Home / Portfolio / WOG / ክፍል 4 – 6፡ እግዚአብሔርና ቃሉ፦ የሚናገር አምላክ

ክፍል 4 – 6፡ እግዚአብሔርና ቃሉ፦ የሚናገር አምላክ

Posted on

(This is the note for the audio series. )

መጽሀፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ነገርግን የእግዚአብሔር ቃል ብለን ሥንል ከተጻፈው ቃል ሰፋ ያለ ሀሳብን ያዘለ እውነት ነው። ቃለ-እግዚአብሔር ስንል፡ እግዚአብሔር ከዘላለም ጀምሮ ይናገር የነበረውን፣አሁን የሚናገረዉን፤ ደግሞም ወደፊት የሚናገርውን ይጨምራል ። የእግዚአብሔር ሥሉስነት ዘላለም እስከሆነ ዘንዳ፤ በሕላዌያት መካከል ንግግር ነበር ማለት ነው። ይህ ለመረዳት እጅግ ታላቅ የሆነውም ሚስጢርም እንኳ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ለምሳሌ፤ እግዚአብሔር ከነቢያቱ ጋር የተነጋገረው ሁሉ አልተጻፈም፤ እንደዚሁም figure1ከመላእክቱም ጋርም (መዝ 103:20)። ሐዋሪያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ቤ/ያን የጻፋቸው ሁለት ተጨማሪ ደብዳቤዎች ነበሩ (1ቆሮ 5፡ 9፤ 2ቆሮ 2:4) እንደዚሁም ጌታችን ኢየሱስ በምድር ያስተማረው፤ የሰራውና የተናገርው ሁሉ እንዳልተጻፈ ሐዋርው ዮሐንስ ግልጽ አድርጎ ነግሮናል። ምንም እንኳ እነዚህ ቃሎች አሁን መስማት ባንችልም ፤ ቁምነገሩ ግን ቃለ-እግዚአብሔር ስንል መጽሀፍ ቅዱስን ብቻ ማለታችን አይደለም። ምንም እንኳ መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ከተናገራቸው ‘ቃሎች’ መካከል አንደ አንዱ ቢሆንም (ይህን በሰፊው በክፍል ሦስት እንዳስሣለን-under Inspiration) ቃለ-እግዚአብሄር ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም ። ለምሳሌ ያህል መዝ 147:13–20 እንመልከት፡፡ ቃል በተጠቀሰበት ቦታ ሁሉ ላይ መጽሀፍ ቅዱስ የሚለውን ተክተን ብንመለከት ልዩነቱ ግልጽ ሆኖ ይታየናል!

ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በዪ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና። 14 በወሰንሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ። 15 ነገሩን (ተዕዛዙን) ወደ ምድር ይሰድዳል፥ ቃሉም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል። 16 አመዳዩን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፤ ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፤ 17 በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፤ በበረዶውስ ፊት ማን ይቆማል? 18 ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፤ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል። 19 ቃሉን ለያዕቆብ፥ ሥርዓቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይናገራል። 20 ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም። ሃሌ ሉያ። (መዝ 147:13–20).

ቁ.15 የእግዚአብሔርን የመግቦት ሥራ ይገልጻል:: ይህም በአፉ ቃል (የተጻፈውን ቃል አይደለም) ክረምትና በጋ እንዲፈራረቅ ይቆጣጠራል። ቁ.18 ግን የተጻፈውን የሕግ መጽሀፍ (ቃል) ያመለክታል። መዝሙረኛው እጅግ ጥልቅ ሚስጢርን ያስተምረናል። ይሀውም ፍጥረትን በቃሉ ሐይል የሚያስተዳድረው አምላክ: ለእስራኤል በተለይ በህጉ መጽሐፍ በኩል ተናግሯታል (ሥለዚህ በክፍል አምስት በሰፊው እንነጋገራለን – the scripture as the media of the Word of God)። መዥሙረኛው በዚህ የህጉ መጽሐፍ አማካይነት እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት መንገድ እንደሆን ይነግረናል! “ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም”. ሌላ ምሳሌ እንመልከት

በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።

(በመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ነበረ፥ መጽሐፍ ቅዱስም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ መጽሐፍ ቅዱስም እግዚአብሔር ነበረ።) ይህም ምንም አይነት ስሜት አይሰጥም። ለምን? ምክኒያቱም ቃለ-እግዚአብሔር ብለን ስንል ሰፊ ስለሆነ ነው።፡ነገር ግን ለጥናታችን ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነገር መጽሀፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑ ነው! እግዚአብሔርን የምናውቅበት፤ መልካሙን ከክፉ የምንለይበት የተገለጠውን ቃል የምናገኘው በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው! ይህ ወደ ፊት እንደምንመለከተው ሐዋርያው ዮሐንስ በክርስቶስ የመጣውን የመገለጥ ድምዳሜ ከዚህ ቀደም በሕግና በነብያት ከተገለጠው ጋራ ሲያነጻጽር “የሕይወት ቃል” ይለዋል ይህንም ‘ከተጻፈው ቃል” ጋር ማወዳደሩ ነው። ስለተጻፈው ቃል ግን ሲናገር “ወንድሞች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረቻችሁ አሮጌ ትእዛዝ እንጂ የምጽፍላችሁ አዲስ ትእዛዝ አይደለችም፤ አሮጌይቱ ትእዛዝ የሰማችኋት ቃል ናት። ዳግመኛ አዲስ ትእዛዝን እጽፍላችኋለሁ፥ ይህም ነገር በእርሱ በእናንተም እውነተኛ ነው፤” ምክኒያቱም “ጨለማው እያለፈና እውነተኛውም ብርሃን” እየበራ ስለሆነ ነው። ይህ አንባቢው አስተውሎ ሊመለከተው የሚገባ እውነት ነው። በአንድ መልኩ ዮሐንስ የሚጽፈው በቅዱሳት መጽሐፍ አስቀድሞ የተገለጠ ነው። አዲስ ነገር አይደለም:: ነገር ግን አሁን የሕይወት ቃል የተጻፈውን ቃል ተከትሎ ስለመጣ (ጨለማው እያለፈ ደግሞ ብርሃኑ እይበራ ስለሆነ) ከዚህ በፊት የተገለጠውን በአዲስ መነጽር እንድንመለከት ያደርገናል። በእቅፉ ከአባቱ ዘንድ የነበረው ልጁ መምጣቱ ከዚህ ቀደም የተሰጠውን መገለጥ መጥቆ፤ በአዲስ መንፈስ መረዳት ፈሶልናልና!

ይህን ካልን የእግዚአብሔር ቃል ስንል ምን ማለታችን ነው? ይህንን ለመመለስ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ማነው የሚለውን እንመልስ.

እግዚአብሔርና ማንነቱ

እግዚአብሔር በባህርይው የሚናገር አምላክ ነው። መናገር ለሕልውናው መሰረታዊ ነው። እግዚአብሔር ከዘላለም እስከለዘላለም በንግግር ውስጥ አለ። ይህ ዘላለማዊ ክሕለት የእግዚአብሔርን ህልውና ከሌሎች ሁሉ እንዲለይ ያደርገዋል። ሥለ እግዚአብሔር ማንነት ስንነጋገር አንደ ምሶሶ ሆነው ሊረዱን የሚችሉ ሦስት የእግዚአብሔር ማነነቶች አሉ። እነዚህም፡ የእግዚአብሔር ምጡቅነት (Transcendence)፤ ሉዓላዊነት (Sovereignty)ና ሕላዌነት (Personality) ናቸው::

