Home / Media Posts / Audio Posts / 009-008: በወንጌል የተቃኘ የቃል-ኪዳን ሕይወት፡ እምነት ፍቅርና ተስፋ (ፍጻሜ ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ P8)

009-008: በወንጌል የተቃኘ የቃል-ኪዳን ሕይወት፡ እምነት ፍቅርና ተስፋ (ፍጻሜ ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ P8)

Posted on

[sz-ytvideo url=”https://www.youtube.com/watch?v=FsajmGuHcy8″ theme=”dark” cover=”local” responsive=”y” autoplay=”n” loop=”n” fullscreen=”y” disablekeyboard=”n” disableiframe=”n” disablerelated=”n” delayed=”n” schemaorg=”n” /]

የቆላስያስ ምዕራፍ አንድን ሐቲታዊ መግለጫ (የሐሳቡ አወቃቀር/ Exegetical Phrasing) ለማግኘት እዚህ ይጫኑ!

ስለ እናንተ በምንጸልይበት ጊዜ፥ የጌታችንን የኢየሱስን አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤ ምክኒያቱም በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተናል[ἀκούσαντες τὴν πίστιν ὑμῶν ἐν Χριστῷ Ἰησοῦ καὶ τὴν ἀγάπην ἣν ἔχετε εἰς πάντας τοὺς ἁγίους]

 1. ሐዋርያው ወደ ምሥጋናና ወደ ልመና ጸሎት ያነሳሳው ስለ ቆላስያስ ሰዎች የሰማው ነገር ነው፦
  1. በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነት፦ ይህ የቆላስያስ ሰዎች በክርስቶስና በወንጌሉ ላይ ያለ እምነታቸውን ያሳያል፤ ይህም በወንጌል ሀይል አማካይነት ነው።
   1. የሚያድን እምነት[ችሁ] Romans 4:1-14) የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው።
    • Colossians 2:11–13 “የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሆናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ።በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችሁ፥ በጥምቀት ደግሞ፥ ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር አሠራር በማመናችሁ፥ ከእርሱ ጋር ተነሣችሁ። እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ”
    • እምነትና ሕግ፦ Romans 4:1-15
    • Romans 5:1–2 1 እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤ 2 በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን።
   2. በክርስቶስ ኢየሱስ ስላለ፦ ይህ እምነት በክርስቶስ ከመሆን የተነሳ የተገኘ መሆኑን ይጦቁመናል። ይህም “በ” የሚለው ቃል ከክርስቶስ ጋር ያለን አንድነታችንን ይጦቁማል። ለዚህ ማብራሪያ የሚቀጥለውን እንይ
  2. ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር፦ ይህ ፍቅር ከላይ ከተጠቀሰው እምነት (ይህም የክርስቶስ ከመሆን የተነሳ) የተገኘ ፍቅር ነው። ፍቅር በክርስቶስ ኢየሱስ ከማመን የመነጨ ነው በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ በፍቅር የሚሰራ እምነት/ life of faith። ይህም በክርስቶስ መሆንና ለቅዱሳን ሁሉ ያለ ፍቅር ሊለያዩ የማይችሉ አንድ ገጽታዎች እንጂ የተነጣጠሉ መንፈሳዊ ፍሬዎች አይደሉም።
   • Galatians 5:4–6 4 በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። እኛ በመንፈስ ከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና። በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።
   • 1 Timothy 1:3–8 3-4 ወደ መቄዶንያ በሄድሁ ጊዜ፥ አንዳንዶች ልዩ ትምህርትን እንዳያስተምሩና ወደ ተረት መጨረሻም ወደሌለው ወደ ትውልዶች ታሪክ እንዳያደምጡ ልታዛቸው በኤፌሶን ትቀመጥ ዘንድ ለመንሁህ፤ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮች ክርክርን ያመጣሉና በእምነት ግን ላለ ለእግዚአብሔር መጋቢነት አይጠቅሙም። የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው፤ ከእነዚህም አንዳንዶች ስተው፥ የሚሉትን ወይም ስለ እነርሱ አስረግጠው የሚናገሩትን ሳያስተውሉ፥ የሕግ አስተማሪዎች ሊሆኑ እየወደዱ፥ ወደ ከንቱ ንግግር ፈቀቅ ብለዋል። 8 ነገር ግን ሰው እንደሚገባ ቢሰራበት ሕግ መልካም እንደ ሆነ እናውቃለን፤
 2. ፍቅርና እምነት ስለሚመነጭ ከዚህ የተነሳ በዚህ ደብዳቤ ሐዋርያው በእምንት እንዲጸኑ ግድ ይላቸዋል። (Col. 1:23; 2:5, 7) ስለዚህ ይህ ዓይነት እምንት ያላቸው ደግሞ ፍቅር ያስተሳስራቸዋል
  • “እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ። ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ። በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት (ሁሉንም በፍጹም አንድነት የሚያስተሳስረውን ፍቅርን ልበሱት) (Colossians 3:13–14)

