Home / Media Posts / Audio Posts / 009-010: የመጥራቱ ተሥፋ ምን እንደሆን ታውቁ ዘንድ (የኤፌሶን ምዕራፍ አንድ ጥናት)

009-010: የመጥራቱ ተሥፋ ምን እንደሆን ታውቁ ዘንድ (የኤፌሶን ምዕራፍ አንድ ጥናት)

Posted on

 

Exegetical outline

ማውጫ

Open Outline
 1. በእ/ር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ (Παῦλος ἀπόστολος Χριστοῦ Ἰησοῦ διὰ θελήματος θεοῦ)

  1. ሐዋርያነት በቀጥታ ከኢየሱስ የተቀበለው ጥሪ ነው ( 1:1; 1 Cor. 1:1; Cf. Acts. 9:1-30; 22:1-21; 26:1-23)
   1. የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋሪያ፡- የክርስቶስ የግል ወኪል ማለት ነው፡ ከዚህ የተነሳ ጳውሎስ እንደ ሐዋርያነቱ ቃሉ መለኮታዊ ሥልጣን አለው
  2. በእ/ር ፈቃድ ሲል ይህን የሐዋርያነቱ ምንጭ ማን እንደሆን ያሳያል ( 1:1)
 2. በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉ ለታመኑ በኤፌሶን ለሚገኙ ቅዱሳን [τοῖς ἁγίοις τοῖς οὖσιν [ἐν Ἐφέσῳ] καὶ πιστοῖς ἐν Χριστῷ Ἰησοῦ,]