እግዚአብሔር ምጡቅነት (God’s Transcendence)፡ ልቀትና ርቀት

 • እግዚአብሔር በራሱ-ምሉዕና በራሱ የሚኖር አምላክ ነው(God’s Independence) በሰው አይገለገልም። ፍጥረትንም ስለሚያስፈልገው አልፈጠረም። ሐዋ 17፡ 24-25፤ ኢዮ 41፡ 11. መዝ 50፡ 10-11፤ በዘላለም ከልጁ ጋርና ከመንፈሱ ጋር በፍጹም ሕብረት ይኖር የነበረ በራሱ ምሉዕ የሆነ አምላክ ነው (ዮሀ 17:5)። ሕልውናውን ከማንም አልተርከበም- እርሱ ግን ህይወት ላለው ነገር ግን መሰረት ነው። ራዕ 4፡ 11፤ ሮሜ 11:35-36፤ 1 ቆሮ 8:6፤ ሆኖም ግን ይህ ማለት እግዚአብሄር ለፍጥረቱ ግድ የለውም ማለት አይደለም። ኤፌ 1፡ 11-12፤ ኢሳ 43:7፤ 62:3-5 በህዝቡ ደስ ይሰኛል!
 • እግዚአብሔር ዘላለማዊ አምላክ ነው፡ (God’s Eternality)”1 አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን። 2 ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ። Ps 90:1–2; ሆኖም ግን እግዚአብሔር በዘመን መካከል ቀን ቀጥሮ ይሰራል ይገለጥማል።
 • እግዚአብሔር አይለወጥም፡ (God’s un-changeableness/ Immutability) በፈቃዱ፤ በሃሳቡ፤ በዕቅዱ፤ በፍጹምነቱ፤ በባሕሪይው፤ በቃሉ…ያው ነው መዝ 102:25-27። አዲስ ነገር አይማርም።፡አስቀድሞ አይቶም አይወስንም።፡ 16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን። 1 Ti 6:16 “ብቻውን አምላክ ለሚሆን ለማይጠፋው ለማይታየውም ለዘመናት ንጉሥ ምስጋናና ክብር እስከ ዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።”1 Ti 1:17.
 • እግዚአብሔር ወሰን የለሽ አምላክ ነው፡(God’s Omnipresence) መዝ 139:7-10

የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት

 • እግዚአብሔር የሁሉ ጌታ ነው፡ (Covenant Lordship) እግዚአብሄር ንጉሥ ነው። መንግስቱም የሰፈነው በሁሉም ላይ ነው። በሁሉ ላይ ልዕልናው ግድ የሆነው ምክኒያቱም ሁሉን የሰራና ያበጀ እርሱ ስለሆነ ነው። ፍጡር ሁሉ ምስጋና ለአምላክነቱ ዕውቅና ለመስጠት የፍጡርነት ግዴታ አለበት። የእ/ር ልዕልና መ.ቅ. በሁለት ያስቀምጠውዋል፡
  • ሉዓላዊ መንግስት፡ “መንግስቱ ሁሉን ትገዛለች“፡- ሁሉም በመንግስቱ ሥር ነው
  • ኪዳናዊ መንግስት፡ “ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው።

 • እግዚአብሔር ባለሥልጣን ነው: (Authority) በቃሉ ሲናገር ሆነ ሲሰራ ፈቃዱን አማክሮ እምጂ ሰውን አማክሮ አይሰራም “እንደፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሰራ– ኤፌ 1:9-11″። ስለሚሰራውም ነገር ማን ለምን እንዲህ ታደርጋለህ የሚለው የለም። የሥልጣን የመጨረሻ ጣራ እግዚአብሔር ነው።
  • ስለ ራሱን ይሚስመሰክ ራሱ ነው። “ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ፥ በራሱ ማለ
  • ነገር ግን፥ አንተ ሰው ሆይ፥ ለእግዚአብሔር የምትመልስ ማን ነህ? ሥራ ሠሪውን። ስለ ምን እንዲህ አድርገህ ሠራኸኝ ይለዋልን? 21 ወይም ሸክላ ሠሪ ከአንዱ ጭቃ ክፍል አንዱን ዕቃ ለክብር አንዱንም ለውርደት ሊሠራ በጭቃ ላይ ሥልጣን የለውምን?
  • “ከጠሪው እንጂ ከሥራ ሳይሆን በምርጫ የሚሆን የእግዚአብሔር አሳብ ይጸና ዘንድ፥ ለእርስዋ። ታላቁ ለታናሹ ይገዛል ተባለላት።”
 • እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ይቆጣጠራል (Control)፡እግዚአብሔር የገዛ ራሱ-ሹምና ምስክር ነው (Self-Governing; self-justifying)፡
  • የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። 34 የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው? 35 ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው? 36 ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
 • የእግዚአብሔር ሕላዌነት (God’s Person-hood)፡ (ቅርበትና መገኘት)

