Home / Media Posts / Audio Posts / 08_02_የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግሥቱ መገለጥ (በወሰን-መጠቅ አገዛዝና በኪዳናዊ አገዛዝ መካከል ያለው ልዩነት) (Audio)

08_02_የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግሥቱ መገለጥ (በወሰን-መጠቅ አገዛዝና በኪዳናዊ አገዛዝ መካከል ያለው ልዩነት) (Audio)

Posted on

ሙሉውን የማጥኛ ጽሑፍ: የዚህን ጥናት ማብራሪያ ጹሑፍ ለማግኘት እዚህ ይጫኑ Kingdom and Sovereignty

በወሰን መጠቅ አገዛዝና በኪዳናዊ አገዛዝ (በሁሉ ጌትነቱና በህዝቡ ገጌትነቱ) መካከል ያለው ልዩነት 

 1. ወሰን-መጠቅ ጌትነት

  ይህን ጌትነት እግዚአብሔር ሁሉን በመፍጠር የተጎናጸፈው ጌትነቱ ነው። ከዚህ የተነሳ ሁሉም በመንግሥቱ አስተዳደር ሥር ነው። ሁሉ የተፈጠረ ዘንድ እስከሆነ ድረስ እግዚአብሔር በሁሉ ላይ ጌታ ነው። ይህ ንጉስ እጅግ ምጡቅ ንጉስ መሆኑን ያሳየው “እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ… ብርሃንም ሆነ!” በውሳኔ ቃል መንግሥቱን ዘርግቶ የነገሠ ልዩ ገዢ ነው! ስለዚህ በዚህ መልኩ ስናየው ማንም ወደ መንግስቱ ይገባል አይባልም ምክኒያቱም ሁሉም በመንግሥቱ ውስጥ ነው። የዚህ አገዛዝ መገለጫው የመግቦት ሥራው ነው። ይህም እግዚአብሔር ከነገስታት; ከሑነቶች ጀርባ ሆኖ የሚገልጸው አስተዳደር ነው! በዚህ አገዛዙ በምድር ተንሳርፍቶ ያለውን አመጽ ይቆጣጠራል; ክፍትን ከዚህ አትለፍ ይለዋል። ሕዝብን ሊቀጣና ፍርዱን ሊገልጽ ዘላለማዊ ሐሳቡን ከታሪክ ጋር ሊያቀናብር ክፋትንና አመጽን በአንድ ወቅት እንዲሰፍኑ ይፈቅዳል (ኢሳ 45፡ 1-7)።

  Psalm 103:19–22 እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥ መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች። 20 ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ። 21 ሠራዊቱ ሁሉ፥ ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ። 22 ፍጥረቶቹ ሁሉ በግዛቱ ስፍራ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ባርኩ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ።

  Psalm 145:13 መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው።

  Psalm 47:2 እግዚአብሔር ልዑል ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።

  Daniel 2:37 አንተ፥ ንጉሥ ሆይ፥ የሰማይ አምላክ መንግሥትንና ኃይልን፥ ብርታትንና ክብርን የሰጠህ የነገሥታት ንጉሥ አንተ ነህ።

  Daniel 5:21 ልዑል አምላክም በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ የሚወድደውንም እንዲሾምበት እስኪያውቅ ድረስ ከሰው ልጆች ተይለቶ ተሰደደ፥ ልቡም እንደ አውሬ ልብ ሆነ፥ መኖሪያውም ከምድረ በዳ አህዮች ጋር ነበረ; እንደ በሬ ሣር በላ፥ አካሉም በሰማይ ጠል ረሰረሰ።

 2. ኪዳናዊ አገዛዝ፡

  ምንም እንኳ እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ቢሆንም ነገር ግን ንግሥናው ተቀናቃኝና አልገዛም ባይ ጠላቶች አሉት። ነገር ግን ከነዚህ አመጸኞች መካከል በጸጋው ወደርሱ እየጠራ ገንዘቡ ባደረጋቸው ሕዝቡ ላይ በማዳን ይነግሳል። በሁሉቱ ጌትነቱ መካከል ልዩነቱ ይህ ንግሥና “መዋጀትና መዳን” ያለበት የንግሥና ክልል ነው። ለዚህ ነው ኒቆዲሞስን ኢየሱስ ዳግም ካልተወለድህ በስተቀር የእግዚአብሔርን መንግስት አታያትም ያለው!

  Exodus 6:5–7 (AMHB)

  5 ደግሞ እኔ ግብፃውያን የገዙአቸውን የእስራኤልን ልጆች ልቅሶ ሰማሁ; ቃል ኪዳኔንም አሰብሁ። 6 ስለዚህም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው። እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከግብፃውያንም ባርነት አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ; በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፥ 7 ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ; እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

  Daniel 2:44–47 (AMHB)

  44 በእነዚያም ነገሥታት ዘመን የሰማይ አምላክ ለዘላለም የማይፈርስ መንግሥት ያስነሣል; ለሌላ ሕዝብም የማይሰጥ መንግሥት ይሆናል; እነዚያንም መንግሥታት ሁሉ ትፈጫቸዋለች ታጠፋቸውማለች፥ ለዘላለምም ትቆማለች። 45 ድንጋዩም እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ ብረቱንና ናሱን ሸክላውንና ብሩን ወርቁንም ሲፈጨው እንዳየህ፥ እንዲሁ ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ታላቁ አምላክ ለንጉሡ አስታውቆታል; ሕልሙም እውነተኛ ፍቺውም የታመነ ነው።…47 ንጉሡም ዳንኤልን። ይህን ምሥጢር ትገልጥ ዘንድ ተችሎሃልና በእውነት አምላካችሁ የአማልክት አምላክ፥ የነገሥታትም ጌታ፥ ምሥጢርም ገላጭ ነው ብሎ ተናገረው።

  የእግዚአብሔር መንግስት ትነሳለች። እንደምጡቅ-ንግሥናው መንግስቱ አትመሰረትም; ሰማይና ምድርን የፈጠረ ዕለት ጀምሮ የተዘረጋ መንግሥት ናት; ነገር ግን በተለየ መልኩ ደግሞ ትዘራለች ትነሳለች! ይህ የኪዳናዊ አገዛዙ ነው!

  እኔም። ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ።

  Isaiah 43:15–19 ቅዱሳችሁ፥ የእስራኤል ፈጣሪ፥ ንጉሣችሁ፥ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። 16 እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል; 17 እግዚአብሔር ሰረገላውንና ፈረሱን ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል; እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፥ አይነሡም; ቀርተዋል፥ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል; እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። 18 የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ። 19 እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለህ; እርሱም አሁን ይበቅላል፥ እናንተም አታውቁትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ።

  Numbers 23:21–23 “በያዕቆብ ላይ ክፋትን አልተመለከተም፥ በእስራኤልም ጠማምነትን አላየም; አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነው፥ የንጉሥም እልልታ በመካከላቸው አለ። 22 እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶአቸዋል;ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው። 23 በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም; በጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል። እግዚአብሔር ምን አደረገ! ይባላል።”

  ማቴዎስ 13:37–42 (AMHB)

  37 እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው። መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው; እርሻውም ዓለም ነው; 38 መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው; 39 እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው; መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው። 40 እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል። 41 የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ 42 ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል; በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

  ማቴዎስ 28:18–20 (AMHB)

  18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። 19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው; እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

© 2013 – 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top