Home / Portfolio / KOG / 008_08 የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግስቱ መገለጥ (Audio)

008_08 የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግስቱ መገለጥ (Audio)

Posted on

የአሁኑና የመጪው ዘመን – ማጠቃለያ

ማቴዎስ 12:31–32 “ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም። በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል; በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም [ዘመን] ቢሆን ወይም በሚመጣው [ዘመን] አይሰረይለትም።”

ማርቆስ 10:29–30 ‘ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ። እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥ አሁን በዚህ ዓለም [ዘመን] ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም [ዘመን] የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።
Chart-Eschatology

ሉቃስ 20:34–36 “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው። የዚህ ዓለም [ዘመን] ልጆች ያገባሉ ይጋባሉም፥  ያን ዓለም [ዘመን]ና ከሙታን ትንሣኤ ሊያገኙ የሚገባቸው እነዚያ ግን አያገቡም አይጋቡምም፥ እንደ መላእክት ናቸውና፥ ሊሞቱም ወደ ፊት አይቻላቸውም፥ የትንሣኤም ልጆች ስለ ሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።

ማቴዎስ 13:36–43 “በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው። የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት። እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው። መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው; እርሻውም ዓለም (ይህ ዘመን-αἰῶνος) ነው; መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው; እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው; መከሩም የዓለም (የዘመን) መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው። እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም [ዘመን] መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል። የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል; በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።

ማቴዎስ 24:3 “እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው። ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም [ዘመን] መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።

ዕብራውያን 6:4–6 “አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም [ዘመን] ኃይል የቀመሱትን በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው; ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።”

ኤፌሶን 1:20–23 “ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም [ዘመን] ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም [ዘመን] ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል; ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።”

ኤፌሶን 2:1–2; 5-7 “በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ; በእነርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ {περιεπατήσατε κατὰ τὸν αἰῶνα τοῦ κόσμου τούτου:- ይህን ቀጥታ ወደ አማርኛ ብተረጉመው፡- “እንደ እዚህ ዓለም ዘመን በተመላለሳችሁ ጊዜ/ according to the age of this world”} በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው።… ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥ በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን” {ይህን ሲል አሁን ግን የኤፌሶን ሰዎች “በዚህ ዓለም የወዲያኛውን ዘመን ሕይወት” እንጂ የዚህን ዘመን ህይወት አለመሆኑን ይነግራቸዋል። ምንም እንኳ በአሁኑ “በክፉው ዘመን” ብንኖርም ነገር ግን እንደ ክፉው ዘመን ፈቃድ አንመላለስም።}

ገላትያ 1:4–5  “ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም [ዘመን] ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ። ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን; አሜን።”

1 ቆሮንቶስ 10:9–11 “ከእነርሱም አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑት በእባቦቹም እንደ ጠፉ ጌታን አንፈታተን። ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደ ጠፉ አታንጐርጕሩ። ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።

1 ቆሮንቶስ 15:23–28 “ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል; ክርስቶስ እንደ በኩራት ነው፥ በኋላም በመምጣቱ ለክርስቶስ የሆኑት ናቸው; በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል። ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና። የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው; ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን። ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው። ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።”

ስለዚህ አዲስ ኪዳን በሁለት ዘመናት መጋጠሚያ ላይ ያለን ሕዝቦች ነን። ስለዚህ መስቀልና ትንሳኤ; ድካምና ብርታት; ክብርና ውርደት; ለቅሶና መጽናናት ሁለቱም እውነቶች ናቸው። አሮጌው እያለፈ አዲሱ እየፈነጠቀ ነውና! በዚህ በአሁኑ ዘመን ከብዶብን ተስፋችን እንናፍቃለን። ምንም እንኳ የመንፈስን ሕይወት ብንቀበልም ነገርግን ሞች ሰውነታችን ግን በትንሳኤ እስኪለወጥ ሞት በእኛ እየሰራ ነው (ፊል 3፡ 20-21)”

ፊልጵስዩስ 3:20–21  “እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን; እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።”

ሮሜ 8:18–28 “ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ። የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና። ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም; ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው። ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ መኖሩን እናውቃለንና። እርሱም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን የመንፈስ በኵራት ያለን ራሳችን ደግሞ የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅን ራሳችን በውስጣችን እንቃትታለንበተስፋ ድነናልና; ነገር ግን ተስፋ የሚደረግበቱ ነገር ቢታይ ተስፋ አይደለም; የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል? የማናየውን ግን ተስፋ ብናደርገው በትዕግሥት እንጠባበቃለን።  እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል; እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል; ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።  እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።”

2 ቆሮንቶስ 5:1–5 “ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና።  በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና፥ ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም።  በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ፥ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን። ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን። የመጨረሻው ጠላታችን ሞት ነው!”

ሮሜ 8:9–10 “እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም። ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፥ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው።

(The body is dead because of sin: because of the sin of Adam curse of death is working in our body. We are dying each day as a result. However at the same time the Spirit is life (parallel with the body is dead) because of the one righteous act of Christ, the resurrection power of Christ is at work in us through his Spirit. Life is the characteristic of the age to come where as death is the chief characteristic of the present evil age that is under God’s judgement. In summary:- if Christ is in you, on one hand your body is subject to death (NIV) because of the present evil age and on the other hand the life of the age to come (life after the resurrection) is at the same time is working Now in this mortal body. Therefore there is a constant tension between the Sin tainted present evil age (the flesh) and the life giving principle of the age to come coming already in the present (the Spirit).)

© 2013 – 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top