Home / Portfolio / Articles / -6- ማዕከላዊ ወንጌል ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ነው!

-6- ማዕከላዊ ወንጌል ክርስቶስን ማዕከል ያደረገ ነው!

Posted on

(This is the last post on this series. If you would like to read the whole article in English, click here AcrobatPDF The Story of the Gospel)

(3) ክርስቶስ የወንጌል ማዕከል ነው!

“ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተተቀበረ፣ በቅዱሳን መጽሐፍት እንደ ተጻፈዉም በሦስተኛው ቀን ተነሳ፣ ከዚያም ለኬፋ ታየ፣ ቀጥሎም ለአስራ ሁለቱ ታየ፣…” 1 ቆሮ 15፤ 4-5

እስከ አሁን ድረስ የተመለከትነው ወንጌል ማዕከላዊ እንደሆነ ነው። አሁን ደግሞ፣ ይህ ማዕከላዊ የሆነው ወንጌል ራሱ ማዕከል ያደረገው ክርስቶስ ላይ መሆኑን እናያለን። ይህንን እንደ አውሎ-ነፋስ (or Hurricanes) አይን ምሳሌ አድርገን ብናይ ግልጽ ይሆንልናል። ክርስቶስ የወንጌል ማዕከል ካልሆነ ወንጌል ጨርሶ ወንጌል አይደለም። ጳውሎስ ይህንን ብዙ አገባብ ባላቸው ቃላት አጠቃሎታል። እነዚህም ቃላት: ሞተ ፣ተቀበረ ፣ ተነሳ እና ታየ የሚሉ ናቸው። Thecenterofallየእነዚህ ግሦች ባለቤት (Subject) ወልድ ነው። እርሱም ሥጋ ለብሶ ኢየሱስ የሚባል ስም የተሰጠውና የእስራኤል ተስፋ ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ከዳዊት ቤት ዘር ‘ክርስቶስ” ሆኖ የተሾመ ነው። ስለዚህ “ክርስቶስ ሞተ ፣ ክርስቶስ ተቀበረ ፣ ክርስቶስ ተነሳ እና ክርስቶስ ታየ ” ስለዚህ ወንጌል ስለሞተው ፣ ስለተቀበረውና በሶስተኛው ቀን ስለተነሳው፤ ስለ እግዚአብሔር ልጅ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የወንጌልን አስኳል ክርስቶስ አለማድረግ፤ በታሪክ የሚከተሉትን እንቅስቃሴዎች እንዲነሱ አድርጓል። በሰዎች ማሕበራዊ ቀውስ ላይ ያተኮረ ወንጌል (the social gospel), በሰው ልጅ ሰብዓዊ መብት ላይያተኮረ ወንጌል (the black liberation gospel)፤ በኢኮኖሚ ብልጽግና ያተኮረ ወንጌል(the prosperity gospel); በሥነ-ልቡናዊ ፍላጎት ያተኮረ ወንጌል (human-centered)። እነዚህ የወንጌልን ትኩረት ዝቅ ከማድረጉም በላይ ሁኔታውን ገልብጦ ተቃራኒ ትርጉም እንዲኖረው ሊያደርግ ይችላል። በመጀመሪያ በቀዳሚነት ወንጌል ስለ እኛ አይደለም (በቀዳሚነት በሚለው ቃል ላይ አንባቢዬ እንዲያተኩር እሻለሁ)፤ ወንጌል ስለ እኛ ሥነልቡናዊ ፍላጎት፣ ማህበራዊ ፍትህ፣ የጤናና የንብረት ብልጽግና አይደለም። ጳውሎስ በአንድ-ወጥ ሐረግ (በአስራ ሰባት ጥቅሶች) ውስጥ ሶስት ጊዜ በመደጋገም ወንጌል ስለእኛ አለመሆኑን በጥንቃቄ አሳይቶናል፤ “ይሄውም፣ በሚወደው በእርሱ በኩል በነጻ የተሰጠን ክቡር የሆነው ጸጋው እንዲመሰገን ነው” (ኤፌ. 1 ፥6፣12፣14) ። ስለዚህ የወንጌል ማዕከል ሰው ሳይሆን የእግዚአብሔር ክብር ነው! የወንጌል ማዕከሉ የሰው ልጆች ፍላጎት አይደለም። ፈጽሞ እኔና እናንተ አይደለንም። ወንጌል አነጣጥሮ ፍንትው አድርጎ የሚያበራው በክርስቶስ ፊት ላይ ነው። ስለዚህ ነው ሐዋርያው “የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ….በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ [ግን] በልባችን ውስጥ የበራ፤ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና” 2ቆሮ 4:4 “ብርሃን ይሁን” የሚለው የእግዚአብሔር ቃል በወንጌል አማካይነት ሲታወጅ፤ ፍንትው የሚያደረገው የክርስቶስን ፊት ነው። እርሱም የእግዚአብሔር አምሳል የሆነው የእግዚአብሔር ክብር ነው! ስሙ ለዘለዓለም ይባረክ! ስለዚህ ነው ወንጌል “ስለ ክርስቶስ የሆነው!” ሲቀጥልም “ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።” 2ቆሮ 4:5 ይህንን ሰፋ አድርገን ከሮሜ 1:1-4 እንመልከት።