[ይህም የሆነው/ ምክኒያቱም] በሰማይ ተዘጋጅቶ ከተቀመጠላችሁ ተስፋ የተነሳ ነው [διὰ τὴν ἐλπίδα τὴν ἀποκειμένην ὑμῖν ἐν τοῖς οὐρανοῖς

 1. እምነት፤ ፍቅርና ተስፋ፦ ከዚህ ቀጥሎ የእምነትና የፍቅር መሰረት ምን እንደሆነ ይነግረናል። አመጣጡ በትክክል ግልጽ ባይሆንልንም (ለምሳሌ በወንጌላት ላይ አሊያም በሐዋርያት ሥራ ላይ አልቀረበም) ሆኖም ግን የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች የሚጋሩት አንድ የአዲስ ኪዳን ህይወት ቀመር አለ፤ ይህም “እምነት፤ ተስፋና ፍቅር” ናቸው።
 2. የሦስቱ ቀመር በአዲስ ኪዳን
  1. በጳውሎስ ደብዳቤዎች፦ 1 Thess 1:3; 5:8; Gal. 5:6; Rom 5:1 -5; Eph. 4:2-5; Titus 2:2; 1 Cor 13: 13;
  2. በሌሎች:- Heb 6:10-12; 10:22-24; 1 Pet 1:3-8; 21 – 22
  3. “እንዲህም ከሆነ፥ እምነት ተስፋ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው” 1 Corinthians 13:13
   1. አሁን ከፍጻሜ ጋር ሲነጻጸርና ሲስተያይ። አሁን…በድንግዝግዝ…ያን ጊዜ ፊት ለፊት
   2. ”ይሻራል….ይኖራል” የሚሻር ነገር አለ…የሚኖር ነገር አለ…በመካከል ያለው ፍጹም የሆነው ሲገለጥ ነው። ይህም ፍጻሜያችን ነው።
   3. ፍቅር ግን እንደሌሎቹ ሥጦታዎች አይደለም፤ ፍቅር ይቀጥላል።
   4. ይህ ፍቅር ከአሁን ጀምሮ ወደ ዘላለም እምር የሚል እውነታ ስለሆነ፤ በፍቅር ላይ እምነትና ተስፋን በመደረብ ያ ሊመጣ ያለውን ፍጹም የፍቅር አንድነት አሁን በእምነትና በተስፋ መገለጡን ለማመልከት “እምነትና ተሥፋን” ይጠቅሳል ምክኒያቱም እነዚህ ሊለያዩ የማይችሉ እውነታዎች ስለሆኑ፤ አንዱ ያለሌላው ትርጉም አይሰጥም። To show the present life in christ.
   5. የፍቅር ትልቅነት የተመሰረተው፦ ምንም እንኳ ፍቅር አሁን ከእምነትና ተሥፋ ጋር ሳይነጣጠል -ልክ ሥጋ ከመንፈስ እንደማይለይ- አብሮ ወደ ፍጻሜ ቢገሰግሥም፤ አሁን ፍቅር ከመንፈሳዊ ስጦታዎች ጋር ቢሰራም (ፍቅር የስጦታውቹ የተሻለ መንገድ) ሁሉም “በዚያን ጊዜ’ ሲሻር ደግሞም እምነትና ተስፋ ወደ ፍጻሜያቸው ሲደርሱ (Rom. 8:24; 2 Cor 5:7) ፍቅር ግን ወደ ሚመጣው ዘመን ይሻገራል።
   6. ስለዚህ የአሁን ሕይወታችን ሊመጣ ላለው ፍጹም ተስፋ ቅምሻ ነው።
 3. የሦስቱ ቀመር ምንነትና አሠራር
  1. በሌሎች ሥፍራ እምነት የተስፋ (Rom 5:2; Gal 5:5) እና የ”ፍቅር” (1 Cor 13:2; 1 Tim 1:5) መሠረት እንደሆነ ነግሮናል
  2. ሦስቱም በአንድ ላይ ሲጠቀሱ አጽንዖት የሚያደርገው
   • እምነትና ፍቅር በልዩ የሲናው ኪዳን ዋነኛ መለዮ፤ ያህዌህ ለቃልኪዳኑ ታማኝ ነው። ከሕዝቡም የሚጠብቀው ይህንኑ ታማኝነትና ፍቅር ነው፡፤“”
   • በወንጌል የተቃኘ የቃል-ኪዳን ሕይወት ምን እንዲመስል ለማሳየት ነው፡፤ (1 Cor 13:13; 1 Thess 1:3)
   • የአዲስ ኪዳን ክርስቲያናዊ ሕይወት (የአዲስ ኪዳን ሕዝብ መለዮ John 13:34-35; 1 John 3:14; 4:20) በክርስቶስ ማመንና በመንፈስ መመራት ሲሆኑ እነዚህም የድሮውን የሲና ኪዳን ቶራህ ሕይወት (Torah observance) ተክቷል;
   • life in the New Covenant produced by the gospel. “Together these words embrace the whole of Christina existence as believers lived out the life of the Spirit in the present age, awaiting consumation. They have faith in God, trust him to forgive and accept them through Christ. Though they don’t see it fully as it were face to face but dimly as a reflection in a mirror, yet they trust in his goodness and mercy, looking to their Hope for the future. Through His resurrection and the gift of the Spirit they have become a thoroughly future oriented people; the present age is on its way out, therefore they live in the present “as if not- 1 Cor 7:29-31”, not conditioned by the present with its hardship or suffering. They are on their way home, destined for an existence in the presence of God that is “face to face”And they love one another as they live this life of faith and hope in the context of a community of brothers and sisters of familiar faith and hope. In the present life of the church these three remain or continue: faith, hope, and love.” (Gordon D. Fee, 1 Corinthians, P.650)
