Home / Media Posts / Audio Posts / 009-005: የማይዋሽ እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ (ፍጻሜ ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ P5)

009-005: የማይዋሽ እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ (ፍጻሜ ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ P5)

Posted on

ስለ ዘር አስደናቂ የሆነ እውነት አለ። በእጃችሁ አንድ ዘር፤ ለምሳሌ ያህል የብርቱካን ዘር፤ ብትይዙ በዚህ ዘር ውስጥ እንኳን ትልቅ የብርቱካን ዛፍ የሚያክል ነገር ሊያወጣ ቀርቶ በውስጡ ሕይወት ያለበትም አይመስለም። new-seeds

ሆኖም ግን ዘር ሦስት ነገሮችን ይፈልጋል፦ አየር፤ ርጥበትና አፈር። ከነዚህ ሁለቱ በዙሪያው እውነት ሲሆኑ፤ ዘር አስደናቂ ነገር ያደርጋል። መብቀል ይጀምራል! አንዳንድ ዘር በመጀመሪያ ሥር ይልካል። ይህም ርጥበትና አየር አግኝቻለሁ ነገር ግን አፈር የት አለ? የሚል ይመስላል። አፈር ካገኘ በኋላ አሁን ግንድ ለመላክ ትዕዛዝ ያስተላልፋል።

እንዲሁ በትንሹ የአዲስ ኪዳን ሕዝብ ህልውና እነዚህን ሁለት እውነታዎች ይፈልጋል። እነዚህም

  1. የፍጻሜ ተስፋ (Eschatological Hope) እና
  2. የልጁና የመንፈሱ መላክ ናቸው (The Gospel Mission of the Son and the Spirit)

እነዚህ ሁለቱ በሌሉበት ሰዎች እግዚአብሔርን በማወቅ ለማደግ አይችሉም። ፍጻሜ ክርስቲያናዊ ሕይወታችንን ይቃኛል ። ወደፊት የምንሆነውን አሁን በክርስቶስ አማካኝነት እግዚአብሔር በመንፈሱ እያካፈለን ሲሆን አንድ ቀን ደግሞ ሙሉ በሙሉ እንወርሳለን። ይህም እውን የሚሆነውንና እየሆነው ያለው በልጁና በመንፈሱ አማካኝነት ነው። ትምሕርታችንም በነዚህ በሁለቱ አበይት ክፍሎች ከፍለናል።

figure_salvation_kingdomከዚህ ቀደም እግዚአብሔርን ማወቅ መዳን፤ መዳን ደግሞ እግዚአብሔርን ማወቅ እንደሆን አይተናል። መዳናችንም አንድ ወጥ፤ ሁሉን ዳሰስ እውነታ ነው። ከዚህ የተነሳ መዳናችን በሶስት መልኩ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡ ድነናል፤ እየዳንን ነው፤ እንድናለን። ይህ የመዳናችን ሦስት ገጽታ የተመሰረተው በእግዚአብሔር መንገሥት አገላለጥ ነው። መዳን የእግዚአብሔር መንገሥት ስጦታ (ዮሐ 3:1-3) በመሆኑ መዳናችን የእግዚአብሔርን መንግሥት ባህርይ ይንጸባረቅበታል። የእግዚአብሔር መንገስት በክርስቶስ መምጣት ስለተገለጠ መዳናችን ተመርቋል። አሁን ድነናል። ከዚህ የተነሳ የአሁኑ ኑሯችን በሁለቱ የተወጠረ ነው።

ሆኖም ግን ገና ክርስቶስ ዳግም ስለሚመለስ፤ እስኪመጣ ድረስ መዳናችንን እንጠባበቃለን። ይህም መዳናችን ተስፋ ነው። ይህ ተስፋ በአንድ ወገን የክብር ተስፋ ቢሆንም በሌላ ወገን ደግሞ የአሁን ገንዘባችን ነው።

ከዚህ ቀጥለን የዚህን ተስፋ ምንነት በሚከተሉት ተከታታይ ክፍሎች እንመልከት።

  1. የተስፋችን እርግጠኛነት የተመሰረተው በእግዚአብሔር ታማኝነት ነው (ዕብ 6፡11-20)
  2. ተስፋችን የተመሰረተው እግዚአብሐር ከዘመናት በፊት ባቀደው እቅድ ላይ ነው (ቲቶ 1:3/ 2ጢሞ 1:9-11)
  3. ተስፋችን ያነጣጠረው በዘላለም ሕይወት ነው (ቲቶ 1:3)
  4. ተስፋችን አንድ ተስፋ ነው (ኤፌ 4:3-6)
  5. ተስፋችን የእግዚአብሔር ተስፋ ቃል መፈጸም ነው (ገላትያ 3-4)
  6. ተስፋችን ሲገለጥ፡- እምነት/ ተስፋ/ ፍቅር (ከወንጌል የመነጨ የአዲስ ኪዳን ሕይወት ቀመር – ቆላ. 1፡3-5)

ይህንን ለማሰር በመጨረሻ የኤፌሶን መጽሐፍ ምዕራፍ አንድን ቃል በቃል እናጠናለን። ስለዚህ አሁን የመጀመሪያውን እንመልከት

የተስፋችን እርግጠኛነት የተመሰረተው በእግዚአብሔር ታማኝነት ነው

[sz-ytvideo url=”https://www.youtube.com/watch?v=ynSHmSpEsvA” theme=”dark” cover=”local” responsive=”y” autoplay=”n” loop=”n” fullscreen=”y” disablekeyboard=”n” disableiframe=”n” disablerelated=”n” delayed=”n” schemaorg=”n” /]

“በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን። እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ። በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ እያበዛሁም አበዛሃለሁ ብሎ፥ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ፥ በራሱ ማለ፤  እንዲሁም እርሱ ከታገሰ በኋላ ተስፋውን አገኘ።  ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፥ ለማስረዳትም የሆነው መሐላ የሙግት ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል፤  ስለዚህም እግዚአብሔር፥ የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደ ማይለወጥ አብልጦ ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ፥ እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ፥ በመሓላ በመካከል ገባ፤  ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው፤  በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ”  (Heb 6:11–20)

“የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ፥  በዘመኑም ጊዜ፥ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ” (Tt 1:1–3)

“ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥  አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል” (2 Ti 1:9–11)

“በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤  አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤  ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።  ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን” (Eph 4:4–7)

© 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like 1 People Liked this
avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top