Home / Media Posts / Audio Posts / 08_03_የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግሥቱ መገለጥ (በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ጌትነትና በዘመናችን በሪፐብሊክ አገዛዝ መካከል ያለው ልዩነት) (Audio)

08_03_የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግሥቱ መገለጥ (በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ጌትነትና በዘመናችን በሪፐብሊክ አገዛዝ መካከል ያለው ልዩነት) (Audio)

Posted on

 

ሙሉውን የማጥኛ ጽሑፍ: የዚህን ጥናት ማብራሪያ ጹሑፍ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ Kingdom and Sovereignty

በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ጌትነትና በዘመናችን በሪፐብሊክ አገዛዝ መካከል ያለውን ልዩነት

መግቢያ

እግዚአብሔር የዲሞክራሲ አመራር የለውም። በብዙሀኑ ሐሳብ አያምንም። አሁን ባለንበት ዓለም ሕዝብ የመረጣቸውና የሕዝቡን ፈቃድ ለማገልገል የተሾሙ መሪዎች አሉ። በብዙሁኑ ፈቃድ ላይ የተመሰረት የመንግሥት መተዳደሪ ሕግ “ሕገ-መንግሥት” ይጻፍና በዚያ መንግሥት ሕዝቡን ያስተዳድራል። ይህ አይነት የመንግሥት አሰራር ፍልስፍና የመንጨው ከክርስቶስ ልደት ከ500 ዓመታት በፊት ሲሆን የቃሉ ምንጭ δημοκρατία (dēmokratía) “የሕዝብ አመራር” ማለት ሲሆን ከሁለት ጥምር ቃላቶች የወጣ ነው። ይህም δμος (dêmos) “ሕዝብ” ማለት ሲሆን κράτος (kratos) “ሐይል/ ሥልጣን/ አመራር ማለት ነው። የጥንታዌው አለም ነገስታት ይህ ለንግስናቸው እንደመሳለቂያ ነው።ምክኒያቱም ነገስታት ይገዛሉ እንጂ አይመከሩም። ነገስታት ሕግ ያወጣሉ እንጂ ሕግ በነሱ ላይ አይሰራም። ንጉሱ ራሱ ሕግ በመሆኑ ንጉሱ የተናገረው ነገር ሕግ ሆኖ የታወጃል። መንግስታቸውም መለዮ ዘውዳዊ “ሞናርኪዝም” ነው; ሕጋቸውም ፍትሐ ነገሥት ሆኖ ይጻፋል።

አሁን ባለንበት ዓለም ያሉ ነገስታቶች ግን የመጽሀፍ ቅዱስን ንግሥና ባለማንጸባረቁ ይህንን ልዩነት ማምጣት ተገቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። የአሁኑ አይነት ንግሥና የመነጨው በተለይ በአሜሪካና በፈረንሳይ ከተንሳው የአብዮት እንቅስቃሴ ነው። ነገሥታት እጅጉን መረን ከመልቀቅ አልፈው ሕዝብን በመጨቆን በፍጹም ጭከና ሲመሩ የተነሳ አብዮት ነው።፡ይህ የነጻነት-ትግል አሁን በአሜሪካ ያለውን አይነት ዲሞክራሲ እንዲሰራፋ አድርጓል። በአለም የቀሩትም ጥቂት ነግሥታት መንግሥታቸው “ሕገ-መንግሥታዊ ንግስና “Constitutional monarchs” በመባል ይታወቃል። ምክኒያቱም ሥልጣናቸውን ለመለማመድ ሕዝብ ባጸደቀው ሕገ-መንግሥት ሥር ብቻ ስለሚተዳደሩ ነው። አሁን በእንግሊዝ አገር ያለችው ንግስት “ኤልሳቤት” ከምልክትነት በስተቀር ብዙ ስልጣን የላትም። ምክኒያቱም ሥልጣኗ በእንግሊዝ ሕገ መንግሥት ሥር ስለሆነ ነው።

