Home / ትምህርተ መለኮት/ Theology / ትምህርተ ክርስቶስ / የክብር ጎዳና፡ ሕልወተ-ክርስቶስና የመስቀሉ ተልዕኮ

የክብር ጎዳና፡ ሕልወተ-ክርስቶስና የመስቀሉ ተልዕኮ

Posted on

(This is my sermon manuscript preached on 09/09/2012. The actual audio sermon is posted here)

በበዓሉም ሊሰግዱ ከወጡት አንዳንዶቹ የግሪክ ሰዎች ነበሩ፤ 21 እነርሱም ከገሊላ ቤተ ሳይዳ ወደሚሆን ወደ ፊልጶስ መጥተው። ጌታ ሆይ፥ ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ብለው ለመኑት። 22 ፊልጶስም መጥቶ ለእንድርያስ ነገረው፤ እንድርያስና ፊልጶስ መጥተው ለኢየሱስ ነገሩት። 23 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል4 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች። ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል። 26 የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፥ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል።7 አሁን ነፍሴ ታውካለች ምንስ እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚህ ሰዓት አድነኝ። ነገር ግን ስለዚህ ወደዚህ ሰዓት መጣሁ። አባት ሆይ፥ ስምህን አክብረው። ስለዚህም። አከበርሁት ደግሞም አከብረዋለሁ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። 29 በዚያ ቆመው የነበሩትም ሕዝብ በሰሙ ጊዜ። ነጐድጓድ ነው አሉ፤ ሌሎች። መልአክ ተናገረው አሉ። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል። ይህ ድምፅ ስለ እናንተ መጥቶአል እጂ ስለ እኔ አይደለም። 31 አሁን የዚህ ዓለም ፍርድ ደርሶአል፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዥ ወደ ውጭ ይጣላል፤ 32 እኔም ከምድር ከፍ ከፍ ያልሁ እንደ ሆነ ሁሉን ወደ እኔ እስባለሁ። 33 በምን ዓይነትም ሞት ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲያመለክታቸው ይህን ተናገረ። እንግዲህ ሕዝቡ። እኛስ ክርስቶስ ለዘላለም እንዲኖር ከሕጉ ሰምተናል፤ አንተስ የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ይል ዘንድ እንዲያስፈልገው እንዴት ትላላህ? ይህ የሰው ልጅ ማን ነው? ብለው መለሱለት።

 • ምልክት
  • ምልክቶቹ የሚያመላክቱትን  ማወቅ ኢየሱሱን ማወቅ ነው
  • አልዓዛርንም ከመቃብር ጠርቶ ከሙታን ሲያስነሣው ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝብ ይመሰክሩለት ነበር። 18 ስለዚህ ደግሞ ሕዝቡ ይህን ምልክት እንዳደረገ ስለ ሰሙ ሊቀበሉት ወጡ።
  • ህዝቡ ኢየሱስን ሊቀበለው የወጣው ምልክት ስላዩ ነበር። ምክንያቱም የአልዓዛር ከሙታን መነሳት ስለ ክርስቶስ ህልውናና ተልዕኮ የሚጠቁም አመላካች ነበርና።
  • በዮሐንስ ወንጌል ዮሐንስ ኢየሱስ የደረጋቸውን ድንቆች ምልክቶች ወይም ሥራዎች ይላቸዋል።
   • ዮሐ 20፡ 30-3130 ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ 31 ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ
    የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።
  • ምልክቶቹ የተሰጡበት ዓላማ አንባቢው፡ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ
   የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ ውጤቱም በስሙ የዘላለምሕይወት ይሆንልን ዘንድ ነው
  • መንፈሳዊ ብስለትና የዘላለማዊ ሕይወት መሰረት የእ/ርን ልጅ
   ኢየሱስን ማወቅ ነው፡፡ 
  • ዘላለማዊ ሕይወት ኢየሱስ ሲገለጥ ዕውን የሚሆነው የመጪው ዘመን ሕይወት ማለት (The Life of the age to come, “zoe-aionios”- literally means “the life of the age”) 
   • ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥ 30 አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም/ዘመን የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።31 ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።” ማር 10፡ 30-31
  • ዮሐ 17፡ 3
   3 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። ይህ ሕይወት የሚሰራው ዕለት ዕለት ክርስቶስን በማወቅ ነው። ይህም የክርስቶስን ህልውናና ተልዕኮ ማወቅ ነው።
  • ዮሐ 17፡4 “እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ”