ወንጌል እግዚአብሔር አብ ነው! ወንጌል ስለ ልጁ ነው!

ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

አንዳንድ ጊዜ መስተዋድዶች (prepositions፣ ለ፤ ከ፤ ስለ፤ በ፤…) ብዙ ክብደት ያላቸው አይመስሉንም። በተለይ ከአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች በይበልጥ መስተዋድዶችን በመጠቀም ትልቅ አስተምሕሮት ሲስጥ የምናየው ሐዋርያው ጳውሎስ ነው። (ሌሎችም ጸሐፊዎች ለምሳሌ ስለ ሥነ-ፍጥረት ሲናገሩ ሁሉም በአንድነት እግዚአብሔር በልጁ በኩል እንደፈጠረ ሲያሳዩ፡ “በኩል – through– የሚለውን መስተዋድድ ለወልድ ሲጠቀሙ “በ” የሚለውን መስተዋድድ ግን ለአብ ይጠቀማሉ። ይህ ለምሳሌ ወልድ በአብ በኩል እንደፈጠረ መስተዋድዱ ቢገላበጥ የአዲስ ኪዳን አስትምህሮት ይፋለሳል። – ዮሐ 1:1-4፤ ዕብ 1:1-4፤ ቆላ 1:15-20፤ 1ቆሮ 8:6) ጳውሎስ እንደልማዱ ታዲያ ወንጌልን ከአብ አንጻር “” የሚለውን መስተዋድድ በመጠቀም የወንጌል ነዳፊና ምንጭ (architect) እንደሆን ሲያሳየን በተመሳሳይ ደግሞ ወንጌል ከወልድ አንጻር “ስለ” የሚባለውን መስተዋድድ በመጠቀም የወንጌል ማዕከል እንደሆን ይነግረናል። ወንጌል ጉዳዩን ስለ ክርስቶስ ያደረገ ዜና ነው። ይህም የመንግሥቱ የድል ምሥራች ሰበር-ዜና ነው።

ሮሜ 1:1-4 ሶስት የሀሳብ ፍሰቶች አሉት። ወንጌል የማን እንደሆነ፤ ወንጌል ስለማን እንደሆነ፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ የወንጌልን ይዘት ደግሞ ምን እንደሆነ ይነግረናል; ይህም ቀድሞ ተስፋ ሆኖ ቆይቶ እንደነበርና አሁን ግን ወንጌል አማካይነት በሥጋ የዳዊት ልጅ ሆኖ ስለተወለደው ደግሞም በቅድስና መንፈስ ከሙታን በመነሳቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በሐይል ስለተገለጠው” ስለ እግዚአብሄር ልጅ፤ ስለ ጌታችን፤ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