ይህ ዳራ/ context ከመጽሀፍ ቅዱሱ ንግሥና የተለየ ነው። እግዚአብሔር ሉዓላዊ ንጉስ ነው። ሥልጣኑ ፍጹም በመሆኑ ይግባኝ የሌለው የሥልጣን ጣራ ነው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ንግሥና ምን ይመስላል? ለምሳሌ አድርገን ኢሳ 33፡22ን እንመልከት፡

22 እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፥

እግዚአብሔር ሕግን ሰጪያችን ነው፥

እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው;

እርሱ ያድነናል።

ይህ አሁንም የዕብራይስጥ ግጥም ነው። ፈራጃችን; ሕግን ሰጪያችንና ንጉሣችን ተመሳሳይ ናቸው። ኢሳያስ ይህን የተናገረው የእግዚአብሔር ምጡቅ-ልዕልናው በሰማያት እንደተዘረጋ ወደፊት ዙፋኑን በሙላት በጽዮን እንደሚያመጣ ሲናገር “5እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጦአልና ከፍ ከፍ አለ; ጽዮንን በፍርድና በጽድቅ ሞላት።” እግዚአብሔር ፈጥኖ ስለሚገልጠው ማዳንና ስለሚያመጣውም ዓለም-ዓቀፍ ደህነት “10 አሁን እነሣለሁ ይላል እግዚአብሔር; አሁን እከበራለሁ; አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ” ውጤቱም “17ዓይኖችህ ንጉሥን በውበቱ ያዩታል; እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ያዩአታል” ራሱ እግዚአብሔር በሙላት ወርዶ ዓለምን ይገዛል! ይህም ፍጹም አገዛዝ በነዚህ ሦስት ቃላቶች ተገልጿል; ፈራጅ; ሕግ ሰጪ; ንጉሥ The three branches of government ቅድም እንደተመለከትነው በዘመናችን እነዚህ ሦስቱም በአንድ ሰው ጫንቃ ላይ አይገኙም። ቢገኙ እነዚህን አምባገነን መሪዎች / dictators/ እንላቸዋለን። ለዚህ ነቀፌታ በቂ ምክኒያት አለን። ሰዎች በጽድቅ መግዛት ስላማይችሉ ነው። ለምሳሌ በአሜሪካን ኮንስቲቲውሽን መሰረት የሥልጣን ክፍፍል ( balance of power) አለ። The executive branch, the judiciary branch and the legislative branch.

እግዚአብሔር አምላካችን ግን ንጉሳችን (መሪ; ገዢ; ጌታችን); ሕግ ሰጪ እና ዳኛችን ነው። በአጭር ቃል አምላካችን ፍጹም ንጉስ ነው!

አምላካችን ፍጹም ንጉስ ነው!

የመዝሙር መጽሀፍ በአንድ ላይ ጠርዞ ያቀናበረው ሰው ስለዚህ ንግሥና ባህሪይ ተረድተው የእሥራኤል ዘማሪዎች የዘመሩትን መዝሙሮች ከPs 93 – Ps 100 በአንድላይ አስቀምጧቸዋል። ለምሳሌ ያህል፡

Psalm 93:1–2 (AMHB) ንግሥናውን ያጎላል በተለይ ምጡቅ-ንግሥናውን (ፈጣሪነቱ)

1 እግዚአብሔር ነገሠ፥ ክብርንም ለበሰ; እግዚአብሔር ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም; ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት። 2 ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም ከዘላለም ነህ።

Psalm 94:1–2 (AMHB) ዳኛነቱን ያጎላል

1 እግዚአብሔር የበቀል አምላክ ነው። የበቀል አምላክ ተገለጠ። 2 የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ከፍ ከፍ በል; ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።

