Home / Media Posts / Audio Posts / 009-009: በወንጌል የተቃኘ ተስፋ-ስለዚህ ተስፋ በወንጌል የእውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ

009-009: በወንጌል የተቃኘ ተስፋ-ስለዚህ ተስፋ በወንጌል የእውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ

Posted on

[sz-ytvideo url=”https://www.youtube.com/watch?v=af-Aw2EYEK4″ theme=”dark” cover=”local” responsive=”y” autoplay=”n” loop=”n” fullscreen=”y” disablekeyboard=”n” disableiframe=”n” disablerelated=”n” delayed=”n” schemaorg=”n” /]

በሰማያት ከተዘጋጀላችሁ ተስፋ የተነሳ (τὴν ἀποκειμένην)

የተዘጋጀ ተስፋ

 • የዚህ ዓረፍተነገር ባለቤት እግዚአብሔር በመሆኑ የዚህ ተስፋ አዘጋጁ እግዚአብሔር ነው።
 • ከዚህ የተነሳ የተስፋችን እርግጠኛነት የተመሰረተው በሰማይ ያለው እርሱ የሚሰራው ሥራ በመሆኑ ነው። (cf. 2 Tim 4:8).

በሰማያት ያለ ተስፋ (ὑμῖν ἐν τοῖς οὐρανοῖς)

ይህ ሰማይ የሚለው ቃል ሁለት እውነታዎችን በውጥረት ይይዛል

 1. በአንድ ወገን አሁን ተስፋችንን እየተካፈልን ነው (2:12- 15; 3:1-5),
  • የመልዓክ ራዕይ አይቻለሁ የሚልና ቀናትንና ወራትን አከብራለሁ የሚል ሌላ መካከለኛ እንዳያሰናክላችሁ ተጠንቀቁ።
   • የመለኮት ሙላት በሙሉ ያለው በእርሱ ነውና
   • በአለቅነትና በሥልጣናት ራስ በሆነው በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋልና፦ ተገረዛችሁ፤ ተቀበአችሁ፤ ተነሳችሁ፤ ሕይወትን ሰጣችሁ፤ ይቅር አላችሁ፤ እዳውን ደመሰሰ፤ ሥልጣናትን ገፈፈ…እንግዲህ ማንም አይፍረድባችሁ (ወይም ሌላ የቀራችሁ አለ ብሎ ማንም አያሳንሳችሁ...ክርስቶስ በነጠላ በቂ ነው!)
 2. በሌላ ወገን ደግሞ ተስፍችን ገና ወደ ፊት ነው፤
  • ይህ በሰማይ የተቀመጠልንን ተስፋ (1:27) ሲገለጥ “ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ። ተስፋችን ተጠብቆ ያለበት ሥፍራ “ሰማያት መሆኑ”
  • ተስፋችን ወደፊት ገና የሚገለጥልን እንደሆንና በዚህ ምድር ሙሉ በሙሉ የእኛ አለመሆኑን ይጦቁመናልColossians 3:4

በወንጌል የእውነት ቃል የተገኘ ተስፋ (ἐν τῷ λόγῳ τῆς ἀληθείας τοῦ εὐαγγελίου)

ስለዚህ ተስፋ በወንጌል የእውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ ይህም ወደ እናንተ ደርሷል። ይህንን ወንጌል ከሰማችሁበትና የእ/ርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በዓለም ዙሪያ እየሰራ እንዳለ ሁሉ በእናንተም ዘንድ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው” (ἣν προηκούσατε ἐν τῷ λόγῳ τῆς ἀληθείας τοῦ εὐαγγελίου τοῦ παρόντος εἰς ὑμᾶς, καθὼς καὶ ἐν παντὶ τῷ κόσμῳ ἐστὶν καρποφορούμενον καὶ αὐξανόμενον καθὼς καὶ ἐν ὑμῖν, ἀφʼ ἧς ἡμέρας ἠκούσατε καὶ ἐπέγνωτε τὴν χάριν τοῦ θεοῦ ἐν ἀληθείᾳ)

 1. ይህ ተስፋ ይዘት ያለው ተስፋ ነው፤ የዚህም ተስፋ ይዘት ከኤጳፍራ የሰሙት ወንጌል ነው እርሱም የእውነት ቃል ነው።
 2. ወንጌል ሰዎችን ወደ እ/ር መንገሥት የሚያስገባ መሿለኪያ ብቻ አይደለም። ወንጌል የክርስትና መሰረት ነው።
  • ሰማችሁ፤ ተቀበላችሁ’ ተመሰርታችሁ፤ ተደላድላችሁ…
  • ወንጌል ሐያል የእ/ር ቃል ነው (1:25; ) የክርስቶስ ቃል ነው (3:16)
  • ከዚህ የተነሳ ሃያልነቱን በሚያስገርም ቃል ይገልጠዋል “በዓለም ዙሪያ እየሰራ ያለ ሐይል ነው”። ምንም እንኳ ሐዋርያው በቆላስያስ እግሩ ረግጦ ባያውቅም ይህ ወደ አሕዛብ መንደር በአገልጎቱ መቀጣጠል የጀመረው የወንጌል ቃል እንደሰደድ እሳት እይተቀጣጠለና እንደ እንጉዳይ እየፈላ በመሆኑ “በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ” ማለት ይችላል።
  •  በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤  በእግዚአብሔር የምትወደዱ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ተመረጣችሁ አውቀናልና። ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ። ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤ ስለዚህም በመቄዶንያና በአካይያ ላሉት ምእመናን ሁሉ ምሳሌ ሆናችሁላቸው። ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፥ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል። (1 Thessalonians 1:2–8 2-3)

“በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው። 7 የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ። (Acts 6:6–7)

“ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ። 24 የእግዚአብሔር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር። 25 በርናባስና ሳውልም አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋር ይዘውት መጡ። (Acts 12:23–25)

እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር። (Acts 19:20)

ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ። 32 አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ። (Acts 20:31–32)

ወንጌል የዚህ ተስፋ መፈጸም የምሥራች ቃል ነው (Isa 40:9; 41:27; 52:7 )

 • ጸጋ፦ የእ/ር ጸጋ በወንጌል የተገለጠ የእ/ር በጎ ስጦታ በመሆኑ ወንጌልና ጸጋ አይነጣጠሉም። ያለ ወንጌል መታወጅ ጸጋ አይሰጥም። (ምናልባት ይህ ይሆን የዘመናችን ችግር?)
  1. ጸጋ የወንጌል ማዕከል ነው፦ Rom 4:16; 5:2; Gal. 1:6
  2. ጸጋ የእ/ር በጎ ሥጦታ ነው (Rom. 3:24; 5:15, 17; Eph. 2:8)
 • ይህም ስጦታ የተገኘው በኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ አማካኝነት ነው (2 Cor 12:9; Eph 3:7; Acts 20:3)

በመንፈስ የሆነ ፍቅራችሁ ( 15:30; Rom 5:5; 15:30; Gal 5:22 – 23)

© 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top