  1. ወንጌል የእግዚአብሔር አብ ነው
  2. ወንጌል ስለ ልጁ ነው
  3. ወንጌል ይዘት አለው፡
    1. አስቀድሞ በነብያቱ አፍ በቅዱሳት መጻሕፍት ተስፋ ነበር (ተሥፋው)
    2. አሁን ግን ልጁ በሥጋ ከዳዊት ዘር ሆኖ መወለዱ (ስጋዌነቱ)
    3. በቅድስና መንፈስ ደግሞ ከሙታን በመነሳቱ በልዩ መንገድ ‘የእግዚአብሔር ልጅ’ መሆኑ መረጋገጡ (ትንሳኤውና እርገቱ)

ስለዚህ፣ ወንጌልን ስንረዳውና ስናውጀው በተቀዳሚነት ከሁኔታዎቻችን ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት ወይንም በሰዎች ላይ ያነጣጠረ ማስመሰል የለብንም።ይህም romance_1ማለት”በኑሮህ ውስጥ ዓላማ እንዲኖርህ ትፈልጋለ?”ከዚህ ሁኔታ ውስጥ መውጣትና የተሻለ ሕይወት መምራት ትፈልጋለህ?” “የዝቅተኝነት ስሜትህ እንዲወገድልህ ትፈልጋለህ?” “ፈውስ ትፈልጋለህ?” “መንግሥተ ሰማያት መግባት ትፈልጋለህ?……”ወንጌል ያበለጽጋል” ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎችንና ለመመለስ መሆን የለበትም። እነዚህን ሁሉ የማይፈልግ ማን አለ? ሰው እነዚህን ሁሉ ይፈልጋል ነገር ግን ክርስቶስን አይፈልግም። ይህን ሁሉ ማትረፍ ይፈልጋል ነገር ግን ክርስቶስ እግር ሥር ተደፍቶ “ጌታዬ አምላኬ” በማለት በሥልጣኑ ዘንግ ሥር መገዛት አይፈልግም። ወንጌል የሚያቀርበው የሰውን ፍላጎትማ ቢሆን ኖሮ መስቀል መሰናክል መሆኑ በቀረ ነበር! ወንጌል ግን የሚሰጠን ክርስቶስን ነው። እንዲያውም “የተሰቀለ ክርስቶስ/ንጉስ – a crucified Messiah! ይህ ለአይሁድ መሰናክል ለግሪኮች ደግሞ ሞኝነት ነው። አብሮ የማይሔዱ እውነታዎች ናቸውና። ንጉሥ ይነግሳል እንጂ እንደ ወንጀለኛና እንደ ደካማ ባሪያ አይሰቀልም። ወንጌል ግን ሐይልንና ድካምን፤ ክብርንና ውርደትን፤ ዙፋንና መስቀልን፤ አንድ ያደርጋል። በወንጌል አማካይነት ክርስቶስን በመስቀል ድካም የተመረቀ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አናየዋለን! ወንጌል ጣቱን ቀስሮ የሚያመለክተን ስለ አባቱ ፈቅድ ሲል የሰው ልጆችን ሐጥያት ያስተሰርይ ዘንድ ከመላእክት አንሶ የነበረውን ነገር ግን አባቱ ከሙታን አስነስቶ ባረጋገጠለትና ጌታም ክርስቶስም እንዲሆን በሾመው በአንድያ ልጁ ላይ ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው ተግዳሮት መቀበል ሳይሆን ‘መንበርከክ ነው!” ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰው ቃል “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” ሲጠቀስ ሰዎች ከክርስቶስ የሚያገኙትን በረከቶች ጎላ አድርጎ በማሳየት የሰዎችን ልብ ለመማረክ ነው። ትኩረቱ ግን በመጀመሪያ “ወደ እኔ ኑ!” ላይ ነው። ከዚያ ነው “እኔም….” የሚለው በረከቶች የቀረቡት።