  • ምንም እምንኳ እግዚአብሔር ከምናውቀው በላይ ምጡቅ ቢሆንም፤ ምንም እንኳ ስለ እግዚአብሔር የምንናገረለት አንዲቷም ቃል እንኳ ፍጹምበፍጹም ሊገልጸው ባይችልም፤ ሥለ እግዚአብሄር ያለን መረዳት ግን እውነትና እርግጥ ነው።
  • ምንም እንኳ ምጡቅ ከመሆኑ የተነሳ በፍጥረቱ ተጸዕኖ ሥር ባይሆንም፤ ነገርግን እንደህላዌ ነቱ ያዝናል፤ ይደሰታል፤ ይገለጣል፤ ከሰዎችና ከፍጥረቱ ጋር ኪዳናት ይገባል።
  • ለዚህ ጥናታችን ወሳኝ ማንነቱ ሕላዌ መሆኑ ነው። ምክኒያቱም እንደ ህላዌነቱ፡
   •  እግዚአብሔር የሚናገር አምላክ ነው።
   • እግዚአብሔር ሥሉስ አምላክ ነው
  • ዘጸ 2፡ 24-25፦ 24 እግዚአብሔርም የለቅሶአቸውን ድምፅ ሰማ፥ እግዚአብሔርም ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አሰበ። 25 እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልጆች አየ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ያለውን ነገር አወቀ።
   • የእግዚአብሔርን ሕላዌነት ለማረጋገጥ የገቡ አራት ቃሎች፦ ሠማ፤ አሰበ፤ አየ፤ አወቀ
  • ዘጸ 3፡ 4-10፦  እግዚአብሔር እርሱ ይመለከት ዘንድ እንደ መጣ ባየ ጊዜ እግዚአብሔር ከቍጥቋጦው ውስጥ እርሱን ጠርቶ። ሙሴ፥ ሙሴ ሆይ አለ። 5 እርሱም። እነሆኝ አለ። ወደዚህ አትቅረብ፤ አንተ የቆምህባት ስፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ አለው። 6 ደግሞም። እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን ሸፈነ። 7 እግዚአብሔርም አለ። በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ፤ 8 ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ። 9 አሁንም እነሆ የእስራኤል ልጆች ጩኸት ወደ እኔ ወጣ፤ ግብፃውያንም የሚያደርጉባቸውን ግፍ ደግሞ አየሁ። 10 አሁንም ና፥ ሕዝቤን የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ታወጣ ዘንድ ወደ ፈርዖን እልክሃለሁ።
   • ሙሴ ሊያይ መጣ ነገር ግን የሚታይ ሳይሆን በፈንታው ሰማ። የማይታይ ነገር ግን የሚያይ፤ የሚሰማ፤ የሚያስታውስና የሚወርድ።
  • “እርሱም። በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ….ስሙስ ማን ነው? ባሉኝ ጊዜ፥ ምን እላቸዋለሁ? አለው። 14እግዚአብሔርም ሙሴን። <<ያለና የሚኖር-እኔ >> እኔ ነኝ አለው፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች። <<ያለና የሚኖር-እኔ>>ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው። 15 እግዚአብሔርም ደግሞ ሙሴን አለው። ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ። የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ “እግዚአብሔር” -ወደ እናንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው፥ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።””እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረው ጀምሮ፥ ከሰማይ ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ከቶ እንዲህ ያለ ታላቅ ነገር ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰምቶ እንደሆነ ከአንተ በፊት የነበረውን የቀደመውን ዘመን ጠይቅ።  አንተ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደ ሰማህ፥ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ በሕይወት ይኖራልን? ” Dt 4:32-33“እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው አለውም። እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ 3 ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ ፤ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር (አስተርእዮ)።…እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከግብፃውያንም ባርነት አወጣችኋለሁ፥ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ፥ 7 ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፥ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። 8 ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እሰጣት ዘንድ ወደ ማልሁባት ምድር አገባችኋለሁ፤ እርስዋንም ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። Ex 6:2; 6–9.
   • እኔ ነኝ (አኅያህ) = ያህዌ (እግዚአብሔር)
   • እግዚአብሔር፦ የመጠሪያ ሥም እንጂ ማዕረግ አይደለም።
   • ኤሎሂም አምላክ/ ፈጣሪነቱን ሲያሳይ፤ አዶናይ ደግሞ ገዢነቱን ያሳያል
   • እግዚአብሔር (እኔነኝ) ግን የዚህ የሁሉን ቻይ አምላክ የግል መጠሪያው ነው (ለምሳሌ ያህል “እኔ ‘ሳምሶን’ ነኝ”)
  • ሥለዚህ አምላካችን ዓላማው ስሙን (Name represents the person in Biblical thought) – ይህም ሕላዌነቱን – ለዓለም ማስተዋወቅ ነው። “አምላክ እግዚአብሔር ነው!” ዘዳ 4፡ 33-35/ 5፡23
  ጸአት 5:2
  ፈርዖንም።ቃሉን እሰማ ዘንድ እስራኤልንስ እለቅቅዘንድ እግዚአብሔር ማንነው? እግዚአብሔርን
  አላውቅም፥እስራኤልንም ደግሞአልለቅቅም አለ። 
  ዘጸአት 6:7 ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፥አምላክምእሆናችኋለሁ፤እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።ዘጸአት 7:5 ግብፃውያንም፥እጄን በግብፅላይ በዘረጋሁጊዜ፥የእስራኤልንም ልጆች ከመካከላቸው ባወጣሁ ጊዜ፥
  እኔእግዚአብሔር እንደ ሆነሁ ያውቃሉ።
  ዘጸአት 6:7ለእኔምሕዝብእንድትሆኑእቀበላችኋለሁ፥አምላክምእሆናችኋለሁ፤እኔምከግብፃውያንባርነት
  ያወጣኋችሁእግዚአብሔር አምላካችሁእንደሆንሁታውቃላችሁ።
  ዘጸአት 6:1–2 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው።በጸናች እጅ ይለቅቃችኋልና፥በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ
  ይሰድዳቸዋልና አሁን በፈርዖን የማደርገውን ታያለህ። 2 እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው
  አለውም።እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤

  ዘጸአት 7:17 እግዚአብሔር እንዲህይላል።እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፤እነሆ እኔ የወንዙን
  ውኃ በእጄ ባለችው በትር እመታለሁ፥ውኃውም ተለውጦ ደም ይሆናል።

  ዘጸአት 8:10 ሙሴም።አምላካችንን እግዚአብሔርን የሚመስል እንደሌለ ታውቅዘንድ እንደ
  ቃልህ ይሁን።  

  ዘጸአት 8:22 በዚያን ቀን በምድር መካከል እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁታውቅ ዘንድ፥በዚያ
  የዝንብ መንጋ እንዳይሆን ሕዝቤ የሚቀመጥባትን የጌሤምን ምድር እለያለሁ።

  ዘጸአት 9:14 በምድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ ታውቅ Hንድ በሰውነትህ በባሪያዎችህም በሕዝብህም ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ አሁን እልካለሁ።

  ዘጸአት 9:16
  ነገር ግን ኃይሌን እገልጥብህ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ላይ ይነገር ዘንድ ስለዚህ
  አስነሥቼሃለሁ።

  ዘጸአት 9:29
  ሙሴም።ከከተማ በወጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግዚአብሔርእዘረጋለሁ፤
  ምድሪቱ ለእግዚአብሔር እንደሆነች ታውቅዘንድ ነጎድጓዱ ይቀራል፥በረዶውም
  ደግሞአይወርድም።

  ዘጸአት 10:1–2
  እግዚአብሔርም ሙሴን።እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቁ ዘንድበ ግብፃውያን
  ያደረግሁትን ነገር ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጅህ በልጅልጅህም ጆሮች
  ትነግር ዘንድ፥ይህችንም ተአምራቴን በመካከላቸው አደረግ ዘንድ የእርሱን የባሪያዎቹንም ልብ አደንድኜአለሁና ወደፈርዖን ግባ አለው።

