልና (1፡4) [sz-ytvideo url=”https://www.youtube.com/watch?v=ONkZUWC39lg” theme=”dark” cover=”local” responsive=”y” autoplay=”n” loop=”n” fullscreen=”y” disablekeyboard=”n” disableiframe=”n” disablerelated=”n” delayed=”n” schemaorg=”n” /] እግዚአብሔርን የምንባርክበት የመጀመሪያ ምክንያት፡- አለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በእርሱ መርጦናልና[καθὼς ἐξελέξατο ἡμᾶς ἐν αὐτῷ πρὸ καταβολῆς κόσμου] ከቁጥ.4-14 ድረስ ለምን እ/ር እንደሚባረክ ምክኒያቱን ይሰጣል። ምርጫ ከብሉይ ጀምሮ…
-
009-010: የባረከን አባትና አምላክ ይባረክ – ኤፌ. 1:3 (የኤፌሶን ምዕራፍ አንድ ጥናት)
“Blessed be the God and the father of our Lord Jesus Christ…” (Eph. 1:3; Cf. 2 Co 1:3; 1 Pe 1:3). [su_note note_color=”#efeeee”][/su_note] Prayers have context. Growing up most of us heard and prayed “Our Father in heaven hallowed be your name….” Communal prayers, such as the Lord’s Prayer are designed to both teach and preserve important summary of faith…
-
009-010: የመጥራቱ ተሥፋ ምን እንደሆን ታውቁ ዘንድ (የኤፌሶን ምዕራፍ አንድ ጥናት)
ስለዚህ እኔ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ስለሚሆን በጌታ በኢየሱስ ስለ ማመንና ለቅዱሳን ሁሉ ስለሚሆን መውደድ ሰምቼ፥ ስለ እናንተ እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም፤ የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። [jwplayer player="2" playlistid="3807"] ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ…
-
009-009: በወንጌል የተቃኘ ተስፋ-ስለዚህ ተስፋ በወንጌል የእውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ
ይህ ተስፋ ይዘት ያለው ተስፋ ነው፤ የዚህም ተስፋ ይዘት ከኤጳፍራ የሰሙት ወንጌል ነው እርሱም የእውነት ቃል ነው። ወንጌል ሰዎችን ወደ እ/ር መንገሥት የሚያስገባ መሿለኪያ ብቻ አይደለም። ወንጌል የክርስትና መሰረት ነው። ይህ ወንጌል ለቆላስያስ አማኞች "የሰማችሁት፤ የተቀበላችሁት’ እንዲሁም ደግሞ ሐዋርያው የወንጌል ግዴታቸውን ይህም "ተመሰርታችሁ፤ ተደላድላችሁ..." ምክኒያቱም ወንጌል ሐያል የእ/ር ቃል ነው (1:25) የክርስቶስ ቃል ነው (3:16) ከዚህ የተነሳ ሃያልነቱን በሚያስገርሙ ሰው-መሰል…
-
009-008: በወንጌል የተቃኘ የቃል-ኪዳን ሕይወት፡ እምነት ፍቅርና ተስፋ (ፍጻሜ ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ P8)
ስለ እናንተ በምንጸልይበት ጊዜ፥ የጌታችንን የኢየሱስን አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ምክኒያቱም በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተናል[ἀκούσαντες τὴν πίστιν ὑμῶν ἐν Χριστῷ Ἰησοῦ καὶ τὴν ἀγάπην ἣν ἔχετε εἰς πάντας τοὺς ἁγίους]ሐዋርያው ወደ ምሥጋናና ወደ ልመና ጸሎት ያነሳሳው ስለ ቆላስያስ ሰዎች የሰማው ነገር ነው፦ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነት፦ ይህ የቆላስያስ ሰዎች በክርስቶስና በወንጌሉ ላይ ያለ እምነታቸውን ያሳያል፤…
-
009-006: ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምጽ የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል! አሁንም መጥቷል! (ፍጻሜ ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ P6)
[su_youtube url=”https://www.youtube.com/watch?v=Kk87X5mQfhc”] Our Christian hope entails Resurrection Existence Resurrected bodies New heaven and new earth, our home of righteousness (Rev. 21-22) Sabbath rest (Heb. 3-4) Perfected vision and fellowship The above blessings however have begun here on this evil age, while we are in it. Therefore at present we posses eternal life, resurrection power, sabbath rest and a realized vision…