ስለዚህ ወንጌል ስለ ክርስቶስ ነው! እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ጥቂቶቹ ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ፣ ወንጌል ያስገኛቸው ጥቅሞች/ ፍሬዎች ናቸው ማለት ይቻላል፤ ነገር ግን አንዳቸውም ወንጌል አይደሉም። ኢየሱስ በኑሮ ውስጥ እንዴት ዓላማ ሊኖረን እንደሚችል ሊያሳየን አልመጣም፤ በእርግጥ እርሱን ከአገኘን በኋላ ለምን መኖር እንደሚገባን ያሳየናል፣ ይሁንና ይህም ቢሆን ወንጌል አይደለም። ወንጌል እኛን ከእግዚአብሔር ጋር ማስታረቅ ብቻ ሳይሆን እርስ በርሳችንም ሊኖረን ስለሚገባው እርቅ (በክርስቶስ አዲስን ሰው በመፍጠር አንድ አድርጎ ያስታረቀ ማለትም በሰውነቱ በቤተክርስቲያን አማካይነት) ይናገራል። ቢሆንም ዋና አላማው እንደ ድህነት፣በሽታ፣ እኩልነት፣ በመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ፍትህን መስጠት አይደልም (ኤፌ. 2፥11-14) ። እንዚህ የወንጌል ፍሬዎች ናቸው። ከላይ የተዘረዘሩትን የሰው ልጆችን ቀውስ ወንጌል ይፈታል። ነገር ግን ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ይህ ነው። ወንጌል እነዚህን የሰው ልጆችን ቀውሶች የሚፈታው (እርቅ ከእግዚአብሔር ጋር፤ እርቅ እርስ-ከእርስ ጋር፤ እርቅ ከፍጥረት ጋር – በዚሁ ቅደም ተከተል)፤ የዳዊትም የእግዚአብሔርም ልጅ የሆነውን ኢየሱስን ማዕከል በማድረግ ነው። ኢየሱስን ካገኘነው በኋላ ግን በእርሱና በደሙ ያለን እምነት ወደ ነፍሳችን እረኛ ይመልሰናል። (በትምህርታችን እንደተመለከትነው፤ ይህም እረፍት በሁለት ዘመናት ተከፍሏል። አሁን በዚህ በዘመን መጨረሻ መንፈሳዊ እረፍትን አግኝተናል ነገርግን አንድ ቀን ዳግም በመምጣቱ ወደ አዲሲቱ ሰማይና ምድር ወደ ተስፋይቱ ምድር በመግባት ፍጹም እረፍት እንገባለን!) ።

ወንጌል አብ ለወልድ፤ ወልድ ደግሞ ለአብ ያለውን ፍቅር ይገልጣል

በመጀመሪያ ልናስተውል የሚገባው በኤደን ገነት በሰይጣን አነሳሽነት የተፈጸመው የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ነው። በኤደን ገነት መካከል የተተከለችው ዛፍ ለአዳምና ለሔዋን የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ centeroftheUniverseሥልጣኑን ማዕከል ያደረገች ምሳሌ ነበረች። ከውድቀት በፊት ለሰው እግዚአብሔር ማዕከላዊ ነበር። ሐሳቡ የተቃኘው በአምላኩ ነበር። ከዚያም የተነሳ እርስ በርስ ትክክለኛ ግንኙነት ነበራቸው (ሁለቱም አይተፋፈሩም ነበር)። ሆኖም ግን ሐጥያት (አመጽ) መርገምን አመጣ። የሰው ልጅ ማዕከል እኔነቱ (self)ና የገዛ ፍላጎቱ(desire) ሆነ (ኤፌ 4፡ 17-23፤ ሮሜ 1:21፤ 1 ጴጥ. 1:18፤ ቆላ. 2:18፤ 2 ጴጥ. 2:18)። ከዚህ ፍርድ ሰዎችን ነጻ ለማውጣትና የእግዚአብሔርን ሥልጣን በሰማይና በምድር ማዕከላዊ አድርጎ ለመመለስ ወንጌል የሰውን ልጆች እይታ ሥልጣንን ሁሉ ተጎናጽፎ መንግሥት ሆኖ ወደ ተገለጠው ወደ እግዚአብሔር ልጅ ይመልሳል። ስለዚህ ወንጌል በአመጽ ሥር የወደቀውን የሰውን ዘር ማዕከሉን ወደ ቀድሞ ቦታው የሚመልስ (restore የሚያደርግ) ነው ማለት ይቻላል። ወንጌል ማዕከል የሚያደርገው ክርስቶስን እንጂ እኔንና እናንተን አይደለም። የወንጌል ትኩረት ተገላብጦ መልዕክቱ ‘ኢየሱስ እኔን እኔ ሊያደርግ መጣ” ይሆንብናል። (If we turn the Gospel around to mean that Jesus came to make ME, ME is idolatory). ልክ ሙሴ፣ አብርሃም፣ ዳዊት …አብን እንዳከበሩት ሁሉ ወልድን እንዲያከብሩት አብ ወስኗል ። ወንጌለ ኢየሱስን ማዕከል ያደርገውም ለዚህ ነው። የወንጌል ዓላማ የእግዚአብሔርን ልጅ ክብር መግለጥ ነው። ስለዚህ፣ በወንጌል የተገለጠው ፍቅር በሱሉስ እግዚአብሔር ማካከል ያለው የፍቅር ልውውጥ ነው።

