Home / Portfolio / WOG / ክፍል 3፡ መግቢያ

ክፍል 3፡ መግቢያ

Posted on

የቃላት አጠቃቀም / Vocabulary

ቃላቶች መግባቢያ እንደመሆናቸው መጠን የቃላት አጠቃቀም/ Usage ና አገባብ/ context ለፍቺ እጅግ ወሳኝነት አለው። የዚህ አላማ እንደሚከተለው ነው።     በመጀመሪያ ደረጃ አለመግባባትን ለማጥበብ ነው። ሰዎች ቃላትን በተለያየ መልኩ ሲጠቀሙ፤ ለአንዱ የሚሰጠው ስሜት ከሌላው እንዲለይ ያደርገዋል። በዚህ ምክኒያት አለመግባባት ይፈጥራል። ሁለተኛ የሚያሻሙ ሃሳቦችን ለማጥበብና ግልጽ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው። ሶስተኛ የእነዚህን ቃላቶች አጠቃቀም ማወቅ፤ የምናምነውን ነገር በትክክል እንደሚያስረዳ እንደማያፍር ሰራተኛ ሆነን እንድንቀርብ ይረዳናል። ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ ‘ሥላሴ’ የሚለው ቃል ነው። ይህ ቃል አገባብ ያለው፤ ትርጉም ያለው፤ ከተልምዶ ንግግር ውጪ የሆነ ከሞሆኑ አንጻር ተናጋሪው ሊሊ የፈለገውን ሃሳብ ፍንትው አድርጎ አንዲያቀርብ የተመረጠ ቃል ነው።

