መስቀልና ዙፋን

Posted on

CrossandThrone

ወንጌል የመንግስቱ መገለጥና በልጁ በኩል ድል መቀዳጀቱን የሚያውጅ የምስራች አዋጅ ነው! መንግሥቱ ግን የተመረቀችው በመስቀሉ ሥራ አማካይነት በመሆኑ ለአይሁድ መሰናክል ለግሪኮች ደግሞ ሞኝነት ሆነ; አብሮ የማይሔዱ እውነታዎች ናቸውና። ንጉሥ ይነግሳል እንጂ እንደ ወንጀለኛና እንደ ደካማ ባሪያ አይሰቀልም። ወንጌል ግን ሐይልንና ድካምን፤ ክብርንና ውርደትን፤ ዙፋንና መስቀልን፤ አንድ ያደርጋል። በወንጌል አማካይነት ክርስቶስን በመስቀል ድካም የተመረቀ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አናየዋለን! ወንጌል ጣቱን ቀስሮ የሚያመለክተን ስለ አባቱ ፈቅድ ሲል የሰው ልጆችን ሐጥያት ያስተሰርይ ዘንድ ከመላእክት አንሶ የነበረውን ነገር ግን አባቱ ከሙታን አስነስቶ ባረጋገጠለትና ጌታም ክርስቶስም እንዲሆን በሾመው በአንድያ ልጁ ላይ ነው።

ይህ ከ “እግዚአብሔር ሉዓላዊነትና የመንግስቱ መገለጥ” ክፍል ሥድስት ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው:: ሙሉውን ትምህርት ለመስማት እዚህ ይጫኑ

© 2013, Samson Tilahun. All rights reserved.

Like Be the first one who likes this post!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Top