  1. በኤፌሶን ላሉ ሲል በአንድ ሕንጻ ሥር የሚያመልኩ አማኖችን በምናባችን እናስብ ይሆናል ሆኖም ግን ኤፌሶን ወደ 250 ሺህ ሕዝብ የሚኖርባት ከተማና የትንሿ እሲያ ዋና ከተማ፤ የጥንትዌው አለም 7 ድንግቶች ተብለው ከሚታወቁ መካከል የሆነችው የአርጠሚስ ጣኦት አስተናጋጅ ከተማ ነበረች።
   1. ታሪካዊ ዓውድ፡
    1. አርጠሚስ የእድል፤ የፍሬማነት…
    2. ከአቴና ካለችው ቤተ ጣዖት ይልቅ ዝና ያተረፈውች ናት
    3. ሐዋ 19 ያንብቡ
   2. ስለዚህ ይህ ደብዳቤ ምናልባት ወደ አንድ ደርዘን ያህል ወደ ሚቆጠሩ በየቤቱ ያሉ ቤተክርስቲያናትን ያመለክታል።
  2. ቅዱሳን፡
   1. ቅዱሳን ሲል አሕዛብንና አይሁድን ጨምሮ በጥቅሉ አማኞችን እንጂ ከአማኞች መካከል ያሉ ጥቂት መንፈሳዊ ሰዎችን አይደለም።
   2. ይህ ቃል በብሉይ ለእ/ር ሕዝብ በጥቅም ላይ የዋለ ነበር (Ex. 22:31; Pss. 16:3; 34:9; Dan. 7:18, 21, 22, 25)
 • ቅዱሳን ያስባላቸው እነርሱ ካደረጉት የተነሳ ሳይሆን
  1. እ/ር ሕዝቡ ይሆኑ ዘንድ ስለመረጣቸው ነበር
  2. ባህርይውን፤ ቅድስናውንና ክብሩን ያንጸባርቁ ዘንድ ስለጠራቸው ነው (Lev. 11:45; 19:2)
 1. ይህ መጠሪያ ለአዲስ ኪዳን ሕዝብም መጠሪያ ሆኗል። (Acts. 9:13; Heb 3:1; Jude 3; Rev. 5:8)
 2. በተለይ ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን መጠሪያ በሙያላይ ያውለዋል (Rom 1:7; 1 Cor 1:2; 2Cor 1:1; Phil 1:1; Col 1:2)
 1. በክርስቶስ ኢየሱስ ለሚያምኑ ()
  1. የእምነታቸውን ማረፊያና ምክኒአይት ማመልከቱ ነው እንጂ የእነርሱን መንፈሳዊ ፍሬ ይህም ታማንነት አይደለም
  2. ይህ እምነት በዚህ መጽሀፍ እያደገ ይመጣል (Eph. 1:13, 15, 19; 2:8; 3:12)
 2. ከእ/ር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን [χάρις ὑμῖν καὶ εἰρήνη ἀπὸ θεοῦ πατρὸς ἡμῶν καὶ κυρίου Ἰησοῦ Χριστοῦ.]
  1. ተመሳሳይ ሰላምታ (Rom 1:7; 1 Cor 1:3; 2Cor :1:2; Gal 1:3; Phill 1:2; 2 Thess. 1:2; Phlm. 3)
  2. ጸጋና ሰላም የሐዋርያው ተወዳጅ ሰላምታ ሲሆን እነዚህ ቃሎች የሐዋርያውን ነገረ መለኮታዊ አስተምሕሮት ሰብሰብ የሚያደርጉ ቃሎች ናቸው። የአዲስ ኪዳን አበይት በረከቶች ናቸው። ይህን በማለቱ ይህ በኤፌሶን ተበታትነው ያሉ አህዛብ አማኞች የአዲስ ኪዳን ህዝብ አካልና የእ/ር ቤተሰብ አባል ናቸው።
   1. ጸጋ (95 ጊዜ በደብዳቤዎቹ በመደጋገም) ለሐዋርያው የአዲስ ኪዳን ልዩ ባሕርይ ነው (Titus. 2:11)
    1. this word in the pagan world was common to denote the faor of the gods or the Emperor toward people
    2. በብሉይ ይህ ቃል ‘ኸሰድ’ ከሚለው የእብራይስጥ የፈለሰ ሐሳብ ነው። ይህ ቃል የእ/ር ከዝቡ ጋር ያለውን የቃል ኪዳን ፍቅር ያመለክታል ( 34:6-7; Num 14:17-19) Ps. 118-1-4
   2. ጸጋ
    1. የጽድቅ ብያኔ ለማግኘታችን ምክኒአይት ነው Rom 3:24
    2. ነጻ የምህረት ሥጦታ ነው 5:15, 17
    3. ደግሞም በእለት ሕይወታችን ከቅድስናው ተካክፋዮች እንድንሆን የምንለወጥበትና ከጌታ የተሰጠንን አገግሎት የምንፍጽበት መንገድም ጭምር ነው 12:9
    4. ስለዚህ በመግቢያው ላይ ጸጋ ብሎ ሰላምታ ሲአቀርብ ሐዋርያው ይህን አዲስ የኪዳን ህዝብ ላይ የጸጋውን ባለጠግነት እንዲያፈስ መለመኑ ነው ( 6:14-15)
   3. ሰላም
    1. ነብዩ ህዝቄል የአዲስ ኪዳን ልዩ ገጽታ ሰላም እንደሆነ ያውጃል (Ez. 37:26)
    2. ይህ የሰላም በረከት ምክኒአይት መሲሁ ነው Isa. 9:6
 • ትሁት ንጉስ ሆኖ የሚገለጠው Zech. 9:9-10
 1. የመሲሁ መወለድ መልካም ዜና በመላእክት የሰላም ዘመን መሆኑ Luke 2:14
 2. ኢየሱስ ለደ/መዛሙርቱ የተዋላቸው ነው John 14:27
 3. ሐዋርያት ስብከት አዋጅ Acts. 10:36
 • የመጽደቃችን ውጤት ነው Rom. 5:1; Gal 5:22
 1. በዚህ መጽሀፍ፡
  1. ጸጋ:- Eph. 1:2, 6,7; 2:5, 7, 8; 3:2, 7, 8; 4:7, 29; 6:24
  2. ሰላም፦ Eph. 1:2; 2:14, 15, 17; 4:3; 6:15, 23
 2. የዚህ ጸጋ ምንጭ አብ ብቻ ሳይሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ጭምር ነው።
  1. ከሙታን በመነሳቱ ከፍ ብሎ ከሥልጣናት በላይ ተሹሟል (1:4) ስለዚህ ኢየሱስ ጌታ ነው
  2. ሐዋርያው የኢየሱስን ጌትነት አጽኖት ያደርጋል፤ በዚህ መጽሀፍ በተለይ ጌትነቱ በሰማያዊ ሥፍራ ላኡ ሐይላት፤ ሥልጣናት፤ አለቃት…መገለጡን ያውጃል።

© 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like 1 People Liked this
avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top