Home / Portfolio / KOG / 008_05 የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግስቱ መገለጥ (Audio)

008_05 የእግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግስቱ መገለጥ (Audio)

Posted on

 

መሲሐዊ ዘመን (ኢሳ 11)

 • አዲስ ዘጸዓት ይገለጣል። እግዚአብሔር ሕዝቡን ከግብጽ እንዳወጣ ለሁለተኛና ለመጨረሻ ጊዜ ህዝቡን ይሰበስባል (Isa 11፡ 11-16)
 • ንግሥናውና አለቅነቱ በምድር ሁሉ ላይ ይሆናል (Dan. 2:44; 7:14, 18, 27; Zechariah 9:9-10; Psalm 72:8-11 ;Heb. 1:8; Rev. 11:15)
 • የእግዚአብሔር መገኘት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መመለስና የቤተ/ መቅደሱ እንደገና በክብር ይሞላል! (Isa 2፡1-4)
 • እግዚአብሔር አዲስ ኪዳን እንደገና ከሕዝቡ ጋር ይገባል; አዲስ ዘጸዓት; አዲስ ኪዳን; አዲስ መንፈስ (Jer 31:21-34; Ezek. 37:26)
 • የእግዚአብሔር መንግሥት በሃይል ትገለጣለች
 • ዓለም አቀፍ ትድግ ይገለጣል
 • ፍጥረት ሁሉ ከሐጥያት; ከሞትና ከአመጽ እጅ ነጻ ሆኖ አዲስ ይሆናል (Isa 65-66; Rev 21-22)

ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (የዳዊት/የእግዚአብሔር ልጅ/ መሢህ ነው)

የሰውን ልጅ ማን ይሉታል…እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው። 16 ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ። …ማቴ 16

ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፥ 22 መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ; የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

ኢየሱስ በሰዎች ዓይን የዮሴፍ የአናጺው ልጅ ቢባልም በአባቱ ዓይን ግን የሚወደው ልጁ ነው›።፡የአብ ምሥክርነት ሦስት የመጽሀፍ ቅዱስ ተስፋ ፍጻሜ ነው። ሆኖም እጅግ አስደናቂ የሚያደርገእው እነዘህ ታላላቅ ተስፋዎች አሁን በአንድ ሰው ላይ መጋጠማቸው ነው። አባቱ ለልጁ ለኢየሱስ ያለበሰው ማንነት በነዚህ ሦስት ማንነቶች ላይ ያተኮረ ነው።

 1. “በአንተ ደስ የሚለኝ”የእግዚአብሔር አገልጋይ ተስፋ በኢሳያስ 40-55 ኢሳ 42፡ 1-9/ ኢሳ 49፡ 1-6/ 50፡ 4-10/ 52፡ 13-53:12። የዚህ አገልጋይ ተል ዕኮውን የሚወጣው በጦር/ በሃይል ሳይሆን በመሰቃየት በመጨነቅ; በመጣልና በመሞት ነው። ይህ አገልጋይ የእግዚአብሔር ሃሳብ በእጁ የምትከናወን የእስራኤልን ተስፋ ፍጻሜ የሚያደርስ
 2. የምወድህ“… ዘፍ 22፡ 2 “2
  የምትወደውን አንድ ልጅህን ይስሐቅን ይዘህ ወደ ሞሪያም ምድር ሂድ; እኔም በምነግርህ በአንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥዋዕት አድርገህ ሠዋው አለ።” ለመስዋዕት የሚቀርበው አባቱ የሚወደው ልጅ።፡አብርሃም የሚወደውን አንድያ ልጁን ሊሰዋ ይስሐቅም አባቱ ሊታዘዝ መስዋዕት እንደሆን ኢየሱስም አባቱ የሚወደው ለብዙዎች መስዋዕት ይሆን ዘንድ የሚቀርብ የመስዋዕቱ በግ ነው። ለይስሐቅ ምትክ አውራ በግ ቢሰጠውም ኢየሱስ ግን በመስቀል ላይ ተተወ። …የመስዋዕቱን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል…ያህዌ ይርዒ ሮሜ 8፡ 32
 3. “አንተ ልጄ ነህ” Ps 2፡ 7 2Sam 7፡ 14; 2 sam 23፡ 1-7; Ps 89; 1-52; Ps 132፡ 10-14 Luke 1፡ 32; Luke 3፡ 22/ ሐዋ 2፡ 30-31; ሐዋ 4፡ 25-28; ሐዋ 13፡ 32-33/ ዕብ 1፡ 5; ዕብ 5፡ 5

Ps 2:7   ትእዛዙን እናገራለሁ; እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።

2 ሳሙ 7:14   እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል; ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ ሰው በሚቀጣበት በትርና በሰው ልጆች መቀጫ እገሥጸዋለሁ;

