Home / Portfolio / KOG / 008_06 የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግስቱ መገለጥ (Audio)

008_06 የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግስቱ መገለጥ (Audio)

Posted on

የልጁ ሁለቱ ምጽዓቶች የዘመን ፍጻሜ መጀመሪያና መደምደሚያ

 <I’m very sorry for the poor quality of the audio towards the end of the recording. The devise is most probably to be blamed.>

መግቢያ


አሁን የእግዚአብሔር ኪዳናዊ መንግስት በምድር በቤተ-ከርስቲያን አማካይነት ተመስርታለች ነገር ግን ፍጻሜው ግን የነገስታት ንጉስ እስኪመጣ ድረስ ይጠብቃል! በዘልማድ የዘመን መጨረሻ ተብሎ የሚባለው ክርስቶስ ሊመለስ አካባቢ ያለው ዘመንና ሑናቴ ነው። ይህ አስተምሕሮት ግን የዲስፐንሴሽናል እንቅስቃሴ አስተምህሮት ነው። አዲስ ኪዳን ስለ ዘመን መጨረሻ ሲመሰክር የሁለት ዘመናት እውነታዎች መነባበር እንደሆን ይናገራል። የክርስቶስ ወደዚህ ወደ አሁኑ ክፉ ዘመን መምጣቱ የዘላለማዊውን ሐይል በዚህ ክፉ ዘመን ጋር እንዲነባበር አድርጎታል።  ለምሳሌ ሐዋርያው ጳውሎስ “የዘመን ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን” ይለናል።  [/column]

ወይም “ሊመጣ ያለውን ዓለም ኃይል የቀመሱትን ” በማለት ሊመጣ ያለውን “የሚመጣውን ዘመን” ኃይል በዚህ በአሁኑ ክፉው ዘመን ሰዎች ይቀምሳሉ፤ ይህም የሚያመለክተው ሁለቱ መነባበራቸውን ነው! ለዚህ ነው በአለም ሳለን መከራ አለብን ነገር ግን ደግሞ አለምን አሸንፈናል! ይህ መነባበር ነብያት ያላዩት ሚስጢር ሆኖ የቆየ እውነታ ነው። “ሁለቱም እስከ መጨረሻ ይደጉ ተዋቸው!” የሚከተለውን ሰዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ። ይህን በሰፊው በክፍል 008-007 እንመለከታለን። አሁን ግን በመጀመሪያ የመጨረሻው ዘመን ታዲያ ሥንል ምን ማለታችን ነው?Chart-Eschatology

የመጨረሻው ዘመን


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ; ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል (1 ጴጥ 1:3–5)

1 ጴጥ 1:18–21   ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ። ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ፥ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሙታን ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ።

ዕብ 9:25–28  ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም; 26 እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ (ἀπὸ καταβολῆς κόσμου)ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር; አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ (በዘመናት መጨረሻ) (ἐπὶ συντελείᾳ τῶν αἰώνων) ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል። 27 ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥ 28 እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል።

14-15 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።

የመጨረሻው ዘመን በብሉይ ኪዳን


ኢሳ 40:1–5  አጽናኑ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ይላል አምላካችሁ። 2 ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ። 3 የአዋጅ ነጋሪ ቃል። የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ ጥረጉ፥ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካከሉ። 4 ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፥ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል; ጠማማውም ይቃናል፥ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል; 5 የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፥ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፥ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።…

ኢሳ 40:10–12  እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይመጣል ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል; እነሆ፥ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው። 11 መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፥ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፥ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል። 12 ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?…18 እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ? 19 የተቀረጸውንስ ምስል ሠራተኛ ሠርቶታል፥ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፥ የብሩንም ሰንሰለት አፍስሶለታል። …25 እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ? ይላል ቅዱሱ። 26 ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ; እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል; በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም። 27 ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ። መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? 28 አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው; አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። 29 ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። 30 ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ; 31 እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ; እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ; ይሮጣሉ፥ አይታክቱም; ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።

ኢሳ 19:1-23  ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እይበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል; የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።..23 በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር መንገድ ይሆናል፥ አሦራዊውም ወደ ግብጽ፥ ግብጻዊውም ወደ አሦር ይገባል; ግብጻውያንም ከአሦራውያን ጋር ይሰግዳሉ። 24-25 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ሕዝቤ ግብጽ፥ የእጄም ሥራ አሦር፥ ርስቴም እስራኤል የተባረከ ይሁን ብሎ ይባርካቸዋልና በዚያ ቀን እስራኤል ለግብጽና ለአሦር ሦስተኛ ይሆናል፥ በምድርም መካከል በረከት ይሆናል።

