Home / Media Posts / 003: አራት መሠረታዊ መርሆች

003: አራት መሠረታዊ መርሆች

Posted on

በእያንዳንዱ ትውልድ መቼም መጪና ሂያጅ፤ እንዲሁም ወቅታዊና ጊዜያዊ፤ የሆኑ አያሌ ጉዳዮች አሉ። በአንድ ወቅት መሠረት አድርገን የያዝነው በሌላ ደግሞ “አይ እርሱማ አሁን አይሰራም” እንባላለን። በዚህ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ጥናት ክፍላችን ላይ ያተኮርነው – “ስለ ሕዝቅኤል መጽሐፍ፤ ከቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ጋር፤ ልናውቅ በሚገባን እና ዘመን መጠቅ በሆኑ በአራት የቅዱሳት መጻህፍት ባህርያት ላይ ነው” እነዚህ በተለይ በዘመናችን ቤተክርስቲያን ትኩረት ልትሰጣቸው የሚገቡ መሠረቶች ናቸው። እነዚህ ከብዙ የአጠናንና የአስተምህሮት ችግሮች እንድንጠበቅ ከመርዳታቸው ባሻገር፦

(1) ቤተክርስቲያን በቃሉ ላይ ትኩረት እንድታደርግ፤ ቃሉንም ስታስተምር በጥራት እንድታስተምር ይረዳታል ብዬ አምናለሁ።

(2) ቤተክርስቲያንን የመጽሐፍ ቅዱስ ስልጣኑን፤ በነጠላ በቂነቱን፤ ግልጽነቱን እና እግዚአብሔርን ለመምሰልና የእ/ር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ዝግጁ እንዲህን የሕይወት-ሞት-አስፈላጊነቱን እንድታስተውል ያደርጓታል።

(3) ቤተክርስቲያን ክርስቶስን ማዕከል ባደረገ አስተምህሮትና አምልኮት እንድትመሰረት ይረዷታል።

(4) ከነፍስ የተለየ ሰውነት ሙት እንደሆን ሁሉ፤ ከአውዱ የተለየ ጥናትም ሙት መሆኑን በማስተዋል፤ ቤተክርስቲያን ራሱን ፍንትው አድርጎ በቃልና በሥራ፤ በብዙ መንገድና ጎዳና ሲናገር እንዲሁም ሲሠራ የኖረውን እግዚአብሔር አምላክን የተናገረውን እንደተናገረ በታማኝነት እንድትገልጥ ግድ ይሏታል።

ስለ ሕዝቅኤል መጽሐፍ ልናውቅ የሚገቡ ዋና ዋና እውነቶች

1ኛ መርህ፦ የሕዝቅኤል መጽሐፍ ከሌሎች መጽሐፍት ጋር፤ ሙሉ በሙሉ እስትንፋሰ-አምላክ/አፊዎተ-አምላክ ነው (2ጢም. 3:14-17)።

፟► 2ኛ መርህ፦ የሕዝቅኤል መጽሐፍ ወደ ሕይወታችን አምጥተን ስናዛምድ፤ ኢየሱስን አንዝለል። በሕዝቄል መጽሐፍና በእኛ መካከል ኢየሱስ እንደቆመ መገንዘብ አለብን። ኢየሱስ መዝለል አደገኛ መዘዝ አለው (ማቴ. 5:17-19; 11:3; Cf. 2:15; ሮሜ. 3:21; 2 ቆሮ. 1:19-20; ሉቃ. 24፡25-27፤ 44-48; ዮሐ. 5፡38-47)።

3ኛ መርህ፦ መረዳት መታዘዝን ይቀድማል፤ ከመረዳት የመነጨ መታዘዝ ደግሞ ጥልቅ መረዳትን ይወልዳል (“ዶሮ ወይስ እንቁላል?”)። ከዚህ የተነሳ የመጀመሪያው ጥያቄ “እግዚአብሔር ምን እንደተናገረ፤ እንዴትና ለምን እንደተናገረ” መገንዘብ ነው (ዘዳ. 6:4-5; 4:1; 1ሳሙ. 15:22-23; ማቴ. 7:21, 24)። ካለመረደታ የመነጨ መታዘዝ ባዶ-መንፈሳዊነት ነው። ውስጡ ይዘት አልባ ነው። መታዘዝ የሌለው መረዳት ደግሞ እንደውርጃ ነው። ማቆጥቆጥ ጀምሮ ግን ከሥሩ ሁለት ጊዜ እንደተነቀለ ዛፍ ይመስላል። እኛም በተለይ ደግሞ በአሁኑ ዘመን ተንሰራፍቶ ያለው “ወቅታዊ-መንፈሳዊነት” የምለው ይህም “ትበረታለ፤ ከፍ ትላለህ፤ ትሻገራለህ፤ ከፍታውን ትወርሳለህ…ወዘተ” ነገር ግን በውስጡ እግዚአብሔርን ማወቅ፤ በቃሉ ላይ መመስረት፤ ክርስቶስን በማንነቱና በሥራው መረዳት ገንዘቡ ያላደረገ መንፈሳዊነት ነው። ከዚህ እጅግ ልንጠበቅ ይገባናል። በአንድ እጅ ኢየሱስ “በስምህ አጋንንትን አውጥተናል፤ በስምህ ትንቢት ተናግረናል [ሲሉት]…አላውቃችሁም” ሲላቸው፤ በሌላው እጅ ደግሞ “ይህ ቃሌን ሰምቶ በተግባር ያላዋለ ሰው [ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራን ሰው] ይመስላል..” ይለናል።

አስተርዕዮተ እግዚአብሔርና ቃሉ፡ በቃልና በሥራ ራሱን የገለጠው አምላክ

ሦስት ዓይነት አውዶች፡ ቅዱስ ቃሉን ለመረዳት ወሳኝ የሆኑ ነገሮች

4ኛ መርህ፦ የሕዝቄልን መጽሐፍ ስናጠናና ስናነብ ከተጻፈበት አውድ አንነጥለው፤ ሦስት አይነት አውዶች (ጥናቱን ይመ.) ይህንን በሜቀጥለው ቪዲዎ እንቀጥላለን።

© 2016 – 2017, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top