“ አብ ወልድን ስለሚወድ የሚያደርገውን ሁሉ ያሳየዋል፤ ትደነቁም ዘንድ ከእነዚህም የሚበልጥ ነገር ያሳየዋል። “ “ ምክንያቱም አብ ሙታንን እንደሚያስነሳ፣ ሕይወትንም እንደሚሰጥ፣ ወልድም ደግሞ ለሚፈቅደው ሁሉ ሕይወትን ይሰጣል።” “ አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ አሳልፎ ሰጥቶታል ፤” “ ይሄውም፣ ሁሉ አብን እንደሚያክብሩ ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ ወልድን የማያከብር፣ የላከውን አብንም አያከብርም።“ “ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም” (ዮሐ. 5፥20-24)።

የአብ ውሳኔ የራሱን ዕቅድና ሥራ ለልጁ በመስጠት ለልጁ ያለውን ፍቅር ለማሳወቅ ነው። ይህም የሚሆነው “ሁሉ አብን እንደሚያክብሩ ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው። በተመሳሳይ መልኩ ፣ የወልድ ዓላማ ደግሞ አባቱ የሰጠውን ሥራ በመፈጸም ለአባቱ ያለውን ፍቅር ማሳወቅ ነው። ይንንም በትክክል የፈጸመው እራሱን ባዶ አድርጎ የባሪያን መልክ በመያዝና ትሑት በመሆን በመስቀል ላይ እስከመሞት ድረስ በመታዘዝ ነው። ኢየሱስ ቀጥሎ ያለውን የጸለየውም ለዚሁ ነው፤

“የሰጠህኝን ሥራ በመፈጸም በምድር አከከበርሁህ ። እንግዲህ አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር ከአንተ ጋር በነበረኝ ክብር በአንተ ዘንድ አክብረኝ” (ዮሐ. 17፥4-5)

የዚህ መታዘዝ ዓላማ አባቱ ከሰጠው አንድም እንኳን እንዳይጠፋ ነው ፤

“ መልሼ ለማንሳት ሕይወቴን አሳልፌ ስልምሰጥ አባቴ ይወደኛል። ሕይወቴን በራሴ ፈቃድ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም፤ አሳልፌ ለመስጠትም ሆነ ለማንሳት ስልጣን አለኝ፤ ይህን ትእዛዝ የተቀበልኩትም ከአባቴ ነው።”

የስሉስ አምላክ ፍቅር መገለጫ መሳሪያዎች!