Psalm 95:3–5 (AMHB) ንግሥናው ወሰን-መጠቅ መሆኑንና ሰዎች ለኪዳን ጌትነቱ በመገዛት ወደ እረፍቱ እንዲገቡ ያዛል

3 እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ ነውና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና። 4 እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥላቸውም; የምድር ዳርቻዎችም በእጁ ውስጥ ናቸው፥ የተራሮች ከፍታዎች የእርሱ ናቸው። 5 ባሕር የእርሱ ናት እርሱም አደረጋት፥ የብስንም እጆቹ ሠሩአት። 6 ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ; በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንበርከክ; 7 እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና። 8 በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑት እንዳስቈጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ። 9 የተፈታተኑኝ
አባቶቻችሁ ፈተኑኝ ሥራዬንም አዩ። 10 ያችን ትውልድ አርባ ዓመት ተቈጥቻት ነበር። ሁልጊዜ ልባቸው ይስታል፥ እነርሱም መንገዴን አላወቁም አልሁ። 11 ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቁጣዬ ማልሁ።

Psalm 96:9–13 (AMHB) ይህ መዝሙር የእግዚአብሔር ኪዳናዊ ጌትነት ከእስራኤል ዳርቻ ባሻገር እንደሚዘረጋ ያሳያል!

9 በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ; ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ። 10 በአሕዛብ መካከል። እግዚአብሔር ነገሠ በሉ። እንዳይናወጥም ዓለሙን እርሱ አጸናው፥ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል። 11 ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ; ባሕርና ሞላዋ ይናወጡ; 12 በረሃ በእርስዋም ያሉ ሁሉ ሐሤትን ያድርጉ; የዱር ዛፎች ሁሉ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይላቸዋል; 13 ይመጣልና; በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣልና; እርሱም ዓለምን በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።

Psalm 97:1–2 (AMHB) እግዚአብሔር ለእስራኤል እንደተገለጠላት ለምድር ሁሉ እንደሚገለጥ ያጎላል

1 እግዚአብሔር ነገሠ; ምድር ሐሤትን ታድርግ፥ ብዙ ደሴቶችም ደስ ይበላቸው። 2 ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው; ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።…7 ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ; መላእክቱ ሁሉ፥ ስገዱለት። 8 አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው; 9 አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና።

Psalm 98:5–9 (AMHB)

5 ለእግዚአብሔር በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ። 6 በዋሽንትና በመለከት ድምፅ በንጉሥ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ። 7 ባሕርና ሞላዋ፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ይናወጡ። 8 ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ; ተራሮች ደስ ይበላቸው፥ በምድር ሊፈርድ ይመጣልና። 9 ለዓለምም በጽድቅ ለአሕዛብም በቅንነት ይፈርዳል።

Psalm 99:1–5 (AMHB)

1 እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ; በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ። 2 እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው; እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ። 3 ግሩምና ቅዱስ ነውና ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመስግኑ። 4 የንጉሥ ክብር ፍርድን ይወድዳል; አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ። 5 አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ።

Psalm 100:1–5 (AMHB)

1 ምድር ሁሉ፥ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥ 2 በደስታም ለእግዚአብሔር ተገዙ፥ በሐሤትም ወደ ፊቱ ግቡ። 3 እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ እወቁ; እርሱ ሠራን እኛም አይደለንም; እኛስ ሕዝቡ የማሰማርያውም በጎች ነን። 4 ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ; አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ; 5 እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘላለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።

ይህ ማለት የሰዎችን ምክር ምክሩ አይደርግም ይልቁንስ ዘላለማዊ ስሉስ-ምክሩን ሕግ አድርጎ ደንግጓል። ምክሩን ያጸናል (ኢሳ 7:7; 25:1; 28:29; 30:1; )።፡ጻድቃንም በምክሩ ይኖራሉ “Psalm 1:1–3 ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ …ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።”

Psalm 33:8–12 ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፍራው፥ እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም; እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም። እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥ የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል። 11 የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘላለም ይኖራል። የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው። 12 እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።”

© 2013 – 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like 1 People Liked this
avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top