ኢሳ 35:2–10 የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ። 3 የደከሙትን እጆች አበርቱ፥ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ። 4 ፈሪ ልብ ላላቸው። እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው…8 በዚያም ጐዳናና መንገድ ይሆናል እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል; ንጹሐንም ያልሆኑ አያልፉበትም፥ ለንጹሐን ግን ይሆናል; ተላላፊዎችና ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም። 9 አንበሳም አይኖርበትም፥ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፥ ከዚያም አይገኙም; የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ; 10 እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ; የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል; ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።

ሰፎንያስ 3:14–16  የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ዘምሪ; እስራኤል ሆይ፥ እልል በል; የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ በፍጹም ልብሽ ሐሤት አድርጊ ደስም ይበልሽ። 15 እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል፥ ጠላትሽንም ጥሎአል; የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ፥ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም። 16 በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም። ጽዮን ሆይ፥ አትፍሪ፥ እጆችሽም አይዛሉ።

አብድዩ 21   21 በዔሳውም ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ አዳኞች ወደ ጽዮን ተራራ ላይ ይወጣሉ; መንግሥቱም ለእግዚአብሔር ይሆናል።

ሚክያስ 4:1–4   በመጨረሻውም ዘመን የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል; አሕዛብም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ። 2 ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው። ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ; እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ። 3 በብዙዎችም አሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ በሩቅም ባሉ በብርቱዎች አሕዛብ ላይ ይበይናል; ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ; ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም ከእንግዲህም ወዲህ ሰልፍ አይማሩም። 4 የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር አፍም ተናግሮአልና ሰው እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ይቀመጣል፥ የሚያስፈራውም የለም።

ኢሳ 52:1–14  ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ; ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ። 2 ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ትቢያን አራግፊ; ተነሺ፥ ተቀመጪ; ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።…7 የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም። አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው። 8 እነሆ፥ ጕበኞችሽ ጮኸዋል; እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ። 9 እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፥እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፥ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፥ በአንድነትም ዘምሩ።…13 እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል; ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል። 14 ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል; 15 ያልተነገረላቸውንም ያያሉና፥ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።

የመጨረሻው ዘመን በአዲስ ኪዳን


ማር 1:2–4  “እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥ 4 ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ…7 ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል። 8 እኔ በውኃ አጠመቅኋችሁ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር። ….14-15 ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።

ሐዋ 3:21–24 21 እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው/ይቆይ ዘንድ ይገባልና። 22 ሙሴም ለአባቶች። ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል; በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት። 23 ያንም ነቢይ የማትሰማው ነፍስ ሁሉ ከሕዝብ ተለይታ ትጠፋለች አለ። 24 ሁለተኛም ከሳሙኤል ጀምሮ ከእርሱም በኋላ የተናገሩት ነቢያት ሁሉ ደግሞ ስለዚህ ወራት ተናገሩ።

ዕብ 9:6–10 ይህም እንደዚህ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ካህናት አገልግሎታቸውን እየፈጸሙ ዘወትር በፊተኛይቱ ድንኳን ይገቡባታል; 7 በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፥ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ስሕተት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም; 8 ፊተኛይቱም ድንኳን በዚህ ገና ቆማ ሳለች፥ ወደ ቅድስት የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል። ይህም ለአሁኑ ዘመን ምሳሌ ነው፥ እንደዚህም መባና መስዋዕት ይቀርባሉ; እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም።

ልጁ እስኪገለጥ ድረስ በምድር ይሰራ የነበረው የእግዚአብሔር መንግሥት እንደጥላ ነበር። አሁን ግን የእግዚአብሔር የሐልወቱ መገለጥ በሆነው በእውነተኛው ንጉስ በኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት መንግሥቱ ተገልጣለች!

ማቴዎስ 11:12–13  “12 ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል። 13 ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ;”

4 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ;

ኤፌ 1:8–10  ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። 9 በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና; 10 በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።..13 እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ; 14 እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።

2 ጢሞ 1:9–11  ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም; ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥ 10-11
አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።

— ——————————————–

© 2013 – 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top