Home / Media Posts / Audio Posts / 08_01_የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግሥቱ መገለጥ (በአገዛዝና በግዛት ክልል መካከል ያለው ልዩነት) (Audio)

08_01_የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግሥቱ መገለጥ (በአገዛዝና በግዛት ክልል መካከል ያለው ልዩነት) (Audio)

Posted on

በአገዛዝና በግዛት ክልል መካከል ያለው ልዩነት፡

1- አገዛዝ

መጀመሪያ ደረጃ የሚናገረው ስለ “አስተዳደር” ወይም አገዛዝ Sovereign rule ሲሆን።

Ps 145:11–13

“ሥለ መንግሥትህ ክብር ይናገራሉ፥

“ሥለ ኃይልህንም ይነጋገራሉ፥

በዚህም ብርቱ ሥራህን;

የመንግሥትህን ግርማ ክብር ያስታውቃሉ

መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፥

ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው።”

ዳንኤል 4:3–4

3
ተአምራቱ እንዴት ታላቅ ነው!

ድንቁም እንዴት ጽኑ ነው!

መንግሥቱም የዘላለም መንግሥት ነው፥

ግዛቱም ለልጅ ልጅ ነው።

Luke 17:20

“ፈሪሳውያንም። የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ። የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም; 21 ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።”

ቆላ 1:13–14

እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን።

2- የግዛት/ የመናገሻ ክልል

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አገዛዙ የሚገለጥበትን ክልል (Realm)ለማመልከት ነው። እግዚአብሔር ምንም እንኳ ምጡቅ እንደመሆኑ በቦታና በሥፍራ ሊወሰን የማይችል መንፈስ የሆነ አምላክ ቢሆንም ነገር ግን ለሕዝቡ ራሱን የሚገልጥበትና ሕዝቡን ይመራ ዘንድ አብሯቸው የሚኖርበት መናገሻ ሥፍራን ይከልላል። ከብሉይ ወደአዲስ ያለው እንቅስቃሴ ከእስራኤል ክልል ጀምሮ እየሰፋ ዓለምን ሁሉ የሚሞላ እንቅስቃሴ ነው።

ማቴ 8:11–13 “እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ; 12 የመንግሥት ልጆች ግን በውጭ ወደ አለው ጨለማ ይጣላሉ; በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። 13 ኢየሱስም ለመቶ አለቃ። ሂድና እንዳመንህ ይሁንልህ አለው። ብላቴናውም በዚያች ሰዓት ተፈወሰ።”

ማቴ 13:41–42 “የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ 42 ወደ እቶነ እሳትም ተጣሉ

ማቴ 26:26–29 “ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና። እንካችሁ፥ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። 27 ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ። ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ; 28 ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። 29 ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣውም።አቸዋል; በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”

ራዕ 5:9–10

መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።

ራዕ 11:15–17
“ሰባተኛው መልአክ ነፋ; በሰማይም። የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል 16 የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው 17 ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ። ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን;”

ራዕ 21:1–8
አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርንም አየሁ፥ ፊተኛው ሰማይና ፊተኛይቱ ምድር አልፈዋልና፥ ባሕርም ወደ ፊት የለም። 2 ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም፥ ለባልዋ እንደ ተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ፥ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ። 3 ታላቅም ድምፅ ከሰማይ። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል; 4 እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ። 5 በዙፋንም የተቀመጠው። እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ። ለእኔም። እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸውና ጻፍ አለኝ። 6 አለኝም። ተፈጽሞአል። አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውኃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ። 7 ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል አምላክም እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል። 8 ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው; ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።

 

© 2013 – 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like 1 People Liked this
avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top