  ዘጸአት 12:11–12
  ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ጫማችሁን በእግራችሁ፥በትራችሁንም በእጃችሁ
  አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፥ፈጥናችሁም ትበሉታላችህ፤እርሱ የእግዚአብሔር
  ፋሲካነው። 12 እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፥በግብፅም አገር
  ከሰው እስከእንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤በግብፅም አማልክት ሁሉ
  ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤እኔ እግዚአብሔር ነኝ

  © 2013 – 2015, Samson Tilahun. All rights reserved.

  Like Be the first one who likes this post!

  2 thoughts on “ክፍል 4 – 6፡ እግዚአብሔርና ቃሉ፦ የሚናገር አምላክ

  1. ሰላም ለቅዱሳን ወንድሞችና እህቶች፤

   እግዚአብሄር የሚናገር አምላክ ስለመሆኑ በተሰጠን ትምህርት ዙሪያ ያለኝን መረዳት ለማንፀባረቅ ፈልጌ ነው። ይህን ሳደርግ አብረዉኝ ከሚማሩት ወንድሞችና እህቶች እንዲሁም ከአስተማሪያችን ከወንድም ሳሚ እርማትን በመጠበቅ ነው። በተማርነው መሰረት እግዚአብሄር የሚናገር አምላክ ነው፤ ይህም ንግግር የተጀመረው በዘላለም ዉስጥ በህላዌያት ማለትም በእግዚአብሄር አብ፣ በእግዚአብሄር ወልድና በእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ መካከል እንደሆነ ነው። ይህ ንግግር ከፍጥረት ታሪክ ጋር የጀመረ ሳይሆን አለም ከመፈጠሯ በፊት በዘመናት ዉስት የነበረ፣ ያለና የሚኖር ንግግር ነው። ህላዌያት ሁል ጊዜ እንደሰሩ ነው፤ ለምሳሌ ጌታ እየሱስ ወደ አባቱ ካረገ በኋላ ተመልሶ እስኪመታ ድረስ ያለስራ የሚቀመጥ የመሰለኝ ጊዜ ነበር። ነገር ግን ጌታ፣ እዚህ ምድር ላይ ለደቀመዛሙርቱና ለወደፊት አማኞች እንደጸለየዉ ሁሉ፣ ካረገ በኋላም የምልጃ አገልግሎት(Intercession Ministry) እያካሄደ ነው። እግዚአብሄር ከፍጥረቱ ጋር ያለዉ ግንኙነት ( በስድስቱ መንገዶች ማለቴ ነው)ፍጡር እስካለ ድረስ ሳያቋርጥ የሚቀጥል ነው::ያልዳነ ሰው ከሃጢአቱ የተነሳ ከእግዚአብሄር መገኘት ዉጭ ቢሆንም ፍርዱን እስኪያአገኝ ድረስ በመግቦቱ ዉስጥ ይኖራል። አንድ ነገር ታሰበኝ፤ መሬት በምህዋሯ ዙሪያ ለሁለት ቀናት መሽከርከር ብታቆም ወይም በምህዋሯ ላይ ያላት አንግል ቢሰፋ ወይም ቢጠብ ምን ያህል አደጋ ነው አልኩ። የእግዚአብሄር ትልቅነት በርግጥም ከአኧምሮ በላይ ነው። በዚህ ትምህርት ከምናገኘዉ መረዳት የተነሳ ራሳችንን ዝቅ በማድረግ፣ በተዋረደ ልብና በተሰበረ መንፈስ አምላካችን ፊት የምንወድቅ እንሁን።

   ጌታ ይባርካችሁ፣
   ካሳሁን

   1. Dear Kassahun, you’re spot on! He’s a gracious God and what an honor to be able to know Him this way and be as one of those who behold and partake in this dynamic life of the Truine God, not only as servants before His thrones, but as sons and daughters of the King, priest and kings of the most high God!

  Leave a Reply

  Your email address will not be published. Required fields are marked *

  Top