Home / Media Posts / Audio Posts / 08_04_የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግሥቱ መገለጥ (Audio)

08_04_የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግሥቱ መገለጥ (Audio)

Posted on

በኪዳኑ መንግሥት መገለጥና በፍጻሜው መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ


ምንም እንኳ የእግዚአብሔር መንግሥት በልጁ በክርስቶስ መምጣት ብትገለጥም ነገር ግን ፍጻሜው ገና አልመጣም! ይህም የእግዚአብሔርን ሐሳብ በሁለት ዘመናት እንዲከፈል አድርጎታል! አዲስ ኪዳን ስለ እግዚአብሔር ኪዳናዊ መንግሥት ሲናገር በሁለት መልኩ ያስቀምጠዋል።

ማቴዎስ 5:3 (AMHB)  በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፥ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።

ማቴዎስ 6:9–10 (AMHB)  እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ 10 ስምህ ይቀደስ; መንግሥትህ ትምጣ; ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን;

መንግሥቱ መጥታለች ደግሞም ትመጣለች

የሁለቱ ልዩነት የተመሰረተው በንጉሱ/ በክርስቶስ ነው። ይህም በምድር ክርስቶስ ሲመላለስ መንግሥቱ ቀርባለች; ነገርግን ክርስቶስ ወደ አባቱ ከተመለሰ በኋላ ግን ዳግም እስኪመጣ ድረስ መንግሥቱን እንጠባበቃለን። ሁለቱም በአሁኑ ዘመን እውነት ነው። ሁኖም ግን ክርስቶስ ከምድር ሳይሆን ከአባቱ ቀኝ ሆኖ ንግሥናውን ይገልጣል። ይህ በአዲስ ኪዳን ጳውሎስ በኤፌሶን “ሰማያዊው ሥፍራ” የሚለው ነው። ነገር ግን በምድር ላይ ኪዳናዊ መንግሥቱ “እንደ እኔ ያለ ሌላ አጽናኝ” ተብሎ ተስፋ በተሰጠው በመንፈስ ቅዱስ በበዓለ ሃምሳ መምጣት አሁን ክርስቶስ መንግስቱን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ይገልጣል።

ይህንን ልዩነት ነብያት ያላዩት ሚስጥር ነበር! ዮሐንስን ጨምሮ። ምክኒያቱም ኢየሱስ ሲያደርግ የሰማው የማዳንን ሥራ ብቻ ሲሰራ እንጂ ክርስቶስ ሲገለጥ ይሰራዋል ተብሎ የሚጠበቀውን የፍርድን ሥራ አልገለጠም። ኢየሱስ ክርስቶስ ከሆነ ለምን የብረትን በትሩ ዮሐንስን እስር በከተቱት በሮማውያን ገዢዎች ላይ አይገለጥም? ይህ ጥያቄ ነበር መልዕክተኞችን እንዲልክ ግድ ያስባለው፡

ማቴዎስ 11:2–6 ዮሐንስም በወህኒ ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና። 3 የሚመጣው አንተ ነህን? ወይስ ሌላ እንጠብቅ? አለው። 4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። ሄዳችሁ ያያችሁትን የሰማችሁትንም ለዮሐንስ አውሩለት; 5 ዕውሮች ያያሉ አንካሶችም ይሄዳሉ፥ ለምጻሞችም ይነጻሉ ደንቆሮችም ይሰማሉ፥ ሙታንም ይነሣሉ 6 ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል; በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።

የሚመጣው የመሲሑ መንግሥት

ስለዚህ እግዚአብሔር ነግሥናው ፍጹም ንግሥና ሲሆን አንድ ቀን ደግሞ ኪዳናዊ ጌትነነቱ/ንግሥናው በምድር ሁሉ ላይ ይገለጣል! ብሉይ ኪዳን ስለዚህ መንግሥት ሲመሰክር፡


 1. መሲሐዊ መንግሥት
  1. የዳዊት ልጅ/ ንጉስ (ቁጥቋጥ/የእሴይ ግንድ) 69; 2 Sam. 7:11–13, 16; Ps. 89:4; 132:11; Isa 4:2; 9:6, 7; 11፡ 1-2; 16:5; Acts 2:30; 13፡ 23 [Rev. 3:7]; Jeremiah 23:5-8; Ge 18:19; Ezekiel 17:22-24; Jer 30:9; Isa. 32:1; Ezek. 37:24; Hos. 3:5; Zech. 9:9; Matt. 2:2; Luke 1:32; 19:38; John 1:49; Je 33:15; Zech 3: 8; 6: 12
  2. እረኛ Eze 34: 23; 37:22, 24; Jer. 23:4, 5; Mic 5:4; 7:14; john 10:11, 16; zech 3:8)
  3. የሰው-ልጅ (dan 7፡9-10; 13-14; ps 8:6; Matt. 26:64; Heb 2፡6-10 Rev. 1:7; 14:14)
  4. ጌታ ps 110:1-2; Isa. 9:6, 7; Rev. 11:15)
  5. የጌታ ባርያ (isa 42: 1-4; 49: 1-6; 50: 4-9; 52:13-53:12)
  6. የተቀባ/ ክርስቶስ፡ በመንፈስ ቅዱስ ተቀብቶ ንጉስ ይሆናል! መንፈስ ያርፍበታል (Lk 4:18; Ac 10:38; Heb 1:9

 2. መሲሐዊ ዘመን (ኢሳ 11)
  1. አዲስ ዘጸዓት ይገለጣል። እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብጽ እንዳወጣ ለሁለተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ህዝቡን ይሰበስባል (Isa 11፡ 11-16)
  2. ንግሥናውና አለቅነቱ በምድር ሁሉ ላይ ይሆናል (Dan. 2:44; 7:14, 18, 27; Zechariah 9:9-10; Psalm 72:8-11 ;Heb. 1:8; Rev. 11:15)
  3. የእግዚአብሔር መገኘት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መመለስና የቤተ/ መቅደሱ እንደገና በክብር ይሞላል! (Isa 2፡1-4)
  4. እግዚአብሔር አዲስ ኪዳን እንደገና ከሕዝቡ ጋር ይገባል; አዲስ ዘጸዓት; አዲስ ኪዳን; አዲስ መንፈስ (Jer 31:21-34; Ezek. 37:26)
  5. የእግዚአብሔር መንግሥት በሃይል ትገለጣለች
  6. ዓለም አቀፍ ትድግ ይገለጣል
  7. ፍጥረት ሁሉ ከሐጥያት; ከሞትና ከአመጽ እጅ ነጻ ሆኖ አዲስ ይሆናል (Isa 65-66; Rev 21-22)
  8. ወ.ዘ.ተ…

© 2013 – 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like 1 People Liked this
avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top