  3. በዚህ ሥፍራ ግን ከሌሎች የሚለየው አጽንዖቱ ያረፈው በተስፋ ላይ ነው። ይህንንም የምናየው እርስ በርሳቸው እይተፍተለተሉ በሚወጡ አረፍተነገሮች ይህንን ታላቅ እውነታ ይነግረናል
   1. ምክኒያቱም፦ ((እምነትና ፍቅር)-› ተስፋ
   2. ከላይ አብን ሐዋርያው የሚያመሰግንበትን ምክኒያት ነግሮናል። ይህም በክርስቶስ ስላላቸው እምነትና ለቅዱሳን ሁሉ ስላላቸው ፍቅር ሲሆን አሁን ደግሞ እነዚህ (እምነትና ፍቅር ወይም በፍቅር የሚሰራ እምነት-love as a manifestation of faith) ደግሞ ሌላ ምክኒያት አላቸው- በሰማይ ከተዘጋጀ ተስፋ የተነሳ። ይህም ተስፋ የፍቅርና የእምነት ምንጭ ሆኖ እናየዋለን።
 4. ተስፋ፦ በቅዱሳት መጻሕፍት ላይ ተስፋ ነገ ከዛሬ ይሻላል የሚል ግላዊ ጉጉት አይደለም።
  1. ተስፋ የተመሰረተው የታመነና ሊዋሽ የማይችለው እ/ር በገባው የተስፋ ቃል ላይ! ከዚህ የተነሳ ተስፋችን ራሱ እግዚአብሔር ነው
  2. በብሉይ ያህዌህ የእስራኤል ኪዳናዊ ተስፋ መሰረት እንደነበር (Pss. 25:3; 31:24; 71:5; 131:3; Ps. 37:9; Lam. 3:21–26), በአዲስ ኪዳን ደግሞ አብ በክርስቶስ ተስፋችን ነው (1 Tim. 1:1). ይህም መዝሙረኞች ያህዌህን እንደ ዓለት የመሰሉት ከዚህ የተነሳ ነው።
  3. 2 Corinthians 1:8–11 8 በእስያ ስለ ደረሰብን መከራችን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ታውቁ ዘንድ እንወዳለንና፤ ስለ ሕይወታችን እንኳ ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከዓቅማችን በላይ ያለ ልክ ከብዶብን ነበር፤ 9 አዎን፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር።እርሱም ይህን ከሚያህል ሞት አዳነን፥ ያድነንማል፤ እናንተም ደግሞ ስለ እኛ እየጸለያችሁ አብራችሁ ስትረዱን፥ በብዙ ሰዎች በኩል ስለ ተሰጠን ስለ ጸጋ ስጦታ ብዙዎች ስለ እኛ ያመሰግኑ ዘንድ፥ ወደ ፊት ደግሞ እንዲያድን በእርሱ ተስፋ አድርገናል። [የዘላለም ሕይወት፤ የሙታን ትንሳኤ እጩዎች ስለሆንን ተስፋ እናደርጋለን]
  4. ይህ ተስፋ እ/ር በሰጠው ተስፋ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ይህ ተስፋ ደግሞ በብሉይ ይሰራ የጀመረው በክርስቶስ የፈጸመውና ዳግም ሲመለስ የሚያጠናቅቀው ፕሮጀችት ነው “ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል። ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ ” (Titus 2:11–15)
  5. ስለዚህ ተስፋ አያሳፍርም/disappoint (Rom 5:5)
 5. ከወንጌል የመነጨ ተስፋ፡ ይህም ተስፋ በዚህ ደብዳቤ ላይ ከወንጌል የመነጨና በወንጌል የሚታወጅ ተስፋ ነው
  • “ይህም፥ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ፥ በሃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል። ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፥ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ” (Colossians 1:23)
  • “ይህም ቃል ከዘላለምና ከትውልዶች ጀምሮ ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው፥ አሁን ግን ለቅዱሳኑ ተገልጦአል። 27 ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ፥ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ የሆነው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው” (Colossians 1:26–27)

© 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top