Ps 132:10–14    11 እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ አይጸጸትምም፥ እንዲህ ብሎ። ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ።

Luke 1:32    እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል;

Luke 3:22    መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ; የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

ሐዋ 4:25–28   በመንፈስ ቅዱስም በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ። አሕዛብ ለምን አጕረመረሙ? ሕዝቡስ ከንቱን ነገር ለምን አሰቡ? 26 የምድር ነገሥታት ተነሡ አለቆችም በጌታና በተቀባው ላይ አብረው ተከማቹ ብለህ የተናገርህ አምላክ ነህ። 27–28 በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።

ሐዋ 13:32–33   እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን; 33 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ። አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና።

ዕብ 1:5    ከመላእክትስ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፥ ደግሞም። እኔ አባት እሆነዋለሁ እርሱም ልጅ ይሆነኛል ያለው ለማን ነው?[/column]

ዕብ 5:5    እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም ነገር ግን። አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ያለው እርሱ ነው;

ኢየሱስና መሲሐዊው ዘመን

ክርስቶስ በምድር ሳለ ያ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይሰጣል የተባለው አዲስ መሲሐዊ ዘመን ፈነጠቀ!

Mark 2:18–22 (AMHB)

18 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጦሙ ነበር። መጥተውም። የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት የሚጦሙት የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጦሙት ስለ ምንድር ነው? አሉት። 19 ኢየሱስም አላቸው። ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጦሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጦሙ አይችሉም። 20 ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፥ በዚያ ወራትም ይጦማሉ። 21 በአረጀ ልብስ አዲስ እራፊ የሚጥፍ የለም; ቢደረግ ግን፥ አዲሱ መጣፊያ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፥ መቀደዱም የባሰ ይሆናል። 22 በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም; ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።

Daniel 9:25 (AMHB)

25 ስለዚህ እወቅ አስተውልም; ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል; እርስዋም በጭንቀት ዘመን ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች።

ማቴዎስ 1:17–18 (AMHB)

17 እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው። 18 የኢየሱስ ክርስቶስም ልደት እንዲህ ነበረ። እናቱ ማርያም ለዮሴፍ በታጨች ጊዜ ሳይገናኙ ከመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።

ሞት ከእግሩሥር መረገጥ ጀመረ (ገና ከሙታን ሳይነሳ!); ሐጥያትን ይቅር ማለት ጀመረ(ማር 2:10) (ገና ደሙን ሳያፈስ!); አጋንንት በታላቅ ሐይል እየጮሁ መውጣት ጀመሩ (ገና በመስቀሉ ድል ሳይጎናጸፍ); የፍጥረት ሐይል ለቃሉ መታዘዝ ጀመረ (ማዕበሉን ጸጥ አደረገ; በውሃ ላይ ተራመደ); በትምህርቱና በሐልወቱ የአዲስ ኪዳንን በረከት ሕዝቡ መቅመስ ጀመረ! በዙሪያው 12 ደ/መዛሙርትን መረጦ ሐዋሪያት ብሎ በመሰየም የአዲስ-ኪዳን ሕዝብ መፈጠሩን አመለከተ። 12 የእግዚአብሔር ሕዝብ ሙላትን ያመለክታል; በቀደመው ኪዳን 12 የእስራኤል ነገድ ሕዝቡ እንዲሆን በፋሲካ በግ ደም እንደተዋጀ; አሁን ደግሞ በገዛ ደሙ የሚዋጃቸውን ሕዝብ ገንዘቡ ያደርግ ዘንድ በፋሲካ ራት “ሲበሉም እንካችሁ ይህ ለብዙዎች ሐጥያት የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ነው!” በማለት ቤተ-ክርስቲያንን መሰረተ (ሐዋ 20)።

Romans 1:1–4 (AMHB)

1-2 ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ። 3-4 ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው; እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ማቴዎስ 28:18–20 (AMHB)

18 ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። 19-20 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው; እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

Hebrews 10:12–22 (AMHB) ንግስና; ክሕነት; መሥዋዕት; አዲስ ኪዳንና መቅደስ

12 እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፥ 13 ጠላቶቹም የእግሩ መረገጫ እስኪደረጉ ድረስ ወደ ፊት ይጠብቃል። 14 አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና። 15-16 መንፈስ ቅዱስም ደግሞ ስለዚህ ይመሰክርልናል; ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ; በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ 17 ብሎ ከተናገረ በኋላ፥ ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውንም ደግሜ አላስብም ይላል። 18 የእነዚህም ስርየት ባለበት ዘንድ፥ ከዚህ ወዲህ ስለ ኃጢአት ማቅረብ የለም። 19-20 እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥ 21 በእግዚአብሔርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ካህን ስላለን፥ 22 ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ;

[/column-group]


© 2013 – 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top