ኢየሱስ ሊያድነን የመጣበት ዋንኛው ዓላማ ትኩረታችንን ራሳችንን ከማምለክ (from self-idolatry) ወደ አባቱ ክብር ለማምጣት ነው። አባት፣ የእርሱ [የእግዚአብሄር] ወንጌል፣ ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረውን የድነትና የፍርድ ዕቅድ በሕልወቱና በሥራው ስለፈጸመው ፣ ስለልጁ እንደሆነ አውጇል። እኛ ደግሞ ክፉዎች የነበርነው የዚህ ፍቅር መግለጫ እቃዎች ሆነን እራሳችንን አግኝተንዋል። አብ ወልድን ይወደዋል ፣ ወልድም አብን ይወደዋል፤ እኛ ደግሞ የዚህ የአብና የወልድ ፍቅር ልውውጥ የሚካሄድበት መሳሪያዎች ሆነናል። “ኦ ይህ ታላቅ ክብር ነው!” ለዚህም ነው በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውና በጉ ፊት በፊታችን ተደፍተን የምናመልከው። እኔና እናንተ ከልጁ ሥራ የተነሳ በሥራው ማዕከል ቆመን ራሳችንን እናገኘዋለን።

“ከዚያም በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን፣ በሽማግሌዎቹም መካከል የታረደ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ ፤ በጉም ሰባት ቀንዶችና ሰባት አይኖች ነበሩት፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ የተላኩት ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው። እርሱም መጥቶ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ መጽሐፉን ወሰደ” ( ራእይ 5፥6-7)።

ወንጌል ሁልጊዜ በተፈጸመ ድርጊት (in past tense) ይገለጻል። ወንጌል እግዚአብሔር በተለይ (exclusively) በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የሠራው ሲሆን ድርጊቱም የልጁ ሞትና ትንሣዔ ላይ ያነጣጠረ ነው። ስለዚህ በመጀመሪያ በተነሳሁበት ነጥብ አጠቃልላለሁ።

____________________________________________

የወንጌል አውድ (the context of the gospel):

ወንጌል የእግዚአብሔር ነው ( የወንጌል ባለቤት እግዚአብሔር ነው)፤ እግዚአብሔር አብ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲፈጽመው የሰጠው ሥራ የወንጌል አውድ ሲሆን ይህም አውድ አብርሃም፣ ሙሴ ፣ ዳዊትና ሁሉም ነቢያት በታማኝነት ያገለገሉት ነው (ዕብ.3፥1-6)። ለዚህም ነው ወንጌላውያኑ (ማለትም ፤ ማቴዎስ ፣ ማርቆስ ፣ ሉቃስና ዮሐንስ ፤ ) የብሉይ ኪዳንን አውድ ይወክል ዘንድ የመጥምቁ ዮሐንስን መንገድ ጠራጊነት በጥንቃቄ በወንጌል ውሥጥ ያካተቱት (ማቴ. 11፥13)

____________________________________________

ወንጌል (The gospel itself):

ወንጌል ስለ እየሱስ ክርስቶስ ነው ፤

እየሱስ ክርስቶስ ስራውን ብቻውን ፈጸመ ፤ በመፈጸሙም የእግዚአብሔርን ዓላማ በሙሉ ወደ ብርሃን አወጣው (ገለጠው)፤

ይህም ወንጌል ነው (ራዕ. 5፥1-6)

__________________________________________

የወንጌል ፍሬ ( The fruit of the Gospel):

ወንጌል በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መስፋፋት ጀመረ፤

የዚህ [ በክርስቶስ] የተፈጸመው የድነት ሥራ ውጤት፤ ስለ ስሙ ንስሐ መግባት፥ እምነት፣ እርቅ ፣ ቅድስና ፣ክብር ፣(glosification) ፣ የመንፈስ [ቅዱስ ] መውረድ ፣ የክርስቲያን ሥነ ምግባር ፣የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ዓላማ መረዳት መቻል…የአዲስ ሰማይና የቅዱሳን ቤት የሆነችው አዲስ ምድር ከላይ መምጣት፤ እነዚህ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ የተገኙ የወንጌል ፍሬዎች ናቸው ።

© 2013 – 2014, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like 1 People Liked this
avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top