 1. አስተርእዮ/Revelation;(φανερόω-phanero/ἀποκάλυψις-Apokalupsis) ማለት መታየት፣ መገለጥ  የመሳሰሉትን ፍች ይይዛል፡ቃሉ- አስተርአየ- ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ነው፡፡ በጥናታችን ወደ ፊት እንደምንመለከተው ይህ ቃል ከመንፈሳዊ አብርሆት/ መረዳት ጋር ስለሚጋጭ ሰዎች አደገኛ ሥህተት ላይ ይወድቃሉ። “የዲያብሎስን ሥራ እንዲያፈርስ የእግዚአብሔር ልጅ ተገለጠ።” “በዘመኑም ጊዜ፥ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤ (ቲቶ 1፡ 3)” ሮሜ 1፡ 19፤ 16:26; 2 ቆሮ 7:12; ቆላ 1:26; 2 ጢሞ 1:10; ዕብ 9:8; 1፤ 4:9; ራዕ 15:4
 2. አብርሆት/Illumination/ ἀποκάλυψις-Apokalupsis)  ማለት ለትክክለኛ መረዳት መለኮታዊ ብርሃንን ማግኘት ማለት ነው:: ይህ በሕይወታችን መንፈስ ቅዱስ የሚሰራው ስራ ነው: “ዓይኖቼን ክፈት፥ ከሕግህም ተኣምራትህን አያለሁ።” (መዝ 119:18) የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። (ኤፌ 1:17)
 3. ቃለ-እግዚአሔር: እግዚአብሔር በባሕሪይው የሚናገር አምላክ ነው። ስለሆነም እስከአሁ ድረስ እየተናገረ ነው። ይህን ቃል ከመጽሀፍ ቅዱስ ለይተን እናየዋለን። መስሀፍ ቅዱስ የእ/ር ቃል ነው ነገር ግን ቃለ እ/ር ግን ከተጻፈው ቃል የሰፋ ነው።እግዚአብሄር ተናግሯል፤ እየተናገረ ነው አንደዚሁም ይናገራል። ይህ መናገር ግን ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። እንዚህን ትምህርቶቹን በጥንቃቄ ተከታተሉ!! ምንም እንኳ እግዚአብሔር በመናገር ላይ ቢሆንም፤ የሚናገረውን ቃል ግን ለአማኞች ነባራዊ መርሕ አይደለም።
  • “ምን ነው? የእግዚአብሔር ቃል የወጣ ከእናንተ ነውን? ወይስ ወደ እናንተ ብቻ ደርሶአልን?  ማንም ነቢይ ወይም መንፈሳዊ የሆነ ቢመስለው ይህች የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ እንደ ሆነች ይወቅ፤  ማንም የማያውቅ ቢኖር ግን አይወቅ።” (1 ቆሮ 14:36-37)
  • “እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን። ከእርሱም ይልቅ እጅግ የጸና የትንቢት ቃል አለን፤ ምድርም እስኪጠባ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪወጣ ድረስ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚጠነቀቅ ይህን ቃል እየጠነቀቃችሁ መልካም ታደርጋላችሁ።ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤  ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ።”” (2ጴጥ 1:19-21)
 4.  ሕላዌያት/Persons of the Trinity በአንዱ አምላክ መካከል ያለውን የአካላት ልዩነት ለመግለጽ የገባ ቃል ነው፤
 5. የአካላት ግብር: በአንዱ የእግዚአብሔር ግብር (ሥራ) ላይ የእያንድንዱን ሕላዌ ( የአብን/የወልድን/የመንፈስ ቅዱስን አስተዋጽዖ) ለማሳየት የገባ ቃል ነው። ይህ ሥራ/ ግብር በሁለት ይመደባል።
  • እግዚአብሔር ከራሱ ጋራ ያለው ግንኙነት፡ በመጀመሪያ እያንዳንዱ የሥላሴ አካላት/ ሕላዌያት ያላቸውን የውስጥ የርስ-በርስ ግንኙነትና ልውውጥ (Intra-Trinitarian relationship/ Opera Ad Intra) ይገልጻል። አብ ለወልድ አባትነቱ፤ ወልድ ደግሞ ለአብ ልጅነቱ፤ እንደዚሁም መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ከአብና ከወልድ በመውጣት እስትንፋስነቱ/ ሠራጺነቱ ነው። …አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና… “አብ ሙታንን እንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል። (ዮሐ 5:24-26.)
  • እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋራ ያለው ግንኙነት፡ ሁለተኛ፤ እግዚአብሔር በጸጋው፤ ይህም በፍጹም ነጻነቱ ፈቅዶ ፍጥረትን ከፈጠረ በኋላ  እግዚአብሔር ከፍጥረቱም ጋር ያለውን ግንኙነት ይገልጻል። ይህም የእግዚአብሔር ግብር (Opera Ad Extra) ይባላል. ይህም ሥራ በአምስት ይከፈላል፡
   • (1)  አስቀድሞ የማቀድ/ የመወሰን/ ሥራ (ዘላለማዊ ፈቃዱ) (Act of Decree/ Eternal Foreordination)፡ “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።…በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤  በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው።  እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን።  ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው። እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤  14 እርሱም የርስታችን መያዣ ነው” (Eph 1:7–14)
   • (2)  የፈጣሪነት ሥራ (ግብረ-ፍጥረት-Acts of Creation)፤ በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤
   • (3) የመግቦት ሥራ  (ግብረ-መግቦት-Acts of Providence)፤ የአግዚአብሔር መግቦት ማለት አንድጊዜ የፈጠረው ፍጥረት እንዲቀጥል መንከባከቡ (Preservation)፤ ማስተዳደሩ (Government)ና የፍጥረቱን ሩጫና ምርጫ ከዘላለም ሓሳቡ ጋር እንዲስማማ መቆጣጠሩ (Concurrence) ነው። እግዚአብሔር ጻድቅና ኀጥእ ሳይል ያለ “ተከፍሎ- ሳያዳላ” ሁሉንም ሰዎች በመግቦቱ ያኖራቸዋል፤ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ፍጥረትን ጨመሮ በመግቦቱ ተለይቷት አያውቅም። ያለ እርሱ መግቦት በሕይወት ሊቀጥል የሚችል ፍጡርም የለም፡፡ ክረምትና በጋ፤ ቀንና ለሊት፤ ሕይወትንና ሞትን፤ መዝራትና ማጨድ፤ ነገስታትን መሾምና ማውረድ…ወዘተ…
   • (4)  የመቤዠት ሥራ (ግብረ-ድነት-Acts of Redemption)፤
   • (5)  ራሱን-የመግለጥ ሥራ (ግብረ-አስተርእዮ-Acts of Revelation)
   • (6)  የመፍረድ ሥራ (Acts of Judgment)

ለማጠቃለል፡

ሐዋርያው ጳውሎስ በአቴና ከሰበከው ሥብከት፤ ከላይ የተዘረዘሩትን የ እግ ዚአብሔርን ሥራ መለየት ትችል/ይ እንደሆን እይ::

“እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ።  ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም፤  እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም።  ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙትእንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።  ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ። እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን እንኖርማለን። እንግዲህ የእግዚአብሔር ዘመዶች ከሆንን፥ አምላክ በሰው ብልሃትና አሳብ የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ እንዲመስል እናስብ ዘንድ አይገባንም።  እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል፤ ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን ረጋግጦአል።” ሐዋ 17:23–31

              

© 2013 – 2014, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top