 • በአባቱ ዘንድ የተወደደ ልጅ ነው

  ኢየሱሱን ማወቅ የተወደደ ልጅ መሆኑን ማወቅ ነው

  • ዮሐንስ 5:20 አብ ወልድን ይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።
  • ዮሐንስ 3:35 አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።
  • ዮሐንስ 15:9 አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።
  • ዮሐንስ 17:23–24 አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።
  • ዮሐንስ 17:26 እኔንም የወደድህባት ፍቅር በእነርሱ እንድትሆን እኔም በእነርሱ፥ ስምህን አስታወቅኋቸው አስታውቃቸውማለሁ።
 • ከአባቱ ዘንድ የተላከ ልጅ ነው
  • ኢየሱሱን ማወቅ የተላከ ልጅ መሆኑን ማወቅ ነው (እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ
   ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።
    
  • ዮሐንስ 4:34 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው። የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
  • ዮሐንስ 5:23–24 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።
  • ዮሐንስ 5:30 እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።
  • ዮሐንስ 5:37 የላከኝ አብም እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል። ድምፁን ከቶ አልሰማችሁም፥ መልኩንም አላያችሁም፤
  • ዮሐንስ 6:38–39 38 ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና። 39 ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው።
  • ዮሐንስ 6:57 ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል።
  • ዮሐንስ 7:16 ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው። ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤
  • ዮሐንስ 7:18 ከራሱ የሚናገር የራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላከውን ክብር የሚፈልግ ግን እርሱ እውነተኛ ነው በእርሱም ዓመፃ የለበትም።
  • ዮሐንስ 7:28 እንግዲህ ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር። እኔንም ታውቁኛላችሁ ከወዴትም እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ እኔም በራሴ አልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው፤
  • ዮሐንስ 7:33 ኢየሱስም። ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ ወደ ላከኝም እሄዳለሁ።
  • ዮሐንስ 8:16 የላከኝ አብ ከእኔ ጋር ነው እንጂ ብቻዬን አይደለሁምና እኔ ብፈርድ ፍርዴ እውነት ነው።
  • ዮሐንስ 8:18 ስለ ራሴ የምመሰክር እኔ ነኝ፥ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።
  • ዮሐንስ 8:26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ አላቸው።
  • ዮሐንስ 8:29 የላከኝም ከእኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም አላቸው።
  • ዮሐንስ 9:4 ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።
  • ዮሐንስ 12:44–45 ኢየሱስም ጮኸ፥ እንዲህም አለ። በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤ 45 እኔንም የሚያይ የላከኝን ያያል።
  • ዮሐንስ 12:49 እኔ ከራሴ አልተናገርሁምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ።
  • ዮሐንስ 13:20 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ማናቸውን የምልከውን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
  • ዮሐንስ 14:24 የማይወደኝ ቃሌን አይጠብቅም፤ የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።
  • ዮሐንስ 16:5 አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም። ወዴት ትሄዳለህ? ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።
  • ዮሐንስ 16:7 እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ። (ኢየሱስ ከአባቱ ዘንድ እንደመጣ፤ አባቱ የሰጠውን ፈቃድ በመፈጸሙ ደግሞ ቀድሞ ወደነበረበት መመለሱ እንደገና ሌላ መልዕክተኛ እንዲመጣ ያደርጋል! መምጣቱም መሔዱም በረከት ነው! ይህንንም በዮሐንስ ወንጌል በመደጋገም ወንጌላዊው ‘ኢየሱስ ገና አልከበረም ነበርና’..በሚል ተደጋጋሚ ሐረግ እናስተውላለን)
  • ዮሐንስ 17:3 እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ
   ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።
  • ዮሐንስ 17:8 የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።
  • ዮሐንስ 17:18 ወደ ዓለም እንደ ላክኸኝ እንዲሁ እኔ ወደ ዓለም ላክኋቸው፤
  • ዮሐንስ 17:21 ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ።
  • ዮሐንስ 17:23 እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል።
  • ዮሐንስ 17:25 ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላወቀህም፥ እኔ ግን አወቅሁህ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አወቁ፤

