Home / Portfolio / Articles / የደቀ መዝሙርነት ዓላማ፤ ምንነትና ሕይወት

የደቀ መዝሙርነት ዓላማ፤ ምንነትና ሕይወት

Posted on

ማቴዎስ 28:16–20

አሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ኢየሱስ ወዳዘዛቸው ተራራ ወደ ገሊላ ሄዱ፥  ባዩትም ጊዜ ሰገዱለት፤ የተጠራጠሩ ግን ነበሩ።  ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው። ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።  እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።

 • ሒደት አመልካች ቃሎች፡ እየሔዳችሁ….እያጠመቃችኋቸው…እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው

 • ሥልጣን “ሁሉ“…አሕዛብን “ሁሉ…ያዘዝኋችሁን “ሁሉ“…

 • ለዚህ መሔድ መንስኤ፡ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ”..እንግዲህ

 • ይህ ኢየሱስ ከሙታን ከመነሳቱ በፊት ሥልጣን አንዳልነበረው አያመለክትም፤ በዚሁ ወንጌል በተደጋጋሚ የክርስቶስ ሥልጣን ትኩረት ተሰጥቶበታል::

A.  በሥጋው ወራት ኢየሱስ:

 • በትምህርቱ ሥልጣን እንደነበረው ማቴ 7:28–29 ኢየሱስም ይህን ነገር በጨረሰ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፤ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና።

 • በርኩሳን መናፍስት ላይ በደዌና በሕማም ሁሉ ሥልጣን እንደነበረው:  ማቴ10:1: አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው።

 • ልጅ ከመሆኑ የተነሳ ሥልጣን እንደነበረው  ማቴ11:27:   ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።

 • ጌተ ከመሆኑ የተነሳ ሥልጣን እንደነበረውማቴ22:41–45  ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ። ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት።  እርሱም። እንኪያስ ዳዊት። ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?  ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው። ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው።

 • ቃሉ የእ/ ቃል በመሆኑ ሥልጣን እንደነበረውማቴ24: 35; ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም።

 • ዮሐ 17:1–2 ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ። አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው።

B.  ከትንሳኤ ባሻገር ያለው ሥልጣን

 • ይህ ልዩነት የተመሰረተው ግን ሥልጣኑ የተንሰራፋበት የክልል ገደብ መነሳቱ ነው።

 • የኢየሱስ አገልግሎት ያተኮረው በጠፉት የእስራኤል በጎች ዙሪያ ነበር

 • ምንም እንኳ እ/ር የምድር ሁሉ ንጉስ ቢሆንም ነገር ግን ምድር ሁሉ ከ እ/ር ጋር የቃል ኪዳን ውስጥ አልገባችም፤ ያም ምድር ሁሉ ደህንነት በሰፈነበት ሥልጣኑ ሥር ሳይሆን በልዑል አገዛዙ ሥር ነበረች አሞ 3: 1-2

 • ነገር ግን እ/ር አህዛብን እንደሚያጸድቅና ወደዚህ ደህንነት ወዳለበት የቃል ኪዳን ክልል ውስጥ እንደሚያስገባ አስቀድሞ በማየት ለአብርሃም  “በአንተ የምድር ወገኖች ይባረካሉ ሲል ወንጌልን ሰበከለት” Gal 3: 8

 • ይህም ወንጌል ሲጀምር የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።

 • ከዚህ የተነሳ አዲስን ቃል ኪዳን መስርቷል፡ “ከዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፥ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።  እያንዳንዱም ጐረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን። ጌታን እወቅ ብሎ አያስተምርም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና።”

 • ማቴ 26:28–29:ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።  ነገር ግን እላችኋለሁ፥ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር ከዚህ ከወይን ፍሬ አዲሱን እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ ከዛሬ ጀምሬ አልጠጣውም።

 • ግን አሁን ከትንሳኤው ባሻገር ከመስቀሉ ሥራና ከትንሳኤው ሐይል የተነሳ የክርስቶስን ሥልጣን ድንበርመጠቅ አድርጎታል

C.  ይህም ሥልጣን ከአባቱ የተቀበለው ሥልጣን ነው፡

ፊል 2 5-11 እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥  በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።  በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤  ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉበኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

ራዕ 5:2–5ብርቱም መልአክ። መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው? ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።  በሰማይም ቢሆን በምድርም ላይ ቢሆን ከምድርም በታች ቢሆን መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው ማንም አልተቻለውም።  መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ።  ከሽማግሌዎቹም አንዱ። አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።….Revelation 5:12–13  በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ። በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ። በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ

ራዕ 11:15–16: የዓለም መንግሥት የጌታችንና የእርሱ የክርስቶስ ሆነች፥ እርሱም ከዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል

D.  ለማጠቃለል፡

 • ይህ ሥልጣን ኢየሱስ የእሥራኤል መሲህ ብቻ ሳይሆን አሁን ይህ ሥልጣኑ የአሕዛብም ጭምር መሆኑን ያሳያል፤

 • አዲስ መሲሃዊ ዘመን ፈንጥቋል። ይህ የአሁኑ ዘመን አርጅቷል ሊያልፍም ተቃርቧል። አዲስ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ መጥቷል;

 • ይህ ዘመን ክርስቶስ ከሰማያዊው ሥፍራ ከአባቱ ቀኝ ሆኖ የሚገዛበት ዘመን ነው።

 • የክርስቶስን ሥልጣን ድንበር መጠቅ ከመሆኑ የተነሳ ለደ/መዛሙርቱም ድንበር መጠቅ ተልዕኮ ሰጥቷቸዋል.

 • የዚህ ተልዕኮ ያነጣጠረው አሕዛብ ሁሉ ላይ ነው without racial distinction

© 2013 – 2014, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top