  የተልዕኮው አላማ 4ቱ ገጽታዎች

  • የዘላለምን ሕይወት መስጠት፡ ዮሐ 5:21፡ 26/ 3፡ 35/ 6:40፤ 47/ 10፡ 10
  • የእ/ር አብን ክብር በትምርቱና በሥራው መግለጥ፡ ዮሐ 1፡ 18/ 14፡ 6-7
  • በእርሱ ላላመኑትና ተልዕኮውን ባልተቀበሉ ላይ የሞትን ፍርድ፤ ላመኑት ደግሞ የዘላለም ሕይወትን ፍርድ ምክኒያት ለመሆን 5፡ 22-23
  • ለመስቀል ሞት ለመታዘዝ፡ 12፡ 23-24
 • የግሪክ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መምጣት፡
  • ከገሊላ ቤተ ሳይዳ ወደሚሆን ወደ ፊልጶስ መጥተው። ጌታ ሆይ፥ ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን ብለው ለመኑት።”
  • ሥጋ የሆነው ቃል የእስራኤል መሲህ ሆኖ ሲገለጥ የገዛ ወገኖቹ አልተቀበሉትም…ዓለሙም አላወቀውም።
  • እግዚአብሔር ለአብርሃም በአንተ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ ሲል፤ የአብርሃም ጥሪ ለአሕዛብ መዳን እንደሆን ወንጌልን አበሰረለት።
  • “እግዚአብሔር አለኝ። አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ። 8 ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።”
  • የእነዚህ የግሪክ ሰዎች (አሕዛብ) ኢየሱስን መፈለጋቸው፤ ለኢየሱስ አባቱ የቀጠረለት ሰዓት እንደደረሰ ምልክት ሆነለት! የአሕዛብ መዳን በደጅ ነው! ይህም መዳን አሁን በደረሰችው ሰዓት እርሱ ራሱን መስዋዕት ሆኖ ባቀረበበት ሥራ የሚገኝ መዳን ነው።
 • ሰዓት፦

  ኢየሱሱን ማወቅ ከአባቱ ዘንድ ተለኮ የፈጸመውን ሥራ ማወቅ ነው

  በእነዚህ ክፍሎች የሰዓቱን እንቅስቃሴ እንመለከት። ሰዓቱ ገና ወደፊት ከመሆን (ዮሐ 2:4፤ 4:21፤ 8:20፤) አሁን እየደረሰ እንደሆን (ዮሐ12:23) በመጨረሻም አንደደረሰ (13:1፤ 17:1)

  • ዮሐንስ 2:4 “ኢየሱስም። አንቺ ሴት፥ ከአንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም አላት።
  • ዮሐንስ 4:21 “ኢየሱስም እንዲህ አላት። አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል።
  • ዮሐንስ 8:20 20 “ኢየሱስ በመቅደስ ሲያስተምር በግምጃ ቤት አጠገብ ይህን ነገር ተናገረ፤ ጊዜው ገና አልደረሰምና ማንም አልያዘውም።
  • ዮሐንስ 12:23 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። የሰው ልጅ ይከብር ዘንድ ሰዓቱ ደርሶአል
  • ዮሐንስ 13:1 “ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ በዚህ ዓለም ያሉትን ወገኖቹን የወደዳቸውን እስከ መጨረሻ ወደዳቸው።
  • ዮሐንስ 17:1 “ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ። አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ፥ በሥጋም ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው።

© 2013, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like 1 People Liked this
avatar

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top